ኢትዮጵያኒዝም
በመጀመሪያ ኢትዮጵያዊነት
ሙዚቃ
የራስህ ቤተ መንግሥት ሁን፡፡ አለበለዚያ ዓለም እስር ቤትህ ትሆናለች !

ወቅታዊ ዜናዎች

ኢትዮጵያኒዝም !
ከአምስት ሺህ በላይ ዕድሜ እንዳላት አንዳንድ ታሪካዊ መረጃዎች የሚናገሩላት አገራችን ኢትዮጵያ በተለይ ከንግስተ ሳባ ጀምሮ አንድነቷን ጠብቃ ነጻነቷን አስከብራ የቆየች ሲሆን ፡ ጥንታዊው የአክሱም መንግስት ስልጣኔ ለዛሬው እድገት መሰረት ሆኖ እያገለገለ ይገኛል ።
ጥንታዊው የግዕዝ ፊደልም የተገኘው ከሳባ ቋንቋ ሲሆን እስከ 19 ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ህዝባዊ ቋንቋና የስነ ጽሁፍ ቋንቋ በመሆን አገልግሏል ።
ግዕዝ ከሴማዊያን ቋንቋዎች መሃከል አንዱ ሲሆን..ሴማዊያን ቋንቋዎች በመባል የሚታወቁትም..ግዕዝ ፡ ትግራይኛ ፡ አማረኛ ፡ ጉራጌኛ ፡ አደርኛ ፡ ጋፋትኛና አርጎብኛ ናቸው ።
ኢትዮጵያ በራሷ ቋንቋ ቅዱስ መጽሃፍን ከጻፉት የመጀመሪያዎቹ የዓለም አገሮች መካከል አንደኛዋ ከአፍሪካም የመጀመሪያዋ አድርጓታል ። የቅዱስ መጽሃፍ ትርጓሜ በምታስፋፋበት ጊዜ ከብዙ አህጉሮች ላይ የጠፋውን መጽሃፈ ሄኖክን ጽፋ ያስቀመጠች በመሆኗ ለዓለም ህዝብ የተሟላውን ቅዱስ መጽሃፍ ልታበረክት ችላለች ። "(ይህ መጽሃፍ በእንግሊዞች ተሰርቋል )
ኢትዮጵያ የራሷ የሆነና ከአውሮፓውያን ለየት ያለ የዓመታት የወራት ቀናትና የሰዓታት አቆጣጠር አላት ። ይኸውም ..በዘመነ ዮሃንስ 366 ቀኖች ፡ በዘመነ ማቲዎስ ፡ ማርቆስና ሉቃስ 365 ቀኖች ሲኖሩ በአንድ ዓመት 12 ወራትና እያንዳንዱ ወር 30 ቀን አለው ። በየአመቱ 5 ወይም 6 ቀን ትርፍ ይኖራል ። እነዚህ ትርፍ ቀናትም ጳጉሜ በመባል ይታወቃሉ ። ስለዚህም ነው ኢትዮጵያ 13 ወራት ጸሃይ የሚወጣባት ሃገር ናት ተብሎ የሚነገርላት ።
ኢትዮጵያኒዝም !

ንግሥተ ማክዳ

ንጉስ ላሊበላ
ከክርስቶስ ልደት አንድ ሺህ ዓመት ያህል ቀደም ብሎ ከነበሩ ገናና ነገስታት የምትወለደው ንግስት ማክዳ (ሳባ) በአያቶቿ ዙፋን ተቀምጣ በአክሱም መናገሻዋ ኢትዮጵያንና የመንን ትገዛ ነበር ::
፭፪ የኢትዮጵያ ንግስት በመሆን የምትታወቀውና ከአክሱም ነገስታት ሁሉ እጅግ የላቀች እንደ ነበረች በብዙ የታሪክ ጸሐፊዎች የሚነገርላት ንግስተ ማክዳ (፱፭፯_፲፩፫) ዓ.ም ኢትዮጵያንና የመንን በአንድነት ትገዛ ነበር :: በንግሥት ማክዳ ዘመን የኢትዮጵያ ወሰን በሰሜን አስከ ላዕላይ ግብጽ : በምዕራብ አስከ እያንዛ ባህር ወይም ነጭ አባይ : በምስራቅ ባህረ ኤርትራን ተሻግሮ አስከ የመን ዳርቻ : በደቡብ እስከ ማዳጋስካር ነበር :: በቀድሞዎቹም ሆነ በአሁኑ ትውልድ በኢትዮጵያውያን አመለካከት የንግሥት ማክዳ ታሪክ በሀገራችን ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ስፍራ ይዞ ይገኛል ::
ከክርስቶስ ልደት በፊት ባሉት ክፍለ ዘመናት ከነበሩት ነገስታት ውስጥም ዋነኛዋ እንደሆነች አድርገው ይቆጥሯታል ::
ንግስት ማክዳ (ሳባ) ከታላቁ የእስራኤል ንጉስ ጠቢቡ ስሎሞን ጋር በነበራት የክብር ግንኙነት ቀዳማዊ ምኒልክን አርግዛና የአይሁድ እምነትን ይዛ እንደመጣች : ከዚያም ጊዜ ጀምሮ የእስራኤል ሃይማኖትና ስርዓት ወደ ኢትዮጵያ ሊገባ እንደቻለ ክብረ ነገስት ያረጋግጣል ::
የንጉስ ሃርቤ የአንድ ወገን ወንድም የሆነው ላሊበላ ወደፊት ታላቅ ሰው እንደሚሆን እናቱ ያወቀችው ህጻኑ አልጋው ላይ ተጋድሞ ሳለ በንብ ሰራዊት ተከቦ ባየች ጊዜ ነበር ። እናቱ ይህንን የንብ ከበባ ባየች ጊዜ በመንፈስ ተቃኝታ ላሊበላ በማለት በታላቅ ድምጽ ጮኽች የሚል አፈታሪክ አለ ።
ላሊበላ ማለት ንቦች ሃይልህን ስልጣንህን አወቁ እንደማለት ነው ።
ከዛጉዌ ነገስታት ውስጥ ታላቅና እጂግ መንፈሳዊ የነበረው ከ 1157 እስከ 1197 ዓ.ም የነገሰው ላሊበላ ከአለት ድንጋይ ተፈልፍለው የታነጹ አስደናቂና እንደ ሰንሰለት የተያያዙ አብያተ ክርስቲያናትን አሳንጿል ።
መናገሻ የሆነችው የሮሃ ከተማም የንጉስ ላሊበላ የክብር ማስታዎሻ እንድትሆን በማለት መጠሪያ ስሟ ላሊበላ በሚል ስያሜ ተለወጠ ።
ላሊበላ ለረጅም ጊዜ በስደት ኢየሩሳሌም ቆይቷል ። ላሊበላ የተሰደደው በ 1160 ገደማ ሲሆን በዚያን ጊዜም ዕድሜው ወደ ሃያ ዓመት ይጠጋ ነበር ። በ1185 ላሊበላ ወደ አገሩ ኢትዮጵያ ተመልሶ ንጉስ ሃርቤንን ከስልጣን በማስወገድ በትረ መንግስቱን ጨበጠ ።
የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ ለመፈጸም የውቅር አብየተ ክርስቲያናቱን ግንባታ በመጀመር እጹብ ድንቅ የሆኑ ከአንድ ወጥ አለቶች ተጠርበው የወጡ አስራ አንድ አብያተ ክርስቲያናትን አሳንጿል ።
ላሊበላ ያሳነጻቸው አብያተ ክርስቲያናት ገጽታዎች ከቅድስቲቱ ምድር በስደት ቆይታው ይዟቸው የተመለሰ ይመስላል ። ለምሳሌ ከተማውን አቋርጦ የሚያልፈውን ወንዝ ዮርዳኖስ ብሎ ሰይሞታል ።
ከአስራ አንዱ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ቤት ጎለጎልታ የተባለውና በተለየ መልኩ የታነጸው በኢየሩሳሌም ያለውን የቀራንዮ መካነ መቃብር እንዲወክል ተደርጎ ነው የተቀረጸው ።
