በመጀመሪያ ኢትዮጵያዊነት የሚለው ትውልድ ትግል ያሸንፋል !!
- sepastopol
- Sep 13, 2014
- 1 min read
የሺ ዘመን አድሜ ያላት አገራችን ኢትዮጵያ በቀደምት ታሪክዋ ትልቅ የነበረችና የተከበረች ነበረች :: የጥንቷን ኢትዮጵያና የአሁኑዋን በታሪክ ገበታ ላይ አስቀምጠን አንደ የሰው ልጅ ንቃተ ሕሊናና አንደ ዘመኑ የዓለም ስልጣኔ ስናነጻጽራቸው ባሁኑ ጊዜ አንድያው በሸርተቴ ቁልቁል ወደ ታች እንደምትንደረደር እንገነዘባለን ::
ዛሬ ኢትዮጵያ በማይተኙላት የታሪክ ጠላቶቿና የእናት ጡት ነካሽ በሆኑት ባንዳ ልጆቿ የባህር በሯ ተዘግቶ አንገቷ ተቆርጦ ህዝቦቿ በዘር በጎሳ ተደራጅተው በዓይነ ቁራኛ አየተያዩና በራሳቸው መሬት የባዕዳን ባርያ ሆነው የጋራ ቤታቸው ኢትዮጵያ አገራዊ ሕልውናዋን ወደ ማጣት አየሄደች ነው :;
ይህንን የፈጠረው የባንዳዎች ስብስብ የሆነው (ህ.ወ.ሀ.ት) ባሳለፋቸው ፪፫ ዓመታት የኢትዮጵያ ሙህራንን ከአገራቸው በማስወጣት : በመግደልና አስር ቤት በማጎር አዲሱን ትውልድ በስነ ልቦና ጦርነት በኢትዮጵያዊነቱ አንዳያስብና አንዳይኮራ : ዓለም የመሰከረላትን ታላቅ አገር ስሟንና ክብሯን ዝቅ በማድረግና ሐሰታዊ ተረት ተረቶችን በመጻፍ ትውልድ በኢትዮጵያዊነቱ እንዲያፍርና የባዕዱ አገር ባህል ተከታይ እንዲሆን አድርጎታል ::
ይህንን አደገኛ እውነታ በማጤንና ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ዘላለማዊ አድርጎ ለማቆየት : ብሎም ኢትዮጵያን ለማዳን ኢትዮጵያዊ መሆን ግድ ይላልና "ኢትዮጵያኒዝም" (በመጀመሪያ ኢትዮጵያዊነት ) በሚል ጥሪ ሰፊ አገራዊ ተልዕኮ ያነገበ የማንቃት ንቅናቄ ተጀምሯል ::
እርስዎም ኢትዮጵያዊ ነኝ ካሉ ...ይህንን ዓላማችንን ተረድተው አብረውን ይሰለፉ ዘንድ አናሳስባለን ::
ኢትዮጵያኒዝም ይለምልም..በመጀመሪያ ኢትዮጵያዊነት !!
Comments