top of page

አንባገነኖች ከሚባሉት በጥቂቱ ...


Professor Richard Pankhurst ‚ Kass and Kass ከሚለዉ መፅሃፍ ላይ Tewodros as innovator በሚለዉ ጥናታዉ ፅሁፋቸዉ ላይ የተወሰነዉን ፅሁፍ አቅርቤላችኃለዉ፡፡
አፄ ቴዎድሮስ የአውሮፓ ዘመናዊ ትምህርት እንዲስፋፋ፤ ዘመናዊ የጦር መሳሪያ እንዲቋቋም፤የሰለጠነና የታጠቀ ዘመናዊ ሰራዊት እንዲገነባ፤ ህዝባቸዉ በእዉቀትና በጥበብ እንዲዳብር፤ የፊዉዳሊዝማ ስርዓት የባሪያ ንግድ እና ኃላቀር ስራዎችና አስተሳሰቦች እንዲቀሩ፤ አንድና ጠንካራ የተከበረች ኢትዩጵያ እንድትመሰረት ፤መሬት የህዝበ ሃብት እንዲሆን ፤ በአጠቃላይ በሃገራቸዉ ስር ነቀል ለዉጥ እንዲመጣ እዉነተኛ ራዕይ የነበራቸዉ እንቁ የሚሊኒየሙ ሃገር ወዳድ ታላቅ መሪ ናቸዉ፡፡
Theophius Waldmeier ………. Mortiz Hall ከብዙ ሙከራና ድካም በኃላ ትንሽ mortar እና ጥይቶችን ሰራ…….. ንጉሰም በደስታ ዘላሉ እግዚአብሄርንም አመሰገኑ ( but he was not fully satisfied for the mortar was too small for him , so he order Mortitz to cast bigger one.
ፀሃፊ ትዕዛዝ ወልደማርያም "…… ከመላ ሃገሪቱ ብዛት ያለዉ ብራስ ተሰብስቦ በጋፋት ፋብሪካ ቀለጠ….. ንጉሱም የመጀመሪያዉን መድፍ ሰሩ፡፡ ስሙም ቦምባ ተባለ…. ይህንን ያህል ቁመትና ስፋት ያለዉ መድፍ በኢትዩጵያ ታይቶም አይታወቅም… ይህ መድፍ አንድን ሰዉ በአንዱ ጫፍ ወደ ሌላዉ ያሾልካል…. "
Haruzd Rassam …….. ንጉሱ የክሪሚን ጦርነት ታሪክ ከሰሙ በኃላ መድፉን ሴብስቶፓል ብለዉ ጠሩት… 7 ቶን ክብደት ነበረዉ ከ500 ያላነሰ ሰዎች መድፉን ወደ ተራራዉ ጫፍ (መቅደላ) ለማድረስ ለመጎተት አስፈልጓል…. ንጉሱ አንድ ቀን Rassamን እንዲህ ብለዉ ነበር ተናገሩት "በህይዎቴ ደስተኛ የሆንኩበት ቀን ቢኖር ይህን መድፍ ሰርቸ ያየሁበት ቀን ነዉ "
እንግሊዛዊ የጆኦግራፊና የታሪክ ተመራማሪና Clements Markham በመቅደላ የኢትዩጵያዉ ንጉስ 24 ብራስ መድፎች……. 4 የብረት መድፎች … 9 የብራስ ሞርታሮች ነበሯቸዉ አንዳንዶቹ በግለፅ የአማርኛ ፊደል ተቀርፆባቸዋል፡፡ እንግሊዞች ጦር መቅደላን ከተቆጣጠሩ በኃላ ሁሉንም የኢትዩጵያዊን መሳሪያዎችና ፋብሪካዎች አዉድመዉታል፡፡
ዘላለማዊ ክብርና ሞገስ ለእዉነተኛዉ ባለራዕይ ለአባ ታጠቅ ካሳ ለቋራዉ አንበሳ!!
# Gondar history and culture /የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ታሪክና ባህል ገጽ/