በአጠገቡ ያለው ደብረዘይት የተባለ ተራራም የተሰየመው ክርስቶስ በመጨረሻው ሰዓት በአይሁድ ጭፍሮች በተያዘበት ቦታ ስም ነው ።
ላሊበላ የራሱን መዲና አዲስቱ እየሩሳሌም ለማድረግ ከመጣሩ በተጨማሪ በዘመነ መንግስቱ ከእየሩሳሌም ጋር የነበረው ግንኙነት አድጓል ።
በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ ፖሊሲ እንዲሁም ከስነ ህንጻ ግንባታና ከደረሰበት መንፈሳዊ እድገት አንጻር ሲገመገም የላሊበላ ዘመነ መንግስት የዛጉዌ ስርወ መንግስት ቁንጮ ነበር ማለት ይቻላል ።
የንጉስ ሃይለ መለኮት ልጅ የሆኑትና በ 1844 እ.ኤ.አ የተወለዱት ዳግማዊ ምኒሊክ አባታቸው በ 1856 በሞት ሲለዩ በሁኔታው የተደናገጡት የሸዋ መኳንንት ወጣቱን ንጉስ ምኒሊክ ለአጼ ቴዎድሮስ በሰላም አስረከቡ ። አጼ ምኒሊክ ከአገር ወዳዱ አጼ ቴዎድሮስ ጋር ጎንደር በኖሩበት ጊዜአቶች ከአጼ ቴዎድሮስ ጋር የቀረበ ግንኙነት እንደነበራቸውና ከንጉሱ ስለ አገር ፍቅር ፡ ፖለቲካና ፡ የጦር ጥበብ እንዲሁም ስለ አገር ብልጽግናና ሌላም ቁም ነገሮች እንደተማሩ ይነገራል ።
እኒህ ብልህና አርቆ ሃሳቢ ተብለው የሚነገርላቸው ንጉስ..ሃይላቸውን በጥበብ ካደራጁ በኋላ በመጋቢት 26 ቀን 1889 ዓ.ም የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ተብለው ዘውድ መጫናቸው ሲረጋገጥ ፡ የጎጃም ንጉስ ተክለሃይማኖት ፡ የወሎ ገዥ ራስ ሚካኤል ፡ የላስታ ገዥ ዋግሹም ብሩ ፡ የሃረርጌ ገዥ ራስ መኮንን እንዲሁም የአውራጃና የወረዳ ገዥዎች ለአዲሱ ንጉሰ ነገስት ታዛዥነታቸውንና እውቅና መስጠታቸውን በይፋ አስታወቁ ። አዲሱ ንጉሰ ነገስት በበኩላቸው ካጣሊያን መንግስት ጋር ወዳጅነት ፈጥሮ ሃይላቸውን በጦር መሳሪያ ለማጠናከር ሲሉ በጄኔራል ባልዲ-ሴራ መሪነት ድል አድርጎ የያዘውን ደጋውን የኤርትራ ክፍለ ሃገር የጣሊያን ግዛት መሆኑን እውቅና ሰጠው ነበር ። በሌላ በኩል ይህ ክፍለ ሃገር አጼ ዮሃንስ በአንድ ወቅት ለማስመለስ ሞክረው ሳይሳካላቸው በመቅረቱ ለመተው ተገደው የነበረ መሆኑ ይታወሳል ።
በሌላ በኩል ደሞ በምኒሊክ ስልጣን መያዝ ያልተደሰቱት የመላው ትግራይ ገዥ ራስ መንገሻ ያባታቸውን ዘውድ የመውረስ ምኞት ነበራቸውና ጣሊያኖች ደጋውን የኤርትራ ክልል በመያዛቸው ተደስተው ነበር ። ስለዚህ ራስ መንገሻ ራሳቸው የጣሊያን ግዛት ወሰን መረብ ፡ በለሳ ፡ ሙና መሆኑን ተስማምቻለሁ ሲሉ ከጄኔራል ጋንዶልፊ ጋር የስምምነት ውል ተፈራረሙ ። በመቀጠልም የጣሊያንን የዲፕሎማቲክ ኮር መኖሪያ በትግራይ እንዲመሰረት ፈቀዱ ።
በዚያን ጊዜ ከራስ መንገሻ ጋር በዚህ ጉዳይ ስምምነት ያልነበራቸው ብቸኛ ከፍተኛ ሹም ራስ አሉላ ነበሩ ። እኒህ ስመጥር ጀግና ጣሊያኖች በሃማሴን ግዛት መገኘታቸውን ካለመፍቀዳቸውም ሌላ የጣሊያን ወሰን መረብ የተባለውን ውል በፍጹም እንደማይቀበሉት ገልጸው በራስ መንገሻ ላይ አምጸው ነበር ።
በሚታወቀው የውጫሌ ውል የኢጣልኛው ቅጅ በተለይ አንቀጽ 17 ላይ ኢትዮጵያ በኢጣልያ የበላይነት የምትተዳደር የሚል እንደሆነ ስለተረጋገጠ አጼ ምኒሊክ ስምምነቱን አፍርሰው እንዳልተቀበሉትም ለአውሮፓ መንግስታት አስገነዘቡ ።
በዚህም የተነሳ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም ከአክሱም 20 ኪ.ሜ በስተምስራቅ በሚገኘው ዓደዋ ላይ ዘመናዊ መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ወራሪ ጦር በተባበረ የኢትዮጵያ ሰራዊት ድል አድርገው መልሰውታል ።
በዚህም ታሪካዊና ትልቅ አንጸባራቂ አፍሪካዊ ተጋድሎ መሳካት ሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች የተሳተፉበትና ትልቅ አገር ወዳድነትና ወገናዊነት የታየበት ጦርነት ነበር ።..ከነዚህም መሃከል ራስ መንገሻ ምንም እንኳ ከጣሊያን ይበልጥ ምኒልክን በጠላትነት ቢመለከቷቸውም የትግራይ መሬት የምንሊክ ጦር ሃይል እንዲጠቀምበት ፈቀዱ ። ይህም በኢትዮጵያውያን ባህል መሰረት የውጭ ጠላት ሊያጠቃ ሲመጣ እርስ በርስ መተጋገዝ የተለመደ በመሆኑ ራስ መንገሻ ራሳቸው 40 ሺህ የሚሆን ሰራዊታቸውን በማዝመት በውጊያው ተሳታፊ ሆነዋል ። እንዲሁም ንጉሰ ነገስቱ ከወሎ ክፍለ ሃገር ገዥ ራስ ሚካኤል ፡ ከጎጃም ገዥ ተክለሃይማኖት የድጋፍ ሃይል እንደሚደርሳቸው የተረጋገጠላቸው ሲሆን ፡ ከሁሉም ይበልጥ የሃረርጌው ገዥ ራስ መኮንን የክተት አዋጅ አስተላልፈው ሰባት ሺህ ወታደር በማስታጠቅ በጉዞ ላይ መሆናቸውን አረጋገጡ ። ከዚህም በተጨማሪ ለጣሊያን መንግስት ተሰልፈው ይዋጉ የነበሩት ራስ ስብሃትና ራስ ሃጎስ ከነወታደሮቻቸውና ከሙሉ ትጥቃቸው ጣሊያንን ከድተው ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጋር መቀላቀላቸው ተረጋገጠ ።
በየካቲት ወር መጨረሻ ጀግናው ራስ አሉላም ከራስ መንገሻና ከራስ ወሌ የድጋፍ ሃይል አግኝተው በመረብ ወንዝ ሸለቆ አካባቢ የጣሊያንን ወታደሮች አጥቅተው በማባረር አዲቋላን አልፈው ከዚያም አዲ ወግሪ ድረስ በመዝለቅ የጠላት ሃይል ወደ ኋላ እንዲያፈገፍግ አድርገውታል ።
