top of page

    ዋዘኛ ጊዜ... 

ቆሜ ተቀምጬ..ተኝቸም አሰብኩት ፡

የትላንቱን ህልሜን..ዛሬ እንደቀጠልኩት ፡

ነገ ይደርስና..ሳሰላስል ውሉን ፡

ሳልፈታው ቋጨኹት ፡

ጊዜ እያታለለ..እንደዋዛ አለፍኩት ። 

                         ዕዳ 

       

አላውቅ ቀን እጣየን 

       ዛሬ እሞት ነገ እሞት ፡

         በህይወት ጎዳና 

         ስሄድ ስሮጥበት ፡:

       እንደ የዋህ ፍጡር 

         ለእርድ እንደሚነዳ ፡

      እኔም እጓዛለሁ 

         ይዤ የሞት ዕዳ ።

         ቁራሽ ዳቦ 

 

 

ተፈጭታ እክታልቅ በውስጤ 

የዳቦ ቁራሽ ቆራጣ ፡

ከደረቅ ሆዴ ተጣብቃ፡ 

 አሻገረቻት ህይወቴን 

ከትላንት መከራ መንጭቃ ።

    አንገቴን ስደፋ 

 

ድብዘዝ ያለ እንደ ጭጋጋት ፡

ቀዝቀዝ ያለ እንደ ንጋት ።

ገርገብ ያለ ያልተዘጋ ፡

ሰፈፍ ያለ ደሞ ያልረጋ ።

ብትን የሚል ስሜት አለኝ ፡

በትካዜ ጉም የሸፈነኝ ።

 

 

ሰላም ቢገኝ 

 

እስኪ ጋደም ልበል 

ትንሽ ላንቀላፋ 

አትቀስቅሱኝ ጭራሽ 

በህልም ዓለም ልጥፋ ።

 

           ሰጋሁ 

 

ልቤ እንደተመኘው..ፍላጎቴ እንዳዬ ፡

ትላንት ላደረኩት..ከዚያም ቀደም ብዬ ።

አላሰብኩለትም..አላዘንኩለትም ፡

ለህግ ለስርዓት..ቲንጥ አልተጨነቅኩም ።

ዛሬ ላይ ግን ቆሜ..እንዲህ እንደዋዛ ፡

ስለ ነገ ሳስብ.. ለነብሴ ቤት ታዛ ።

ፍርሃት ፍርሃት.. ይለኛል ፡

ፍርድህ... ያሰጋኛል ።

የምትገርም ዓለም 

 

የዓለምን ገጽታ እያየሁ 

አዋቂ ጥበበኛ ነኝ እላለሁ ፡

እራሴን አደንቃለሁ ።

  ግን..

ትልቅ የስጋት አምባ ፡

ካድናቆቴ በስተጀርባ ፡

አለ የሃዘኔ እንባ ።

   ታዲያ እንባዬን ሳየው ፡

   መፍለቂያ ምንጩን ሳውቀው ፡

   ደግሞ ያስቀኛል ሁኔታው  ።

የዖሪት ዘፍጥረት ጣምራ ጎኑ ፡

አብሮ የመኖር ቃል ኪዳኑ ፡

መች ይሆን መፈጸሚያ ቀኑ ፡?

      ዝምታ 

እንቅልፍ ያሳጣኝ መኝታ 

ሰላም የነሳኝ ጧት ማታ ፡

የውስጥ ጩኸት ነው ዝምታ ።


አንተ ቻይ አንተ ታጋሽ 
አንተ የቆሎ ተማሪ
አንተ የቅኔ ቀማሪ
አንተ የእግዚአብሔር አገልጋይ 
አንተ የኑሮ ተበዳይ
አንተ የቃል ኪዳን ቀለበት
ያረፈብህ የእግዚአብሔር ጣት 
ስለ እመብርሃን ብለህ 
ለእፍኝ ቆሎ አንገት ደፍተህ
ዓይንህን ወደ ሰማይ 
ልብህን ወደ አዶናይ 
ልከህ መዝሙረ ዳዊትን ስታዜም 
ከሀጢአት ሰውረኝ ኤሎኪም 
ኤሎኪም ሰውረኝ
ለልቤ ቅንነት ሙላልኝ
ከይቅርታህ መርቅልኝ 
ጥበብንም አስተምረኝ 
እያልክ ፀሎትህ የሰመረ 
ሰምና ወርቅህ የዳበረ
የፍቅር እስከ መቃብር ቤተኛ
የኢትዮጵያ ታሪክ መገኛ 
አንተ የቆሎ ተማሪ
አንተ የእመብርሃን ስም ጠሪ
ሁሉ እየመጣ ሲሄድ
አንተ ብቻ ኗሪ ፣ አንተ ብቻ ቀሪ ።

 

 

 

የቆሎ ተማሪ

ተዛማጅ ገጾች 

news
news
g7pf news
arbegnoch

         ያነበቡትን ወደዉታል ? አንግዲያውስ ላንባቢዎች አዳዲስ መረጃዎችን ለማቅረብ ይተባበሩን ..ኢትዮጵያኒዝም 

Donate with PayPal

© 2023 by "This Just In". Proudly created with Wix.com

bottom of page