ሰባስቶፖል 

ጠንካራ እና የተከበረ መሪ ለመሆን ሰብዓዊ ርህራሄ፡ ጥልቅ የሀገር ፍቅር ስሜት እንዲሁም በእድሜ እና በልምድ የዳበረ ብስለት እንደሚያስፈልግ የታመነ ነው። ነገር ግን አለማችን በሺህ በሚቆጠሩ አመታት ታሪኳ፡ ከዚህ በብርቱ ያፈነገጡ፡ መላው አለምን ጉድ ያስባሉ ብዙ አምባገነን መሪዎችን አስተናግዳለች። እነኚህ ሰብዓዊነት ያልፈጠረባቸው ቁንጮ አምባገነኖች ፖለቲካዊ አላማቸውን ለማስፈጸም፡ ስልጣናቸውን ለማስጠበቅና ሀይላቸውን ለማጠናከር፡ ከቁብም የማይቆጥሩትን የሰው ልጅ ህይወት፡ በሺዎችና በሚሊየኖች በሚገመት ቁጥር፡ ያለርህራሄ ወደ ሞት ሸኝተዋል።

ታዲያ ብዙዎች አምባገነን ሲባል ቀድሞ የሚታሰባቸው፡ ፈጥኖ ድቅን የሚልባቸው የናዚው ቁንጮ አዶልፍ ሒትለር ነው። ነገር ግን ከወራት በፊት ውጤቱ በድረ-ገጽ የተለቀቀ አንድ ጥናት የቻይናን አብዮት መርተው፡ ኋላም ህዝባዊ ሪፐብሊክ ቻይናን መስርተው ለሰላሳ አመት ያህል አንቀጥቅጠው የገዟት ማኦ ዜዶንግን(ማኦ ሴ-ቱንግ)ያህል ብዙ ህዝብ የፈጀ አምባገነን መሪ እስካሁን አልተገኘም፡ በአለማችንም አልታየም። የጥናቱ ውጤት በገደሉት ሰው ብዛት፡ የአለማችን የምንግዜም ቁንጮ አምባገነኖች ናቸው ያላቸውን አስር መሪዎች ይፋ አድርጓል። ጓድ መንጌም በድምሩ 1.5 ሚሊየን ሰዎችን በመፍጀት ከቁንጮ አምባገነኖች ተርታ በዘጠኝነት ተሰልፏል።

 

የጥናቱ ሙሉ ውጤት የአምባገነኖቹን ዝርዝርና ያስገደሉትን ሰው ብዛት ይፋ እንደሚከተለው ይፋ አድርጓል፦
1)ማኦ ዜዶንግ፡ ቻይና(1943-1976)—78 ሚሊየን
2) ጆሴፍ ስታሊን፡ ሶቭየት ህብረት (1922-1953)—23 ሚሊየን
3)አዶልፍ ሒትለር፡ ጀርመን (1934-1945))—17 ሚሊየን
4)ሊዎፖልድ ሁለተኛ ወይም ዳግማዊ ሊዎፖልድ፡ ቤልጂየም(1865-1909)—15 ሚሊየን
5)ሒደኪ ቶጆ፡ ጃፓን(1941-1944)—5 ሚሊየን
6)ኢስማኤል ኤንቨር፡ ቱርክ (1913-1919)—2.5 ሚሊየን
7)ፖል ፖት፡ ቻምቦዲያ (1963-1981) —1.7 ሚሊየን
8)ኪም ኢል ሱንግ፡ ሰሜን ኮሪያ (1948-1994) —1.6 ሚሊየን
9)መንግስቱ ሐይለማርያም፡ ኢትዮጲያ(1974-1991)—1.5 ሚሊየን
10)ያኩባ ጎዎን፡ ናይጄሪያ(1966-1975)—1.1 ሚሊየን