በዚህ ትልቅ የዓደዋ ጦርነት የንጉሰ ነገስቱ ባለቤት እተጌ ጣይቱ ጀግንነታቸውን ስላስመሰከሩ ከጦርነቱ በኋላ "ጣይቱ የዓደዋ አርበኛ " የሚል መጠሪያ አግኝተው ነበር ።
በምኒሊክ ዘመነ መንግስት የስልጣኔ ጮራ የሚፈነጥቁ አዳዲስ የአሰራር ስልቶችና የልማት ስራዎች በአዲስ አበባ የተጀመረበት ዘመን ነበር ።
ከእነዚህም ውስጥ..የፖስታ ቴምብር ፡ ቴሌፎን ቴሌግራፍ አገልግሎት ፡ የባንክ አገልግሎት ፡ የገንዘብ ማውጣት ፡ ዘመናዊ ትምህርት ቤትና ሆስፒታል እንዲሁም ከአዲስ አበባ -ጂቡቲ የምድር ባቡር መስመር መዘርጋት ይገኙበታል ።
ከአጼ ምኒሊክ አጠገብ ብዙ ጊዜ የኖረውና ከእርሳቸው ጋር የጠበቀ ወዳጅነት መመስረት የቻለው ዴካስትሮ የተባለው ደራሲ ስለምኒሊክ ቀጥሎ የሚነበበውን ጽፏል ።
በተፈጥሯቸው ቁጡ እና ጦርነት አፍቃሪ አይደሉም ። የአማራና የኦሮሞ ዝርያ ያላቸው ሲሆን በደም ስራቸው ውስጥ ከአባታቸው የወረሱት አርቆ አስተዋይነት ፡ ከእናታቸው ደግሞ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ኦሮማዊ የእናትነት ርህራሄና ደግነት አላቸው ። ከሁለቱ ብሄረሰቦች የወረሱት የተቀላቀለ ደም በሰውነታቸው ውስጥ ዳብሮ በመንጸባረቁ በአስተሳሰባቸውም ውስጥ እጥፍ የሆነ አዎንታዊ ገጽታ ሊኖራቸው ችሏል ። ይህም በአነጋገራቸው በአድራጎታቸውና በእንቅስቃሴአቸው አማካኝነት ሲገለጽ እንደኖረ የማይታበይ ሃቅ ነው ።
..በዚህም ጸባያቸው እምዬ ምኒሊክ የሚል መጠሪያ የተሰጣቸው አስተዋይ መሪ..የተሻሻለ አገራዊ አስተዳደርን ከመፍጠራቸው ውጭ ዘውዳዊ አገዛዛቸው ተራማጂና በምዕራብ መንግስታት ዘንድ ተወዳጂነት ያተረፈ ነበር ።
ከራስ ስሁል ሚካኤል እስከ ራስ አሊ ድረስ ያለው ጊዜ (1762-1845) ዘመነ መሳፍን በመባል ይታወቃል ። ይህ የተባለበትም ምክንያት በብሉይ ኪዳን እንደ ተጻፈው በዚያን ዘመን በእስራኤል ንጉስ አልነበረም ። ሁሉም ሰው የፈቀደውን ያደርግ ነበር ። (መሳፍንት 21፡ 25) የሚለውን ስለሚያስታውስ ነው ።
ይህ ጊዜ የጨለማው ዘመን በመባልም በሌላ ስሙ ይታወቃል ።
በተለያዩ ክፍለ ሃገሮች ሙሉ ስልጣንና ሃይል የነበራቸው መሳፍንት ብቻ ነበሩ ። ጠንካራ ማዕከላዊ መንግስትም አልነበረም ።
በዚህ የጭንቅ ዘመን መካከል ጎንደር ውስጥ ድምቢያ ከምትባል ትንሽ ወረዳ ከምትገኝ ቋራ ከምትባል ስፍራ ልዩ ስሟ ቸርጌ ከምትባል መንደር ከዝቅተኛው ቤተሰብ የተወለደው ካሳ ሃይሉ ተነሳ ።
ቋረኛው ካሳ በነበረው የጦር ታክቲክ ብስለት የተነሳ ባጭር ጊዜ ውስጥ ሊጠናከር ቻለ ።
ወዲያውም የጎጃሙን ደጃዝማች ጎሹን ፡ የጎንደሩን ራስ አሊን ፡ የሰሜንና የትግራይ ትግሪኚን ፡ ደጃች ውቤንና የሸዋን ንጉስ ሃይለመለኮትን ተራ በተራ ድል አደረጋቸው ።
ቴዎድሮስ ጀግና ንጉስ ስለነበረ በዚህ የተነሳ ከ(1845-1860) ዓ.ም በነበረው የ 15 ዓመት መንግስት ኢትዮጵያን እንደ ጥንቷ በአንድ ሃይል ንጉሰ ነገስት ስር ተጠቃልላ ለመተዳደር አበቃት ።
አጼ ቴዎድሮስ ኢትዮጵያን በዘመናዊ አስተዳደር ለመምራትና ኢትዮጵያን በዘመኑ ከነበሩ ሃያላን አገራት ጎራ ለማሰለፍ የጋለ ሃሳብ ነበራቸው ።
ዘመናዊት ኢትዮጵያን ከመገንባት በተጨማሪ የኢትዮጵያን ግዛት በማስፋትና ቀይ ባህርን በመሻገር ቱርኮችን ድል በመንሳት እየሩሳሌምን ጨምሮ ለማስተዳደር ያልሙ ነበር ።
ይህንንም ህልማቸውን በመረዳት..ድግስ ላይ..
ታጠቅ ብሎ ፈረስ..ካሳ ብሎ ስም ፡
አርብ አርብ ይሸበራል..እየሩሳሌም ። በማለት ይቀነቀንላቸው ነበር ..። እሳቸውም ሞቅ ሲላቸው..
..መይሳው ካሳ ባጭር ታጣቂ ..ዘመድ ከዘመድ አደባላቂ ።
የኢትዮጵያ ባል የእየሩሳሌም እጮኛ እያሉ ይፎክሩ ነበር ..።
አጼ ቲዎድሮስ አንዳንድ አስቸኳይና ጠቃሚ ነገሮችን እንደ መንገድ ቅየሳና የጦር መሳሪያ ማሰራት ተያይዘውት ስለነበር በመጀመሪያ ጊዜ ሰባስቶፖል በሚባል ስም የሚታወቀውን ምድፍ በጋፋት መንደር አሰሩ ።
ወታደሮቻቸውም በደሞዝ እንዲተዳደሩ የቤተ ክርስቲያን ማደሪያ እንዲቀነስ ማድረግ ሃሳብ ነበራቸው ።
ወደ ታሪካቸው መጨርሻ ምዕራፍ የእንግሊዝ መንግስት አውሮፓዊያኑን እስረኞች ለማስፈታት ከሰላሳ ሺህ የሚበልጥ ጦር ከዘመናዊ ትጥቅና ዝግጂት ጋር በመላኩና የንጉሱን ቦታ በሚፈልጉ ኢትዮጵያዊያን መሳፍንት እገዛ መቅደላ ላይ በተደረገው ጦርነት የአጼ ቴዎድሮስ ኢትዮጵያን አንድ አድርጎ ስልጣኔ የማስፋፋት የተቀደሰ ዓላማ ከንቱ ሊሆን ቻለ ።
..ኢትዮጵያ ከእንግዲህ ምን ይዋጥሽ..?
ተስፋ ባጣ ምድረ በዳ ፡
ያንድ እውነት ይሆናል ዕዳ ።
እናት እስትንፋስ አልሆንኩሽም
ሆኜብሽ መራር መካሪ ፡
ሩቅ አላሚ..ቅርብ አዳሪ ።
በሚያዝያ ወር መጀመሪያ ላይ በ 1860 ዓ.ም እጃቸውን ለጠላት ጦር ከመስጠት ይልቅ ሞትን በመምረጥ እስከዛሬ ትውልድ የሚኮራበትንና የራሳቸውንም አትንኩኝ ባይነት ጸባይ በራሳቸው የሽጉጥ ጥይት ባደባባይ አሳይተው አለፉ ።
..መቅደላ አፋፉ ላይ ..ጩኸት በረከተ ፡
..የሴቱን አናውቅም..ወንድ አንድ ሰው ሞተ ።
ገደልን እንዳይሉ ሞተው..አገኟቸው ፡
ማረክን እንዳይሉ..ሰው የለ በጃቸው ፡
ምን አሉ እንግሊዞች..ሲገቡ አገራቸው ?

