ኢትዮጵያኒዝም
በመጀመሪያ ኢትዮጵያዊነት
ሙዚቃ
የራስህ ቤተ መንግሥት ሁን፡፡ አለበለዚያ ዓለም እስር ቤትህ ትሆናለች !

ወቅታዊ ዜናዎች


ያልተስተዋለው ጥበቃ ‿︵‿︵
ድመቶች በቡድን ሰብሰብ ብለው እያወጉ እያለ አንበሳ አያቸውና ‹‹ጥርቅም አድርጌ ነው የምበላቸው››ሲል አሰበ፡፡
ነገር ግን ያልተለመደ አይነት የመረጋጋት እና የመስከን ስሜት ወረረው፡፡ስለዚህ እብሪቱን ትቶ አብሮአቸው ሊቀመጥ እና ወጋቸውን ለማዳመጥ ወሰነ፡፡
‹‹የአምላክ ያለህ ››አለች አንደኛዋ ድመት የአንበሳውን መኖር ልብ ሳትል‹‹ቀኑን ሙሉ እኮ ነው በጸሎት የዋልነው፡፡ ከሰማይ አይጥ እንዲያዘንብልን ጠየቅን››
ሌላኛዋ ከአፋ ነጠቀቻት፡፡
‹‹ግን እስካሁን ምንም ጠብ ያለ ነገር የለም፡፡ጌታ በትክክል መኖሩ የሚያጠራጥር ነገር እኮ ነው፡፡››
ሰማዩ በዝምታ ቀጠለ፡፡ድመቶቹም እምነታቸውን ማጣታቸውን አወጁ፡፡
አንበሳው ተነሳና ትቷቸው በራሱ መንገድ መጓዝ ያዘ፡፡እንዲህ እያሰበ
‹‹የነገርች አኳኋን ይገርማል፡፡ እነዚህ ደቃቃ እንስሳት ልገድላቸው ውጥን ነበረኝ፡፡ግን አምላክ አስቆመኝ፡፡ እንደዚህም ሆኖ ግን በመሎኮታዊ ጸጋ ማመናቸውን ተው፡፡ ስላጠጡት ነገር በጣም በመብሰክሰካቸው ስላገኙት ጥበቃ ምንም ይስተዋሉት ጉዳይ የለም፡፡››
የትንሹ ልጅ ርኀራኄ _________
ከቀኖች በአንዱ ቀን የአሥር ዓመቱ ልጅ አይስክሬም መመገብ ፈልጎ ካፍቴሪያ ውስጥ ጠረጴዛ ስቦ ተቀመጠና አስተናጋጇን ጠየቃት፡፡ “ትልቁ የአይስክሬም ኩባያ ስንት ይሸጣል?” አስተናጋጇ “75 ሳንቲም” አለችው፡፡ ትንሹ ልጅ እጁ ላይ ያዘውን ሳንቲም መቆጠር ጀመረ፡፡ ቀጠል እድርጎ አሁንም በድጋሜ ጥያቄ አቀረበ፡፡ “በትንሹ ኩባያ አይስክሬም ስንት ያወጣል?” በዚህ ጊዜ አስተናጋጇ በትዕግስት ማጣት ሁና “65 ሳንቲም” አለችው፡፡ ትንሹ ልጅም “እሽ ትንሹን አምጭልኝ” አላት፡፡ የቀረበለትን አይስክሪም ተመግቦ ሒሳቡን በሒሳብ መክፈያ ደብተሩ ውስጥ አስቀምጦ ወጣ፡፡ አስተናጋጇ መጥታ የሒሳብ መክፈያ ደብተሩን አንስታ ስትወስድ ባየችው ነገር ታላቅ ሀፍረት ተሰማት፤ የትንሹ ልጅ አድራጎትም ልቧን ነካው፡፡ ትንሹ ልጅ ለአስተናጋጇ ቲፕ ይሆናት ዘንድ በሒሳብ ደብተሩ ውስጥ 10 ሳንቲም ትቶ ነበር የወጣው፡፡
የአይስክሬሙን ዋጋ ደጋግሞ ይጠይቃት የነበረውም በእጁ ከያዘው ሳንቲም አንጻር ምንያህል ተጠቅሞ ለአስተናጋጇም ቲፕ እንዲተርፈው በማሰብ ነበር፡፡ ትንሹ ልጅ ለራሱ አይስክሬም ከመጠቀሙ በፊት ለአስተናጋጇም ርኀራኄ ተሰምቶት ነበር፡፡ በጎነትንና ለሌሎች ማሰብንም አሳይቷታል፡፡እራሱን ከማሰቡ በፊት ሌሎቸችንም ማሰብ እነዳለበት ተረድቷልና፡፡
ምንጭ ከcitehr Little Boy's Consideration በሚል ርዕስ የቀረበውን እንደተረጎምኩት
( #ምሥጋናው ግሸን ወልደ አገሬ)
12-01-2007 ዓ.ም