ከተጠቀሱት አስር አምባገነኖች፡ አምስቱ ሀገራቸውን ሲያስተዳድሩ የነበረው ሶሻሊስታዊ ርዕዮተ-አለምን በሚከተል ፓርቲ መሆኑ የሚነግረን አንዳች እውነት አለ። ይህ ከታች ያለው link፡ THE LOGIC OF POLITICAL SURVIVAL ለሚል መጽሀፍ የቀረበ ነው። መጽሀፉ በሙስና፡ በጦርነት፡ በአምባገነንነት የተጨማለቁ መሪዎች እንዴት ለአመታት ስልጣን ይዘው መቆየት እንደቻሉ፡ ሰላምና ብልጽግናን ማስፈን የቻሉት ደግሞ ስልጣናቸው ማጠሩን በተመለከተ መሰረታዊ ጥያቄ ያነሳል፤ መልስ ለመስጠትም ይሞክራል።መልካም ንባብ! 

 

ጥናቱ እንደ አዲስ ሲካሄድ ደሞ ባንዳው መለሰ ዜናዊን እንደሚያካትት ምንም ጥርጥር የለውም ::

ደመና ገላጩ ከተወለደ 105 ዓመት ሊሆነው ነው!!

የዛሬ 105 ዓመት ጥቅምት 7 ቀን 1902 ዓ.ም አንድ ሕጻን ወደ ምድር መጣ፡፡ የበቀለበት ደብር እንዶር ኪዳነ ምህረት ትሰኛለች፡፡ የህጻኑ አባት ካህን ሲሆኑ አባ አለማየሁ ሰሎሞን፣ እናታቸው ደግሞ ወ/ሮ ደስታ ዓለሙ ይባላሉ፡፡ የህጻኑ ወላጆች በአካባቢው ልማድ መሰረት ልጃቸውን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የትምህርት ስርአት ውስጥ እንዲያልፍ አድርገውታል፡፡ በዚህም በደብረ ኤልያስ በደብረ ወርቅ እና በዲማ ትምህርቱን እየተከታተለ በመንፈስም በአካልም አድጓል፡፡ በኋላም ወደ አዲስ አባባ በመምጣት በሲዊዲሽ ሚሽነሪ ት/ቤት እና በተፈሪ መኮንን ት/ቤት ትምህርቱን ተከታትሏል፡፡ ኋላም በአዲስ አበባ በመምህርነት በጎጃም በጉምሩክ ሥራ ባለሙያነት ሠርቷል፡፡ በተጨማሪም ሐገሩን በአርበኝነት፣ በዲፕሎማትነት በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አገልግሏል፡፡ (በኢጣሊያ ወረራ ወቅት 1929-1933 ዓ.ም. ከልዑል ራስ አምኃ ኃ/ስላሴ ጦር ጋር በአርበኝነት ሲጋ ቆይቶ በምእራብ ኢትዮዽያ በጣሊያን ተማርኮ፥ ወደ ኢጣሊያ በግዞት ከቆየ በኋላ በ1936 ዓ.ም. ወደ ሀገሩ በነፃነት ተመልሷል።) 
ከዚህ ሁሉ በላይ ግን ታላቅ ክብር እና ሞገስን ያሰጠው በህዝብም ልብ ውስጥ ያስቀመጠው ለኢትዮጵያ ሥነጽሑፍ ያበረከተው አስተዋጽዖ ነው፡፡ አስቀድሞ ሌሎች ሁለት መጸሐፍትን ማሳተም ቢችልም ከሁሉ በላይ ስሙን በደማቅ ቀለም እንዲጻፍ ያደረገው ዘመን አይሽሬ ሥራው የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሥነጽሁፍ ዐምድ መሆኑ የተመሰከረለት “ፍቅር እስከ መቃብር” (1958) የተሰኘው ልብ ወለዱ ነው፡፡ ይህ መጸሐፍ ከወጣ ግማሽ ክፍለ ዘመን ሊያስቆጥር እየተቃረበ ሲሆን ዛሬም ድረስ የኢትዮጵያ ሥነጽሑፍ መለኪያ ሆኖ ሲጠቀስ ይስተዋላል፡፡
የዚህ መጸሐፍ ደራሲ ሀዲስ አለማየሁ ከዚህ በተጨማሪ፡- 
የአበሻና የወደፊቱ ጋብቻ (1929 ተውኔት)
ተረት ተረት የመሰረት (1948)
ኢትዮዽያ ምን አይነት አስተዳደር ያስፈልጋታል? (1966)
ትዝታ (1985 ግለ ታሪክ)
ወንጀለኛው ዳኛ (1974)
የልምዣት (1980) የተሰኙ መጸሐፍትን ለንባብ አብቅተዋል፡፡ በህይወታቸው መጨረሻ አካባቢ ነሐሴ 27 ቀን 1991 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ የሰጣቸው ሲሆን ኅዳር 28 ቀን 1996 ዓ.ም. በ94 ዓመታቸው ከ10 አመት በፊት ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል፡፡ እኒህ የኢትዮጵያ ሥነጽሑፍ ባለታሪክ ሰው ከተወለዱ ጥቅምት 7, 2007 ዓ.ም ልክ 105 ዓመታቸው ይሆናል፡፡