ዳግማዊ ምኒልክ

ዳግማዊ ቴዎድሮስ
የግእዝ ፊደላት
(በሕሊና በለጠ)
‘ፈደለ’ ማለት ‘ጻፈ’ ወይም ‘ፈጠረ’ ማለት ነው፡፡ ፊደል የሚለው ቃል ከዚህ የግእዝ ግስ የወጣ ነው፡፡ ‘ግእዝ’ የሚለውን ቃል ደግሞ ብዙዎች ‘ ገአዘ’ ከሚለውና ‘ነፃ አወጣ’ ወይም ‘ነፃ ወጣ’ የሚል ትርጉም ካለው ግስ ጋር ያያይዙታል፡፡ የግእዝ ፊደላት የቃላቱ ትርጉም አመጣጥ እንደተገለፀው ቢሆንም ‘የግእዝ ፊደላት’ የሚለውን ቃል ግን ለመረዳት በራሱ ግልጽ ነው፡፡
የግእዝ ፊደላት በዓለም ላይ ጥንታዊ ከሆኑት ፊደላት ውስጥ የሚመደብ ነው፡፡ እንደውም የሃይማኖት አባቶች የመጀመሪያው የዓለምን ቋንቋ ግእዝ አድርገው የመጀመሪያውም ፊደል የግእዝ ፊደል እንደሆነ ይገልፃሉ፡፡ ይህንንም ሲያረጋግጡ ጥንታዊው (የመጀመሪያው) መጽሐፍ ከክርስቶስ ልደት 4000 ዓመት በፊት የተጻፈው መጽሐፈ ሄኖክ መሆኑን ገልጸው፣ ይህ የአዳም ሰባተኛ ትውልድ የሆነው ሄኖክ ደግሞ ኢትዮጵያዊ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ በ1948 ዓ.ም በሙት ባሕር አካባቢ በኩምራን ደሴት የተገኙት የጽሑፍ ጥቅሎች (Qumran Scrolls or Dead Sea Scrolls) እስኪገኙ ድረስ መጽሐፈ ሄኖክ በጥንታዊነት የሚገኘው በግሪክና በግእዝ ቋንቋ ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ ግሪካውያን የእነርሱ ትክክለኛውና የመጀመሪያው እንደሆነ ይከራከሩ ነበር፡፡ ሆኖም ከኩምራን ጥቅሎች አንዱ የዚህ መጽሐፍ የዕብራይስጡ ኮፒ በመሆኑና ይህ መጽሐፍ ከግሪኩ ይልቅ ለግእዙ የቀረበ በመሆኑ የግእዙ ጥንታዊ ለመሆኑ ምስክር ሆነ፡፡ የኩምራን ጥቅሎች ጥናቶች እንደሚጠቁሙት የተቀበሩት ፈሪሳውያን፣ ሰዱቃውያን፣ ሳዶቃውያን፣ ዚሎታውያንና ሌሎችም የአይሁድ ክፍሎች ከሚኖሩበት ርቀው በቦታው ይኖሩ በነበሩት ኤሴያውያን/ኤሴናውያን (Essenes) ነው፡፡ ጥጦስ በ70 ዓ.ም. ኢየሩሳሌምን ሲያጠፋ ወደ ኤሴናውያንም ሊያጠቃቸው ሄዶ ነበርና መምጣቱን የሰሙትና በትኅርምት የሚኖሩት ኤሴናውያን መጽሐፎቻቸውን በማሰሮ እያደረጉ ቀበሯቸው፡፡ በ1948 የተገኙትም እነዚሁ ናቸው፡፡ ይህም ቢሆን ግን በተናጠል የግእዝ ፊደልን ጥንታዊነት ሳይሆን በጥቅሉ የሴማውያን ቋንቋዎች ፊደላትን ጥንታዊነት ነው የሚያሳየው፡፡ (ሴማውያን ቋንቋዎች ከሚባሉት አረቢክ፣ አካድ፣ ከነዐናይት ፡ዕብራይስጥ፣ ፍንቄ ሲሆኑ ከግእዝ ጋር የኢትዮጵያ ሴማውያን ቋንቋዎች የሚባሉት ደግሞ ሳባ፣ ግእዝ፣ ትግረ፣ ትግርኛ፣ አማርኛ፣ ጉራጊኛ፣ አርጎብኛ…ወዘተ ናቸው፡፡)
ሌላኛው ጥቆማ ደግሞ የሴማውያን ፊደላት አንድ ወቅት ላይ ተመሳሳይ እንደነበሩና በየፊደላቱ በተደረጉ ለውጦች እየተለያዩ እንደመጡ ያስረዳል፡፡
የዚህ ጽሑፍ ትኩረት የግእዝ ፊደላት ላይ በመሆኑ የእይታችንን አቅጣጫ ወደዚህ ሀገራዊ ሀብት እንመልሰው፡፡ የግእዝ ፊደላት የጽሑፍ አገልግሎት ላይ የዋሉት በዚህ ጊዜ ነው ለማለት ቢከብድም ጥንታዊ ጽሑፎችን በመመርመር ከብዙ ዘመናት በፊት እንደሆነ ግን መገመት አይከብድም፡፡ ለዚህ ደግሞ ለቋንቋው ክብር ሰጥተው (ምናልባትም ለግል ጥቅማቸው ብለው) በሀገራችን ሳይጀመር የBA እና የMA ደረጃ አቋቁመው የሚያስተምሩት የውጪ ዜጎች በተለይም ጀርመናውያን ምስክር ናቸው፡፡
አሁን የምንጠቀምባቸው የግእዝ ፊደላት በአብዛኛው ቅርፃቸውን ያገኙት ከ335-350 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜ ነው፡፡ የግእዝ ፊደላት በቁጥር 26 ናቸው፡፡ እነዚህም፡-
ሀ ረ ኀ ዐ መ ፐ*
ለ ሰ ነ ዘ ጰ*
ሐ ቀ አ የ ጸ
መ በ ከ ደ ፀ
ሠ ተ ወ ገ ፈ
*ጰ እና ፐ ድምጻቸው ከግሪክ ፊደላት እንደተወሰደ ይታመናል፡፡
ከነዚህ ሌላ የምናውቃቸው ፊደላት የግእዝ ፊደላት አይደሉም፡፡ አንዳንድ ምሁራን ሰባቱን ማለትም ‘ሸ’፣ ‘ቸ’፣‘ኘ’፣ ‘ዠ’ ፣ ‘ጀ’፣ ‘ጨ’፣ እና ‘ኸ’ ን የአማርኛ ፊደላት ፤ ‘ሏ’ ‘ሟ’ ‘ሷ’ ‘ሯ’….የመሳሰሉትን ደግሞ ዲቃላ/የተዳቀሉ ፊደላት ሲሉ ሌሎች ደግሞ ሁሉም ዲቃላ ፊደላት ናቸው ይላሉ፡፡ የላይኞቹ የ ‘አማርኛ ፊደላት’ ብለው የጠሩበት ምክንያት በአማርኛ ቋንቋ ውስጥ በጊዜ ሂደት የተፈጠሩ ድምፆችን ለመወከል የተፈጠሩ በመሆናቸው ነው፡፡ የዲቃላ (የተዳቀሉ) ፊደላትን አመጣጥ እንደሚከተለው እንመልከት፡፡
- ሏ፣ ሟ….እነዚህ ፊደላትን ለማሳጠር የተፈጠሩ ናቸው፡፡
ለምሳሌ፡- ‘ላሟ’ ለማለት ‘ላምዋ’ ብሎ ሦስት ፊደላትን ከመጠቀም ‘ላሟ’ በማለት
ለማሳጠር ነው፡፡
- የሰባቱ ፊደላት አማጣጥ ግን ከዚህ ይለያል፡፡ ድምጻቸውንም ቅርፃቸውንም ከግእዝ ቢወስዱም አጠቃቀማቸው ይለያያል፡፡
ሸ ድምጹን ከ ‘ሠ’ ቅርፁን ከ ‘ሰ’
ቸ ድምጹን ከ ‘ከ’ ቅርፁን ከ‘ተ’
ኘ ድምጹን ከ ‘ነ’ ቅርፁን ከ ‘ነ’
ዠ ድምጹን ከ ‘ዘ’ ቅርፁን ከ ‘ዘ’
ጀ ድምጹን ከ ‘ገ’ ቅርፁን ከ ‘ደ’
ጨ ድምጹን ከ ‘ቀ’ ቅርፁን ከ ‘ጠ’
ኸ ድምጹን ከ ‘ሀ’ ቅርፁን ከ ‘’ከ
(ከነዚህ ውጭም ከ‘አ’ ድምጽና ቅርጽ የተፈጠረ ‘ኧ’ የሚባለውን ፊደል ከነዚህ ጋር ይቆጥሩታል)
እነዚህ ፊደላት ድምጻቸው በግእዝ ውስጥ የለም፡፡ በአማርኛው ውስጥ ግን አለ፡፡ አሁንም በምሳሌ ስናይ ‘ነገሠ’ ብለን ‘ንጉሥ’ ፣ ‘ንግሥ’ ፣‘ነጋሽ’ እንላለን፡፡ ‘ነጋሽ’ የሚለውን ቃል በግእዙ ‘ነጋሢ’ ይለዋል፡፡ አማርኛው አዲስ ድምጽ ‘ሸ’ ን ስለፈጠረ ፊደሉን ተጠቀመው፡፡ ሆኖም አንዳንድ ምሁራን በጥንታዊው ግእዝ ‘ሠ’ የሚለው ፊደል ‘ሸ’ የሚል ድምጽንም ጭምር ይወክል እንደነበር ይገልጻሉ፡፡
የሌሎቹም አመጣጥ ተመሳሳይ ይዘት ቢኖረውም ‘ኸ’ እና ‘ኧ’ ግን ካለ ምክንያት የተፈጠሩ እንደሆኑ ብዙዎቹ ይጠቁማሉ፡፡ ምክንያቱም ‘ኸ’ እራሱ ድምጹ የ ‘ሀ’ ነውና፡፡(የ ‘ሀ’ ትክክለኛ ድምጽ አሁን ‘ኸ’ ን የምንጠራበት ነው፡፡ ነገር ግን በተለምዶና በጊዜ ሂደት ‘ሀ’ን ‘ሃ’ ብለን እንጠራለን፡፡ ‘ለ’ን ‘ለ’ ብለን እንጂ ራብዑን በመውሰድ ‘ላ’ ብለን አንጠራውም፡፡ ሌሎቹም ተናባቢ (consonant) ፊደላትን ግእዛቸውን በራብዕ አንጠራም፡፡ ነገር ግን ‘ሀ’ ን እና ‘አ’ ን ድምጻቸውን ከ ‘ሃ’ እና ‘ኣ’ ጋር (ከራብዓቸው ጋር) አንድ በማድረጋችን ‘ኸ’ እና ‘ኧ’ የተባሉ ፊደላትን መፍጠር አስፈለገን፡፡
ቀዳማይና ደሐራይ የግእዝ ፊደላት
ቀዳማይ የግእዝ ፊደላት የሚባሉት 26ቱ የመጀመሪያ የግእዝ ፊደላት ሲሆኑ ደሐራይ የግእዝ ፊደላት የሚባሉት ደግሞ በቀዳማይ የግእዝ ፊደላት ላይ የ ‘—’ እና የ ‘o’ ምልክትን በመጨመር የተፈጠሩት ከካዕብ እስከ ሳብዕ ያሉት ፊደላት ናቸው፡፡ ይህንን ለመረዳት የሚከተለውን ሠንጠረዥ እንመልከት፡፡
ቀዳማይ ግእዝ ደሐራይ ግእዝ
ሀ ሀ ሁ ሂ ሃ ሄ ህ ሆ
ለ ለ ሉ ሊ ላ ሌ ል ሎ
ሐ ሐ ሑ ሒ ሓ ሔ ሕ ሖ
መ መ ሙ ሚ ማ ሜ ም ሞ
ሠ ሠ ሡ ሢ ሣ ሤ ሥ ሦ
ረ ረ ሩ ሪ ራ ሬ ር ሮ
.