‿︵ አፍሪካዊው ‿︵
ጀርመን ሀገራ በሚገኘኝ በአንድ ዩንቨርስቲ ምግብ መመገቢያ አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡ አንዲት ወጣት ሴት ተማሪ በሰሀን ምግቧን ያዘችና ቁጭ አለች፡፡ ወዲያውኑ ግን መመገቢያ ማንኪያ ረስታ ስለመጣች ለማምጣት ተነስታ ሄደች፡፡ ወደ ወንበሯ ስትመለስ ግን በጣም መደመምን በፈጠረባት መልኩ አንድ ጥቁር አፍሪካዊ ሰው ወንበሯ ላይ ተቀምጦ እርሷ ትታው ከሄደችው ሰሃን ላይ ሲመገብ ደረሰች፡፡
በመጀመሪያ ተማሪዋ ፊት ላይ ግራ መጋባትና እና ጭንቀት ታየባት፡፡ ወዲያው ግን እራሷን አረጋግታ ምናልባት አፍሪካዊው የአውሮፓውያኑን በተለይ ከግል ንብረት ጋር የሚያያዝ ስልጣኔን ባያውቅ ነው ብላ ገመተች ወይም የራሱን ምግብ ከፍሎ ለመመገብ የሚበቃ ገንዘብ የለውም ብላም በማሰብ ወደ ሰውየው በመሄድ ፊት ለፊት በመቀመጥ ወዳጅነትን የሚጋብዝ ደማቅ ፈገግታ ለገሰችው አፍሪካዊውም በበኩሉ የሞቀ ፈገግታ መለሰላት፡፡
ተማሪዋ እራሷን መርዳት እናዳለባት ስለተረዳች መመገቢያ ሹካ አንስታ በቅን ደስታ እና ፈቃደኝነት ምግቧን ከአፍሪካዊው ጋር መጋራት ያዘች፡፡ እርሱ ሳላጣ በላ፡፡እርሷ ሾርባውን ወሰደች፡፡ወጡን ተጋሩ ፍራፍሬውንም አብረው ተመገቡ፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ሰውየው ፊት ላይ ምንም አይነት ቅራኔ ወይም የመረበሽ ስሜት አልታየም :: ከተማሪዋ ፊት ላይ ደግሞ ለስላሳ፣ ጋባዥ፣ እና ደግነትን የተሞላ ፈገግታ ነበር፡፡
ምሳቸውን እንዲህ ተመግበው እንደጨረሱ ተማሪዋ ቡና ለማምጣት ተነሳች፡፡
ይሄኔ ነበር አፍሪካዊው ሰው ጀርባ ባለው ሌላ ወንበር ላይ ገና ስትቀመጥ ያንጠለጠለችውን ኮት እና ማንም ያልነካውን ምግቧን ያየችው፡፡
‿︵ ምንም እንኩዋን ከስልጣኔ ከፍታ ለይ ቆሚያለሁ ብላ ያሰበችው ተማሪ ብትሸወድም አፍሪካዊው አብራው ስትመገብ ባለመከፋቱና እንዲሁም ፈቃድን በመቸር ስልጣኔውን አሳይቷታል፡፡
ሁለቱ ዝሆኖች
ሰውዬው በሀሳብ ተውጦ በመጓዝ ላይ ሳለ ድንገት በአንድ የገበሬ ግቢ ውስጥ ዝሆኖች በገመድ ታስረው ቆመው ይመለከታል። ቆሞ አስተዋለ።‘~~~~~ "እነዚህን የሚያካክሉ ግዙፍ ፍጥረታት እንዴት በነዚህ ቀጫጭን ገመዶች ታዘው ሊቆሙ ይችላሉ?" በዚህ ቁመናቸው በረትም ሆነ ብረት ሰባብረው መሄድ እንደሚችሉ አሰበ። የዚህን ጥያቄ መልስ ሳያገኝ ጉዞውን ለመቀጠል አዕምሮው አልፈቀደለትም። ቀጥ ብሎ ወደ ውስጥ ገባና ገበሬውን አገኘው።
"ለመሆኑ እንዴት ቢሆን ነው በዝች ቀጭን ገመድ ታስረው ሊቆሙ የቻሉት?" ሲል ጠየቀው።
ገበሬውም የሰውየው መገረም አግባብ እንደሆነ ከገለጸለት በሁዋላ .........."ምን መሰለህ ጌታዬ! ዝሆኖቹን ከህጻንነታቸው ጀምረን በነዚሁ ገመዶች ነው የምናስራቸው። ህጻን በነበሩ ጊዜ ይሄ ገመድ እነሱን ይዞ ለማስቀረት በቂ ነበር። እያደጉ ሲሄዱም ምንም እንኳን በአካል ቢገዝፉም ዛሬም ድረስ ገመዱ ሀይል ያለው ይመስላቸዋል። ስለዚህ በጥሶ ለመሄድ ምንም ጥረት አያደርጉም!" ሲል መልሰለት።
የሰው ልጅም እንዲሁ ነው። ልጆች ሳለን በብዙ ቀጫጭን ገመዶች እንታሰራለን። ስናድግ እነዚህ ገመዶች በአምሮዋችን እንደገዘፉ ይቀሩና ዘመናችንን ሁሉ ጠፍንገው እንዳሰሩን እንኖራለን። በነዚሁ ገመዶች እንደተተበትብን እናስባለን፣ እንምላለን፣ እንከራከራለን፣ እንጣለለን፣ .......ወዘተ!
እነዚህ ገመዶች ደግሞ በባህል፣ በቋንቋ፣ በሀይማኖት፣ በዘርና በጎሳ ሰበብ የሚመጡ ናቸው። ሰው ግን የታሰረበትን ገመድ በጥሶ ሳይሆን ፈትቶ መላቀቅ የሚችል ባለ አዕምሮ ነው። ይህንንም የሚያደርጉት በጣም ውስን ሰዎች ናቸው።

ጓደኛ