 ሀዲስ አለማየሁ

ዘይግረም...

በሀገራችን በጣም ለአጭር ጊዜ የነገሠውን ንጉሥ ያውቁታል? ምን ያህል ጊዜ የነገሠ ይመስልዎታል? በኢትዮጵያ በጣም ለአጭር ጊዜ የነገሠው ንጉሥ “ገስዮ” እንደሚባል ትገልጻለች፡፡ “ገስዮ” ከቀዳማዊ ምኒሊክ ጀምሮ ሲቆጠር 15ኛው ንጉሥ ሲሆን የነገሠው ለ6 ሠዓታት ብቻ ነው፡፡ ሁሉም እየመጣ እጅ ሲነሳውና በበዓለ ሲመቱ ብዙ ክብር ሲቸረው በሥነ ልቡናው ዝግጁ ስላልነበር በድንጋጤ እንደሞተ ይነገራል፡፡ (እንዲኽም አይነት ንጉሥ ነበር- ነፍስ ይማር!)

ፖስታ 

የፖስታ አገልግሎት በኢትዮጲያ ምድር 1890ወቹ መጀመሪያ ላይ ሊዮን ቹፍንግ በተባለ በአገራችን ለረጅም ጊዜ የኖረ የፈረንሳይ ነጋዴ አማካኝነት እንዲሁም የንጉስ የቅርብ ወዳጅ በነበረው በስዊዙ ተወላጅ ቢተወደድ አልፍረድ ኢልግ አማካሪነት ከዛም በአጤ ምንሊክ ትዕዛዝ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ መከፈቱን ከዚህ በፊት ይህን በተመለከተ በፈረንጅ አንደበት ብዛት ያላቸው ጽሁፎች ማቅረቤን አስታውሳለሁ።

ፖስታ በአገርኛ ዘይቤ "ጦማር" ትባላለች ፖስታ አመላላሽ ደግሞ "ጦማሪ" የፖስታ ቤት "ደጀ'ጦምር" ይባሉ ነበር። ምንም እንኩዋን እስከ ሁለተኛው የጥሊያን ወረራ ዘመን ድረስ የአገሬው ህዝብ እምብዛም የጦምር አገልግሎት ባያስፈልገውም ነገር ግን ደጀ'ጦምር በሯን ለአገልግሎት ከፍታ ለበርካታ አመታት ጥቂቶቹን ተጠቃሚወችን ስታገለግል ኖራለች።

አጤ ምንሊክም በተለያዩ አውራጃወች, ወረዳወች እና ክፍለሀገራት በተለያየ ተግባራት ያሰማሮአቸው ሹሞች ዘንድ መልዕክታቸውን የሚልኩት በዚህ በዘመናዊው የጦማር አግልግሎት ነበር, በዚህም ምክንያት በአንዳንድ ቦታወች ላይ ጦማሪወች የንጉስ መልዕክተኛ እየተባሉ ይጠሩ እንደነበር በታሪክ ተጽፎአል።