.
ፐ ፐ ፑ ፒ ፓ ፔ ፕ ፖ
ደሐራይ የግእዝ ፊደላት በቀዳማይ የግእዝ ፊደላት ላይ የተጨመሩት አባ ፍሬምናጦስ (Frementus) ወይም አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን በተባሉ ከሲሪያ (ግሪክ) በመጡ አባት ነው፡፡ እኚህ አባት ሜራፒየስ (Merapius) በተባለ ግሪካዊ ፈላስፋ እየተመሩ ኤዴሲየስ (aedisius) ከተባለ ወንድማቸው ጋር በልጅነታቸው በንጉሥ አልአሜዳ ቀዳማዊ (የኢዛናና ሳይዛና ወይም የአብርሃ እና አፅብሃ አባት) ዘመን ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ናቸው፡፡ ሜራፒየስ እነ ፍሬምናጦስን ሊወስድ ያሰበው በቀይ ባሕር በኩል ወደ ሕንድ ነበር፡፡ መንገድ ስተው በኢትዮጵያ ግዛት ሲገኙ ከሮማውያን ጋር ጥሩ ግንኙነት ያልነበራቸው የአልአሜዳ ጦረኞች ጠላት የመጣ መስሏቸው ጥቃት ከፍተው ሜራፒየስን ገድለው ሁለቱን ልጆች ወደ ንጉሡ ወሠዱ፡፡ ንጉሡም የግሪክ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑትን እነዚህን ልጆች ተንከባክቦ ከራሡ ልጆች ኢዛናና ሳይዛና ጋር በጊዜው ወደ ነበረው ታላቅ የብሉይ ኪዳን ት/ቤት ወደ ‘ቤተ ቀጢን’ አስገብቷቸው ለ7 ዓመታት እንበረም በተባለው መምህር ሥር ተምረው ግእዝን በሚገባ አወቁ፡፡
ከዚህም በኋላ አባ ፍሬምናጦስ ቋንቋውን ይበልጥ ለማሳደግ በፊደላቱ ላይ ‘—’ እና የ ‘o’ ምልክቶችን በመጨመር ደሐራይ ግእዝን አስተዋወቁ፡፡ ይህንንም ሊቃውንት ከ335-350 በሚገባ አጥንተው ከ350 በኋላ በይፋ ጥቅም ላይ ዋለ፡፡ እዚህ ላይ ምናልባት ከዛ በፊት የነበሩት መጻሕፍት እንዴት ተጻፉ? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡ በጊዜው የፊደላቱ ቅርጽ እንጂ ድምጻቸው ነበር፡፡ ሁሉም የነበሩት ድምጾች ግን በጽሑፍ የሚወከሉት በቀዳማይ ግእዝ ነበር፡፡ ለምሳሌ ‘ሀ’ የሚወክለው ድምጽ ከግእዝ - ሳብዕ ያሉትን ነው፡፡
ይህም ማለት ‘ሀ’ ‘ሁ’ ‘ሂ’ ‘ሃ’ ‘ሄ’ ‘ህ’ ‘ሆ’ ለማለት በጽሑፍ የሚወከሉት በ ‘ሀ’ ነው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ እንደንባቡ ሂደት (contextually) ድምጾች ይለያሉ እንጂ ቅርጹ አንድ ነው፡፡
ከዚህ የተለየ አመለካከት ያላቸው ምሁራን ደግሞ ለሰባቱም ድምጽ (ከግእዝ - ሳብዕ ላሉት) የተለዩ አናባቢዎች ነበሩ ይላሉ፡፡ እነዚህም የሚከተሉት ናቸው፡፡
- አ፣ ሀ ራብዕንና ሳድስ ድምጽን ለመግለፅ (ራብዕና ሳድስ ለማድረግ)
ምሳሌ፡- በ + አ (በአ) = ባ፣ ብ
በ+ሀ (በሀ) = ባ፣ብ
- ወ ካዕብንና ሳብዕ ድምጽን ለመግለጽ (ካዕብና ሳብዕ ለማድረግ)
ምሳሌ፡- በ + ወ (በወ)= ቡ፣ቦ
- የ ሐምስንና ሣልስን ለመግለፅ (ሐምስና ሣልስ ለማድረግ)
ምሳሌ፡- በ + የ (በየ) = ቤ ፣ ቢ
አሁን በአናባቢነት ‘አ’ የሚሠጠውን አገልግሎት ይሠጡ ነበር ማለት ነው፡፡
ይቆየን፡፡ በቀጣይ ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ሞክሼ ፊደላት የምንለው ይኖራል፡፡
© ዘሕሊና (ይህ ጽሑፍ ናፍቆት ኢትዮጵያ መጽሔት ላይ የወጣ ነው፡፡)


ሞክሼ ፊደላት ሀ፣ ሐ፣ ኀ፤ ሠ፣ሰ፤ አ፣ዐ እና ጸ፣ፀ ናቸው፡፡ የእነዚህን ፊደላት ጥቅም ብዙዎቹ አይረዱም፡፡ ልዩነትም ያላቸው እንደሆኑ ይዘነጋሉ፡፡ በአማርኛው ላይ ብዙዎቹ ልዩነቱን ቢያጠፉትም በግእዙ ግን አሁንም ልዩነት አላቸው፡፡ በጥንታዊ አጠቃቀማቸው በድምጽም ጭምር ልዩነት አላቸው፡፡ ‘ሀ’ ላልቶ የሚነበብ፣ ‘ሐ’ ጠብቆ የሚነበብ፣ ‘ኀ’ በጉሮሮ የሚነበብ፣ ‘ሠ’ የ ‘ሸ’ን በመሰለ ድምጽ የሚነበብ፣ ‘ሰ’ በጥርስ የሚነበብ፣ ‘አ’ ላልቶ የሚነበብ፣ ‘ዐ’ ጠብቆ ፣ ‘ፀ’ የ‘ጠ’ን በመሰለ ድምጽ የሚነበብ (ምሳሌ፡- ፀሐይ- ጠሐይ፣ ፀበል - ጠበል)፣ ‘ጸ’ አሁን እንደሚነበበው የሚነበብ ሆነው በተለየ ድምጻቸው ይታወቁ ነበር፡፡
ሞክሼ ፊደላትን በዘፈቀደ መጠቀም የትርጉም ስህተት ሊያመጣ ይችላል፡፡ ያስነቅፋልም፡፡ ይህንንም በመንቀፍ ሊቁ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ‘መዝገበ-ፊደል’ በተባለ መጽሐፋቸው የሚከተለውን ገጥመዋል፡፡
“እንዳገኙ መጣፍ በድፍረት በመላ
የቋንቋ ደረመን የመጽሐፍ ቢስ ገላ
ንባብ የሚያሳክክ ምሥጢር የሚቆምጥ
መልክዐ ትርጓሜ የሚለዋውጥ”
የሞክሼ ፊደላትን የትርጉም ለውጥ በሚከተሉት ቃላት ይበልጥ መረዳት ይቻላል፡፡
ድህነት- ማጣት፣ መቸገር
ድኅነት- መዳን፣ መፈወስ
ንስሐ- መፀፀት፣ ማዘን
ንስኃ- ክርፋት፣ ግማት
ሐበ - ኮሶ
ኀበ - ወደ
ቅንአት - ክፋት (ቅናት)
ቅንዓት - ቅንነት፣ መልካምነት
ሰአለ - አሳለ፣ ኡሁ ኡሁ አለ
ሰዐለ - ፣ ለመነ
ሠዐለ- ሥዕል ሣለ
ገዐዘ - ጉዞ አደረገ፣ አጓጓዘ
ገአዘ - ነፃ ሆነ ( ግእዝ ከዚህ ነው የወጣው)
የግእዝ ፊደላት በአጠቃቀም ላይ ጥንቃቄን የሚሹ የሀገር ሀብት ናቸው፡፡ ምንም እንኳን በአሁኑ ወቅት የሚደረግላቸው ትኩረት ቢቀንስም (እንደውም አንዳንዶች አይጠቅሙም ይቀነሱ እያሉ ቢጮሁም) ማንኛውም ኢትዮጵያዊ እንደ አክሱምና ላሊበላ ሊንከባከባቸው የሚገባ ታላላቅ ሀብቶች ናቸው፡፡ በዚህ ጽሑፍ የተዳሰሱት ከፊል ባህሪያቸው ነው፡፡ መጻሕፍትና የቋንቋው ሊቃውንት ደግሞ በስፋትና በምልዐት ይዳስስታልና መረዳት ተገቢ ነው፡፡ ይቆየን፡፡
© ዘሕሊና

ethiopianism
Ethiopianism Prevails!
.
--- On this date on June 28, 1778, the British loyalists' Ethiopian Regiment prevails in the Battle of Monmouth.
.
The Battle of Monmouth was an American Revolutionary War battle fought on June 28, 1778 in Monmouth County, New Jersey. The Continental Army under General George Washington attacked the rear of the British Army column commanded by Lieutenant General Sir Henry Clinton as they left Monmouth Court House (modern Freehold Borough). It is known as the Battle of Monmouth Courthouse.
.
The battle was considered inconclusive; with both sides claiming victory.
.
So what is the Ethiopian Regiment?
.
In November 1775 Lord Dunmore, royal governor of Virginia, issued a proclamation promising freedom for any enslaved black in Virginia who joined the British army. Within a month, nearly three hundred slaves had joined what would be known as “Lord Dunmore’s Ethiopian Regiment.” Later, thousands of slaves fled plantations for British promises of emancipation. At the end of the war, the British kept their word, to some at least, and evacuated as many as fourteen thousand “Black Loyalists” to Nova Scotia, Jamaica, and England.
.
This was the beginning of early Ethiopianism.
የፓን አፍሪካኒዝም ራዕይ ጭንገፋ!
Geez Bet | Tuesday, June 11, 2013
ክፍል አንድ
W. E. B. Du Bois
ምዕራባዊያን አፍሪካን በበጎ ነገር አያነሷትም፡፡ የቀደምት ስልጣኔዋንም አምነውአይቀበሉትም፡፡ አፍሪካዊያኑም ቢሆኑ ስለማንነታቸውና ስለታሪካቸው ያላቸውእውቀት ፈረንጆች አፍሪካን ከሚያውቋት እጅግ ያነሰ ነው፡፡ ይህ ነገር ደግሞ አሁንአፍሪካ ካለባት ችግር በተጨማሪ ነገሩ የገለባ እሳት ሆኖባታል፡፡ አፍሪካ ባንድ ወቅትኃያል ሃገር ነበረች፡፡ ነገር ግን ያ ስልጣኔዋ ተሸመደመደና ወደ ጨለማው ዘመንገባች፡፡ የስልጣኔ መሽመድመድ በታሪክ አፍሪካ ብቻ ሳትሆን አውሮፓንምደቁሷታል፡፡ ምስጋና ይግባቸውና የሰሜን አፍሪካ ሙሮች (Moors)፣ በሰባተኛውመቶ ክፍለ ዘመን ወደ አውሮፓ ተሻግረው፣ ጨለማ ውስጥ የምትገኘውን አህጉርአቀኑ፡፡ ከዚያ በኋላ አውሮፓ ሰለጠነችና አፍሪካን ተቀራመተች፡፡ ይህንን የአፍሪካቅርምጥ የአብርሆት (Enlightenment) ዘመን ልሂቃን የሚባሉት ጭምርደግፈውታል፡፡ የአፍሪካ ህዝብ ሰብአዊ መብቱ ተገፎ ሰው ያለመሆኑ ታወጀ እናለባርነት ተጋዘ፣ ተገረፈ፣ ተሰቃየ፣ ተሰቀለ፣ ታደነ፣ ታነቀ፣ ተገደለ፣ ንብረቱ ተዘረፈ፣የአገር ባለቤትነቱን ተነጠቀ፣ ሳይፈልግ የወራሪዎቹን ባህል፣ ትምህርት፣ ኃይማኖትእንዲቀበል ተገደደ ………. ምን ያልሆነው አለ? እናም ይሄንን ግፍ አሽቀንጥረውለመጣል ሃሳብ ያላቸው ጥቁር ልሂቃን በየቦታው ማኮብኮብ ጀመሩ፡፡ በመጀመሪያሰለ እነዚህን ንቅናቄዎች እና ኢትዮጵያኒዝም ትንሽ እንመለከታለን፡፡ ከዚያም ወደ ፓንአፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ እና ዓላማ፣ በመጨረሻም የፓን አፍሪካኒዝም ራዕይ እንዴት በአፍሪካዊያን አምባገነን መሪዎች እንደጨነገፈ
በሶስት ተከታታይ ክፍሎች እንመለከታለን፡፡ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ በደቡብ አፍሪካ በነጮች ይጨቆኑ የነበሩት እና በእምነቱ ውስጥምንም ቦታ ያልተሰጣቸው ጥቁሮች ከአንግሊካን እና ሜቶዲስት ደብር (Church) ተገንጥለው በውጣት ኢትዮጵያዊ ደብር (Ethiopian Church) መሰረቱ፡፡ በሰበካቸው ውስጥም “አፍሪካ ለአፍሪካዊያን” የሚል ነበረው፡፡ ይህም እንቅስቃሴ ኢትዮጵያኒዝም የሚባል አስተሳሰብእንዲጀመር ረድቷል፡፡ የዌስልያን ሚኒስተር ማንጌና ሞኮን (Mangena Mokone) ኢትዮጵያኒዝም የሚለውን ቃል ለመጀመሪያ ጊዜእንደተጠቀመ ብዙዎች ያምናሉ፡፡ የኢትዮጵያኒዝም እሳቤ ወደ ምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ናይጄሪያ፣ ጋና፣ ካሜሮን፣ ሮዶዥያና ሌሎችምአንሰራርቶ ነበር፡፡ ከአፍሪካ ውጭ ደግሞ ይህ እሳቤ በካረቢያን እና ሰሜን አሜሪካ እንደሰደድ እሳት ተስፋፍቶ ነበር፡፡ አንዳንድ ጸሐፍትኢትዮጵያኒዝም የሚለውን ጽንሰ ሃሳብ ለማብራራት እንደሚያስቸግር ቢያትቱም ዋና ጽንሰ ሃሳቡ ኃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ፍልስፍናን ያካተተነው፡፡ በሃይማኖታዊው ካየነው ጥቁሮች በነጮች የበላይነት የሚመራውን ደብር ትተን፣ የራሳችንን ከማንነታችን ጋር ትስስር ያላትን አፍሪካዊት(ኢትዮጵያዊት) ደብር እንመስርት የሚል ነው፡፡ ፖለቲካዊው ደግሞ በአለም የሚገኙ ጥቁሮች የነጮችን የፈላጭ ቆራጭ ገዥነትን ለመገርሰስኢትዮጵያን እንደ አርዓያ በመውሰድ የሚደረግ እንቅስቃሴ ነበር፡፡ በተለይ የአድዋ ድል፣ የኢትዮጵያ ቀደምትነት ስልጣኔ እና በመጽሐፍ ቅዱስስሟ መጠቀሱ ለኢትዮጵያኒዝም እሳቤ እና ለፓን አፍሪካኒዝም ፍልስፍና ጉልህ አስተዋጽኦ ነበራቸው፡