አንዱ ጦማሪ ከአንድ መንደር ብዙ መንገድ ተጉዞ በወዲያኛው መንደር ለሚገኘው ለሌላው ጦማሪ የተላከውን ጦማር ያቀብል እና ይመለሳል, ታዲያ እንደዚህ እየተቀባበሉ አንዲት ከንጉሱ የተለክች ጦማር በክብር በቁርበት ተጥቅልላ በሳልስቷ ሐረር ትገባ ነበር። ከዚህ በተረፈ በዛን ዘመን በአብዛኛው የጦማር አገልግሎት ተጠቃሚወቹ በኢትዮጲያ ምድር የኖሩ ወይም ለተለያየ ጉዳይ ይመጡ በነበሩ ምዕራባውያን እና የሩቅ ምስራቅ ተወላጆች ነበሩ። 

 

የኢትዮጵያ ቱሪዝም ኮሚሽን “የ13 ወር ፀጋ” በሚል ርዕስ ከሚያሳትማቸው ፖስተሮች የዝነኛዋ “ውቢት ኢትዮጵያ” አስደናቂ ተፈጥሮአዊ ውበትና ግርማ ሞገስ የታየበት ፖስተርዋ ሁሌ ከማይረሱን መሃል አንዳቸው ነው። 

የ4 ልጆች እናት የነበረችው አልማዝ አመንሲሳ የወለጋ ክፍለ ሀገር ተወልዳ አድጋ ከልጆችዋና ለቱሪዝም ኮሚሽን ተቀጥረው ይሰሩ ከነበረው ባለቤቷ ጋር አዲስ አበባ ትኖር ነበር። ከልጇ ዲቦራ ቢሩ ልንረዳው እንደቻልነው አልማዝ አመንሲሳ ሞዴል ወይ የፊልም ተዋናይት አልነበረችም። 1970ዎቹ የብሄራዊ ቱሪዝም ኮሚሽን ለገቢ ማሰባሰብያ የሚሆኑ ድንቅ ድንቅ ፎቶዎችን አንስቶ ለመልቀቅ የፈለገበት ወቅት ነበር። አልማዝ በቱሪዝም ኮሚሽን ፎቶ የመነሳት እድል አጋጥሟት ነው ለ <<ውቢት ኢትዮጵያ>>ነቷ ልታበቃ የቻለችው። ኩባዊ ኢትዮጵያዊው የታሪክ ምሁር ኤድዋርዶ ባይሮኖ እንዳስረዳን አልማዝ አመንሲሳ ለፎቶዉ 5 ሳንቲም ሳትቀበል ፎቶዉ ያስገኘና እስከ ዛሬ እያመነጨ ያለው ገቢ ሙሉ ለሙሉ ለኮሚሽኑ እንዲረከብና የሃገራችን ቱሪዝምን እንዲያገለግል ፍላጎቷ ነበር።

በ2000 ዓም ለህክምና ወደ አሜሪካ አምርታ ህዳር ወር 2001 ዓም ውቢት ኢትዮጵያ በሞት ተለየችን። 

መልከ መልካሟ ውቢት ኢትዮጵያ ሀገርዋን ላገለገለችበትና ስማችን ላስጠራችበት ምስጋናችን ይገባታል።
 

--ከአውድማ የወደቀው የጥሊያን ጦር አድዋ 1896--

በእንግሊዝ አገር ውስጥ የምትኖሩ ጓደኞቼ የዚህን ምስል original ገጽታ እና ሌሎችም የአድዋን ጦርነት የተመለከቱ የተለያዩ ምስሎች London ከተማ በሚገኘው British war Museum ውስጥ ታገኙታላችሁ የዚህን ምስል ሙሉ ታሪክ ደግሞ ባለፈው የጠቀስኩት በቀድሞው የእንግሊዙ archaeologist Sean Mclachian “The Italian Disaster in Ethiopia ብሎ በጻፈው መጽሀፍ ውስጥ ተጥቅሶአል።

ስለ አድዋ ጦርነት 28 መጽሀፍት በ28 ታሪክ ጸሀፊያን ተጽፎአል ስለዚህ ታሪክን የማወቅ ፍላጎት ያለው ያገኘውን መረጃ እያነበበ እና እውቀቱን እያሰፋ ይሄዳል እንጂ የጳውሎስ ኞኞን መጽሀፍ ብቻ አንብቦ በቃኝ ታሪክ አውቃለሁ እያለ መከራከር አይችልም። በተጨማሪ ደግሞ እስካሁን ድረስ ይህ አባቶቻችን በባዶ እግራቸው እና በራበው ሆዳቸው እስከ አፍንጫው ታጥቆ የመጣውን የአውሮጳ ወራሪ ድባቅ የመቱበት አኩሪ ታሪካቸው ፊልም ተስርቶ ለትውልድ አለመቀመጡ ያሳዝነኛል።

ጋዜጠኛው አይዋሽም። የጥሊያንን ጦርን ተከትሎ የመጣው እና ወደጦሩ አውድማ በጠራው ሰማይ ላይ በመንጋ እየተንጋጉ ከሜዳው የወደቁትን የጥሊያን ወታደሮች የበሰበሰ በድን ሊመንችፉ የሚበሩትን አሞሮች አቅጣጫ ተከትሎ በመሄድ ታሪኩን የዘገበው የጥንቱ እንግሊዝ ጋዜጠኛ Thomas Hughes አንድም ሳይደብቅ ተርኮታል።

....የተቆራረጥውን እጅ ፤ እግር እና አንገት በየቦታው ተዝረክርኮ በአይሁ ቅስፈት ወደዚህ ግድም የመጣሁበትን ዕለት እረገምኩ ከዛም በከባድ ፍርሀት ተውጬ ሸበጤን ጥዬ በሀይለኛ ጩኸት ቁጥቋጦውን አልፎ ወደሚገኘው ባዶ መንደር በሩጫ ተፈተለኩ....The frightened war reporter wrote

 

 

ስንት ሰዓት ነው?

ሰዐት...በምስሉ ላይ የሚታየው የወርቅ ሰዐት ከዘጠኝ ዓመት በፊት በጄኔሻ ለአንድ ሀብታም አረብ ነጋዴ በጨረታ ከ$50,000 በላይ የተሸጠው, በምዕራባውያን ዕለተ አቆጣጠር በ1877 ዓ ም አልፍረድ ኢልግ በተባለ ኢትዮጲያ ውስጥ ይኖር በነበረ የስዊስ ተወላጅ የእጅ ባለሙያ ተሰርታ በምዕራባውያን ዕለተ አቆጣጠር በ1893 ዓ ም አጤ ሚኒሊክ ሊዎን ቹፍኑግ ለተባለ ለኢትዮጲያ ብዙ መልካም ውለታወችን የዋለ የፈረንሳይ ዜጋ ነጋዴ ለምስጋና የሰጡት ስጦታ ነበረች።

ይህቺ ድንቅ 18k የወርቅ ዕለተ መለኪያ በምዕራባውያን አቆጣጠር በ1894 ዓ ም በአዲስ አበባ ከሊዎን ቹፍንግ ቤት ውስጥ ባልታወቁ ሰውች ተሰራቃ ደብዛዋ መጥፋቱን የቀድሞው ትውልድ ታሪክ አስታዋሽ ጳውሎስ ኞኞ ግልጽ አድርጎ ነግሮናል። ከዛም በ2009 ዓ ም ለ105 አመታት ተድብቃ ከኖረችበት በድንገት ወጥታ ተቀባብታ እና ተወልውላ በጄኔሻ ከተማ ለጨረታ ቀርባ ለአንድ የኦማን ተወላጅ ሀብታም ነጋዴ ከላይ በተጠቀሰው መሸጧ ተነግሮአል።

ከየት እንደተገኘች ይህን ሁሉ ዘመን የት እንደነበርች ማን እንዳመጣት የሚገልጽ ምንም አይነት መረጃ አልቀረበም, የጠየቀም ሰው የለም። ለዛሪ እኔም ሰዓት ወደ ኢትዮጲያ መቼ እንደገባች የሚገልጽ መረጃ ያለው ምንም አይነት ታሪክ የለኝም, ነገር ግን በዛ ዘመን የነበረችው የታላቅዋ ብሪታንያ ንግስት ቪክቶሪያ ለአጼ ተዎድሮስ እና ለአጼ ዮሐንስ በተለያዩ አመታት በስጦታ መልክ የወርቅ ሰዓቶች እንደሰጠቻቸው በታሪክ ተጽፎአል።