ፓን አፍሪካኒዝም፡- በመላው ዓለም የሚገኙትን አፍሪካዊያን አንድነት (ሶሊዳሪቲ) የሚቀሰቅስ ርዕዮተዓለም ነው፡፡ ፓን አፍሪካኒዝምመነሻውን ከጥንት የአፍሪካዊያን ስልጣኔ ጋር ያይዛል፡፡ ጥቁሮች ከጥንት ጀምረው እስካሁን ይዘውት የመጡትንና ጥንት የነበሩትን ታሪካዊ፣ባሕላዊ፣ ኪነ-ጥበባዊ፣ መንፈሳዊ፣ ሳይንሳዊና ፍልስፍናዊ እሴቶችን በሕዝብ ዘንድ ማስረጽ አንደኛው ዓላማቸው ነው፡፡ የፓን አፍሪካኒዝምንቅናቄዎች ቀደም ሲል የተጀመሩ ቢሆንም ዘመናዊው የፓን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ የተጀመረው ግን በ1887 በትሪኒዳዱ የህግ ምሁር ሄነሪሲልቬስተር ዊሊያምስ “አፍሪካን አሶሴሽን” በሚል ስያሜ ነበር የተቋቋመው፡፡ እዚህ ላይ (ስለ መጀመሪያው የፓን አፍሪካን መስራች) በታሪክሰዎች ዘንድ ልዩነት አለ፡፡ አንዳንድ የታሪክ መጽሐፍት ላይ (ጸሐፊዎች) የመጀመሪያው የፓን አፍሪካን መስራች (ጽንሰ ሃሳብ አመንጭ)ላይቤሪያዊው መምህር፣ ጸሐፊ፣ ዲፕሎማትና ፖለቲከኛ ኤድዋርድ ዊልሞት ብላይደን ነው ሲሉ ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ ሄነሪሲልቬስተር ዊሊያምስ ነው ይላሉ፡፡ በአፍሪካም ይህን የፓን አፍሪካኒዝም አስተሳሰብ ካስፋፉትና ድርጅታዊ መሰረት ከሰጡት አንዱ የማላዊውዜጋ የነበረው የባብቲስት ሚሲዮናዊ ዮሴፍ ቡዝ ነበር፡፡
የፓን አፍሪካን የመጀመሪያውን ጉባኤም በሐምሌ ወር በ1900 ለንደን ላይ በሄነሪ ሲልቬስተር ዊሊያምስ አስተባባሪነት ከአፍሪካ፣ከዩናትድ ስቴትስ፣ ከካረቢያን እና ከአውሮፓ ሃገራት በተውጣጡ 32 ተወካዮች ተካሄደ፡፡ በዚህ ስብሰባ ላይ ከአፍሪካ የጋና (ጎልድ ኮሰት)፣ሴራሊዮን፣ ላይቤሪያ እና ኢትዮጵያ ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡ የኢትዮጵያው ንጉሰ ነገሰት ዳግማዊ ምኒሊክ የሃይቲውን ቤኒቶ ሲልቪያን ወክለውልከው ነበር፡፡ በዚሁ ስብሰባ ፓን አፍሪካን አሶሴሽን የሚል ድርጅትም አቋቋሙ፡፡ ከተሰብሳቢዎቹ አንዱ ታዋቂው አፍሮ አሜሪካዊው ምሁርዱቦይስ (ዱ ቧ) ተገኝቷል፡፡ ዱቦይስ ከሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ በማህበራዊ ጥናት ዶክትሬቱን ያገኜ ሲሆን በአሜሪካም በጥቁሮች ታሪክየመጀመሪያ ጥቁር ሰው ነው ደኮትሬት በማግኜት፡፡ በአትላንታ ዩኒቨርስቲም የታሪክ፣ ማህበራዊ ሳይንስ (ሶሲዎሎጅ) እና ምጣኔ ሃብት ፕሮፌሰርነበር፡፡ ዱቦይስ የአሜሪካን ጥቁሮች በማንቃት በኩል ያደረገው ትግል እጅግ ከፍተኛ ነበር፡፡ ብዙ መጽሐፍትን ጽፏል፡፡ ታላቅ ስራው(Magnum Opus) ተደርጎ የሚወሰደው Black reconstruction in America ሲሆን ሌላው ተወዳጅ ስራው ደግሞ The Souls of Black Folk ነው፡፡ የ National Association for the Advancement of Colored People (NAACP) መስራች ሲሆን የዚሁድርጅት ልሳን ለሆነው The Crisis ዋና ኤዲተር ነበር፡፡ ፓን አፍሪካን ከመሰረቱት መካከል ግንባር ቀደሙ ነው፡፡
በ1913 የኢትዮጵያ ኮኮብ (The star of Ethiopia) የሚል ተውኔት ደርሶ ለህዝብ እንዲታይ አድርጓል፡፡ በተጨማሪም ኢትዮጵያን“የሰው ልጆች ሁሉ እናት (መፈጠሪያ)” ብሎ ይጠራት እና ያስተምር ነበር፡፡ የዓለም ስልጣኔ ሁሉ ከናይል ሸለቆ (ግብጽና ኢትዮጵያ)እንደተጀመረም ያቀነቅን ነበር፡፡ የፓን አፍሪካን እንቅስቃሴም ለግማሽ ምዕተ ዓመት ያህል መርቷል፡፡ ከለንደኑ ስብሰባ በኋላ አራት የፓንአፍሪካን ስብሰባዎች (በ1919 ፓሪስ፣ በ1921 ሎንዶንና ብራሰልስ፣ በ1923 ሎንዶንና ሊዝበን፣ በ1927 ኒው ዮርክ) የተዘጋጁት በዚህ ምሁርመሪነት ነበር፡፡ ያለ ዱቦይስ አሰተዋጽኦ ፓን አፍሪካኒዝም ወይም በተዘዋዋሪ የአሁኑ አፍሪካ ሕብረት ምን አልባትም ላይኖር ይችላል፡፡የሚገርመው የኢትዮጵያና የአፍሪካዋያን ብዙ መገናኛ ብዙሓን ስለዚህ ጎምቱ የጥቁር ምሁርና የፓን አፍሪካን አባት ሚና ሲናገሩ፣ ሲጽፉ ወይምሲዘክሩ አይታይም፡፡ ዱቦይስ እና ኩዋሜ ንኩርማህ በፓን አፍሪካን ምስረታ ጉዳይ የሚነጻጸሩ አይደሉም፡፡ ርቀታቸው የሰማይና የምድር ነውብሎ የዚህ ጦማር ጸሀፊ ያምናል፡፡ ንኩርማህ፣ጁሊየስ ኒሬሬ፣ ጆሞ ኬንያታ ወዘተ. በ1945ቱ የማንቸስተሩ ፓን አፍሪካን ስብሰባ ላይ የተገኙየርዕዮቱ ልጆቹ ናቸው፡፡ በርግጥ ከማንቸስተሩ የፓን አፍሪካን ስብሰባ በኋላ መሪነቱ በአፍሪካዊያን እጅ ገብቷል፡፡ ዱቦይስ በሶሻሊዝም ፍቅርጋር እስከ ሕይወቱ ፍጻሜ የወደቀ ነበር፡፡ የሶሻሊዝም ፍልስፍናው እንዳልገባው ቢናገሩም እሱ ግን ካፒታሊዝም የሰው ልጆች ዘረኛ እንዲሆኑአድርጓል ይላል፡፡ እንም ዘረኝነትን ለማስቀረት ሶሻሊዝም ፍቱን መፍትሔ ነው ብሎ ያምናል፡፡ በዚህ ምክንያትም አሜሪካ አንቅራ ነበርየምትጠላው፡፡ በ1957 ጋና ነጻነቷን ስታገኝ የክብር እንግዳ አድርጋ ጠራችው፡፡ ነገር ግን አሜሪካ ጋና አትሄዳትም አለችና ፓስፖርቱንቀማችው፡፡ ነገር ግን በ1960 ፓስፖርቱን ስላገኜ ወደ ጋና ሄደ፡፡ እናም ለጋና የሪፓብሊክ ምስረታ በዓል ላይ ተገኘ፡፡ በዚሁ ሰዓትም ከንኩርማህጋር ኢንሳክሎፒዲያ አፍሪካን ለማዘጋጀት ተስማሙ፡፡ በጀቱም በጋናዊያን መንግስት ነበር የሚሸፈነው፡፡ እናም በ1961 ከአሜሪካ ሚስቱን ይዞበመምጣት ጋና ከተመ፡፡ የኢንሳክሎፒዲያውን ስራም ጀመረ፡፡ በ1963 አሜሪካ ፓስፖርቱን ለማደስ ፈቃደኛ ስላልሆነች የክብር እንግዳ ሆኖጋና ተቀመጠ፡፡ ነገር በዚያው ዓመት በነሃሴ ወር 1963 አክራ ውስጥ ሕይወቱ አለፈች፡፡ የተቀበረበት ቦታም የዱቦይስ መታሰቢያ ማዕከልተብሎ ተሰይሟል፡፡