ይህቺ ውድ እቃ... ለሊት,.. ውድቅት.., አጥቢያ.. ውጋግ,... ማለዳ,... ጧት...ቀትር... ሰዓት,... ከሰዓት... ምሽት እና ማታን ተራ በተራ ለያይታ ለማህበረሰቡ ያሳወቅች ጠቃሚ መገልገያ ናት። በ1900 መጀመሪያወቹ ላይ የነበሩት ሊቅ አለቃ ታዬ, "ጊዜ ነጋሪ" ወይም "እለተ መለኪያ" ብለው ተርጉመዋታል።

 

በ1866 እ.ኤ.አ ከእንግሊዝ ንግስት ቪክቶሪያ ዋና መልዕክተኛ ሃርሙዝ ራሳም ጋር በህክምና ባለሙያነት አብሮ ወደ አቢሲኒያ የመጣዉ ዶክተር ሄነሪ ብላክ በአጼ ቴዎድሮስ መቅደላ እስር ለ2 ዓመት ታስሮ በቆየበት ወቅት ስለ አጠቃላይ ሃገሪቱ እና ስለ አጼ ቴዎድሮስ መንግስት በተመለከተ ከእስር ተፈትቶ ወደ ሃገሪ እንግሊዝ ሲመለስ ‘’A NARRATIVE OF CAPTIVITY IN ABYSSINIA’’ በሚል ባሳተመዉ መጽሃፉ ዉስጥ ብዙ ያልተነገሩና የማናዉቃቸዉን ታሪኮችን አካትቷል፡፡ ከዚህም ዉስጥ ሁላችንም እንደምናዉቀዉ የአጼ ቴዎድሮስን መልክ በተለያዩ ባለሙያዎች በቀለም ቅብ ስዕልና በእርሳስ በተሳለ ስዕል / sketch/ ብቻ ነዉ የምናዉቀዉ፡፡ በመሆኑም የአጼ ቴዎድሮሰን ምስል ከሰዓሊያን ሰዓሊያን ይለያያል፡፡ ነገር ግን ዶክተር ሄነሪ ብላንክ የአጼ ቴዎድሮስ መልክና ቁመና ምን እንደሚመስል በዚህ መጽሃፍ ገጽ 10 ላይ እንዲህ ይላል፡፡

 

“When I first met Theodore, in January, 1866, he must have been about forty-eight years of age. His complexion was darker than that of the majority of his countrymen, the nose slightly curved, the mouth large, and the lips so small as hardly to be perceived. Of middle size, well knit, wiry rather than muscular, he excelled as a horseman, in the use of the spear, and on foot would tire his hardiest followers. The expression of his dark eyes, slightly depressed, was strange; if he was in good humor they were soft, with a kind of gazelle-like timidity about them that made one love him; but when angry the fierce and bloodshot eye seemed to shed fire. In moments of violent passion his whole aspect was frightful: his black visage acquired an ashy hue, his thin compressed lips left but a whitish margin around the mouth, his very hair stood erect, and his whole deportment was a terrible illustration of savage and ungovernable fury.’’

ይህንን የዶክተር ሄነሪ ብላንክ መጽሃፍ “የእስራት ዘመን በአበሻ አገር ፡” የቴዎድሮስ እሥረኛ በሚል አቶ ዳኘዉ ወልደ ሥላሴ ለአጼ ቴዎድሮስ መቶኛ ዓመት መታሰቢያ እንዲሆን በተረጎሙት ገጽ 26 እንዲህ ይላል ፡-

“በ1858 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ አጼ ቴዎድሮስን ስናገኝ እድሚያቸዉ 48 ይሆን ነበር ፡፡ መልካቸዉም ከብዙዎቹ አበሻዎች ጠቆር ያሉ ጠይም፤ አፍንጫቸዉ ደፍጠጥ፤ አፋቸዉ ሰፋ፤ ከንፈሮቻዉ ትንንሽ፤ ጠጋጋ ቀጠን ያሉ፤ በፈረሰኝነታቸዉና በጦር አወራወር ስልታቸዉና በወታደርነታዉ የተመሰገኑ ፤ ጠንካራ የሆነዉን ጭፍራቸዉን ለማቸነፍ ችሎታ ያላቸዉ ሰዉ ነበሩ፡፡ ጎድጎድ ያሉት ጥቋቁር ዓይኖቻቸዉ አገላለጥ አስደንጋጭ ሲሆን በሰላም ጊዜ ደስ የሚያሰኙ ፤ የሰዉን ፍቅር የሚያስገኙ፤ ለስላሳ ሁነዉ በተቆጡ ጊዜ ደግሞ በርበሬ መስለዉ የሚያስደነግጡና የሚያሸብሩ ፤ እሳተ ጋሞራ የሚወረዉሩ ነበሩ፡፡ በድንገት ሲቆጡ መላ አካላታቸዉ የሰዉን ልጅ ከፍ ካለ ድንጋጤ ላይ ይጥላል፡፡ ጠይሙ ገላቸዉ ሲኮሰኮስ ፤ስሱ ከንፈራዉ ሲንቀሳቀስና ጠጉራቸዉ ሲቆም በጠቅላላዉ ሰዉነታቸዉ የአንበሳነት ጠባይ የያዘ አስደንጋጭ ይሆናል፡፡”

ይህንን በተመለከተ ተዋቂዉ ደራሲ ጳዉሎስ ኞኞ “አጼ ቴዎድሮስ” በሚለዉ ግሩም የታሪክ መጽሃፋቸዉ ዉስጥ ይህንን የዶክተር ሄነሪ ብላንክ መጽሃፍ በአቶ ዳኘዉ ወልደ ሥላሴ የተተረጎመዉን ገለፃ መሰረት በማድረግ የአጼ ቴዎድሮስ መልክ እንዲህ በሚመስል መልኩ አስለዉታል፡፡

በአሹ ዋሴ የቀረበ

- Ethiopianism Poetics -
.
April is National Poetry Month - What an excellent excuse to reveal the magnificence and mysticism of Ethiopianism through poetry

Frances Ellen Watkins Harper (September 24, 1825 – February 22, 1911) was an African-American 
abolitionist, poet and author. Born free in Baltimore, Maryland, she had a long and prolific career, publishing her first book of poetry at age 20 and her widely praised Iola Leroy, at age 67. In 1850, she became the first woman to teach sewing at the Union Seminary. 
.

 

.
Yes, Ethiopia yet shall stretch
Her bleeding hands abroad;
Her cry of agony shall reach
The burning throne of God.
.
The tyrant's yoke from off her neck,
His fetters from her soul,
The mighty hand of God shall break
And spurn the base control.
.
Redeemed from dust, and freed from chains,
Her sons shall lift their eyes;
From lofty hills and verdant plains
Shall shouts of triumph rise.
.
Upon the dark, despairing brow
Shall play a smile of peace;
For God shall bend unto her woe,
And bid her sorrows cease.
.
'Neath sheltering vines and stately palms
Shall laughing children play;
And aged sires, with joyous psalms,
Shall gladden every day.
.
Secure by night and blest by day,
Shall pass her happy hours;
Within her peaceful bowers.
.
Thy bleeding hands abroad;
Thy cry of agony shall reach
And find the throne of God. 
.

(Source: wikipedia; Poems on Miscellaneous Subjects(1854))

ተዛማጅ ገጾች 

news
news
g7pf news
arbegnoch

         ያነበቡትን ወደዉታል ? አንግዲያውስ ላንባቢዎች አዳዲስ መረጃዎችን ለማቅረብ ይተባበሩን ..ኢትዮጵያኒዝም 

Donate with PayPal

© 2023 by "This Just In". Proudly created with Wix.com

bottom of page