ሌላው ፓን አፍሪካን ሲነሳ ከመስራቾቹ ግንባር ቀደም የሆነውና አነጋጋሪው ማርቆስ ጋርቬይን እናገኛለን፡፡ አንዳንዶች ጋርቬይንየጥቁሮች ሙሴ እያሉ ይጠሩታል፡፡ ሙሴ እስራኤላዊያንን ከግብጽ ባርነት አላቆ ወደ ተስፋይቱ ምድር በመውሰድ ነጻ እንዳወጣቸው ሁሉ፣ጋርቬይም ጥቁሮቹን ከጭቆናና ከባርነት አላቆ ወደ ተስፋይቱ ምድር አፍሪካ ለመውሰድ እና ጥቁሮችን አንድ ለማድረግ (ለማስተሳሰር) ያደረገውተጋድሎ ግሩም ነበር፡፡ ፍልስፍናውም ጋርቬይዝም ይባል ነበር፡፡ ጋርቬይ ዓለም አቀፍ የጥቁሮች መሻሻል ማህበር፣ አፍሪካን ኮሚኒቲስ ሊግ፣ብላክ ስታር ላይን ኮርፖሬሽን የሚባሉ ድርጅቶችን አቋቁሟል፡፡ ጋርቬይ የጥቁር አሜሪካዊያን ድርጅት በሆነው ኔሽን ኦቭ-ኢዝላም ያለው ክብርበጣም የገዘፈ እና እንደነብይም የሚመለከቱት ነው፡፡ በራስ ተፈሪያን እምነትም ከንጉስ ኃይለሥላሴ ቀጥሎ እንደ አምላክ (ነብይ) የሚቆጠርሰው ነው፡፡ ነገር ግን እዚህ ላይ አንድ ማንሳት ያለብን ተቃራኒ ጉዳይ አለ፡፡ ጣሊያን ኢትዮጵያን ስትወር፣ ንጉስ ኃይለ ስላሴ ወደ እንግሊዝየመሄዳቸውን ጉዳይ ጋርቬይ እንዲህ በቀላሉ አላለፈውም፡፡ ንጉስ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን በአደባባይ ለስጋቸው ሳስተው፣ ወገናቸውን ጦርነትውስጥ ማግደው አውሮፓ እጃቸውን ሊሰጡ መጡ ብሎ ከመሳለቁም በላይ ቦቅቧቃና ፈሪ ብሎ ሰደባቸው፡፡ ስለዚህ ጉዳይ በዝርዝር ሌላ ጊዜይዘን እንመጣለን፡፡
ጋርቬይ ነጮችን ስግብግቦች፣ ራስ ወዳዶች እና ፍቅር የለሾች ሲል በተለያየ ጊዜ ይገልጻቸው ነበር፡፡ ፍቅር፣ መተሳሰብና ለጋስነት ምንጩአፍሪካ ግብጽና ኢትዮጵያ እንደሆነ ይሰብክ ነበር፡፡ በአሜሪካም በየጎዳነው እናንተ የሃያላን ልጆች ሆይ አትነሱም ወይ እያለ መሳጭ ንግግርያደርግ ነበር፡፡ የሚገርመው ይህ ጥቁሮችን በመላው ዓለም ያንቀሳቀሰና ያነቃው ሰው (ጋርቬይ) ከዱቦይስ ጋር የከረረ ጠብ ውስጥ ገብተውነበር፡፡ ዱቦይስ በመጀመሪያ ብላክ ስታር ላይን የተሰኘውን የመርከብ ንግድ እቅድ (በማርከስ ጋርቬይ የተነደፈውን) ደግፎት ነበር፡፡ ጋርቬይጥቁሮች በሙሉ ወደ አፍሪካ ይመለሱ፣ በአፍሪካ አሜሪካዊያንም ይመሩ (ይስተዳደሩ) ሲል፣ ዱቦይስ ደግሞ ወደ አፍሪካ እንመለስ የምትለውንሃሳብ እደግፈዋለሁ፡፡ ነገር ግን አፍሪካ በአፍሮ አሜሪካዊያን ይመሩ የምትለው ነገር ፈጽሞ የማይሆን ነው በማለት ይቃወመዋል፡፡ በዚህ ሁለትጽንፍ ሃሳብ ባለመስማማት ባደባባይ እስከ መሰዳደብ ደርሰዋል፡፡ ዱቦይስ ጋርቬይን በአሜሪካና በመላው ዓለም ለሚኖሩ ጥቁሮች አደገኛ ጠላትብሎ ከመፈረጁም በላይ ይሄ ሰው ከሃዲ ወይም እብድ መሆን አለበት ሲል ወርፎታል፡፡ ጋርቬይ ደግሞ ዱቦይስን “አንተ እኮ ነጭ እና የጥቁርዲቃላ በተጨማሪም የነጭ ኔግሮ (White men’s nigger) ነህ’’ ይለው ነበር፡፡ ከዚህ ሌላ ጋርቬይ ብላክ ስታር ላይን የሚባለውን ድርጁቱንለማጥፋት አሻጥር እየሰራብኝ ነው በማለት ይወቅሰው ነበር፡፡
ሌላው ለፓን አፍሪካኒዝም ድርጅት ምስረታ ትልቅ አስተዋጽኦ ካደረጉት መካከል ኢትዮጵያዊውን ቲ. ራስ መኮነን እናገኛለን፡፡ መኮነንየተወለደው ጉያና (Guyana) ውስጥ ሲሆን አያቱ ከሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ በአንድ ስኮትላዳዊ የማዕድን ሰራተኛ ነበር የተወሰደው፡፡ ስሙንየቀየረው (ቲ. ራስ መኮነን የተባለው) በሁለተኛው የጣሊያን ኢትዮጵያን ወረራ ጊዜ ነበር፡፡ ለምን ስሙን ቀየረ ካላችሁ፣ አፍሪካዊ ዝርያእንዳለው ለማመልከት ነበር፡፡ አሜሪካ ኮርኔል ዩኒቨርስቲ ከተማረ በኋላ ያቀናው ወደ ዴንማርክ-አውሮፓ ነበር፡፡ ያኔ ታዲያ ኮፐንሃገን-ዴንማርክ ውስጥ የእርሻ ኮሌጅ ውስጥ እየተማረ እያለ ዴንማርክ ለጣሊያን የኢትዮጵያን ንጹሃን ሕዝቦች መግደያ የሚሆን ጅምላ ጨራሽ መርዝአምርታ ትሰጣት ነበር፡፡ ይህንን ድርጊት ጋዜጦች ላይ ጦማር በመጻፍ በግልጽ ተቃወመ፡፡ 18 ወር ከተቀመጠባት ዴንማርክም ተባረረ፡፡ ከዚያወደ እንግሊዝ ተጓዘና በእነ ጆርጅ ፓድሞር በተመሰረተው ኢንተርናሽናል አፍሪካን ሰርቪስ ቢሮ ንቁ ተሳታፊ በመሆንና የቢሮውም የቢዝነስማናጄር በመሆን አገልግሏል፡፡ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ግን ወደ ማንቸስተር ዩኒቨርስቲ በማቅናት ታሪክ አጠና፡፡ በእንግሊዝም የስራፈጣሪ በሆን ብዙ ሆቴሎችን ከፈተ፡፡ ከጆርጅ ፓድሞር እና ኩዋሜ ንኩርማህ ጋር በመሆንም የ1945ቱን የፓን አፍሪካን ኮንግረስ ለማደራጄትብዙ ደክሟል፡፡ በ1947 ፓን አፍሪካ የተባለ ህትመት ልሳን መሰረተና የአፍሪካን የቀን ተቀን ስቃያቸውንና ፍላጎታቸውን ለመላውአፍሪካዊያንና አሜሪካዊያን ያሰራጭ ነበር፡፡
በ1957 ጋና ነጻነቷን ስታገኝ መኮነን ከንኩርማህና ፓድሞር ጋር ሆኖ የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን ለመመስረት ወደ ጋና ሄደ፡፡ በ1966ንኩርማህ መፈንቅለ መንግስት ከተካሄድባቸው በኋላ መኮነን ወደ እስር ቤት ተወረወረ፡፡ ከእስር የተፈቱት በጆሞ ኬንያታ ጥረት ነበር፡፡ ከዚያምጆሞ ኬንያታ አገሬ አገርህ ነው በማለት ይመስላል ወደ ኬንያ ወሰዱት፡፡ ከዚያም የኬንያ ዜግነት ሰጥተው የአገሪቱ የቱሪዝም ሚነስተር አድርገውሾሙት፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያዊ ዝርያ ያለውን ፓን አፍሪካኒስት ብዙዎቻችን አናውቅም፡፡ ምን አልባት የናይሮቢ ዩኒቨርሰትቲ ፕሮፌሰር የሆኑትኬኔት ኪንግ ከዘጠኝ ወር በላይ ሞኮነንን ቃለ መጠይቅ አድርጎ በ1973 ያሳተመውን Pan-Africanism from Within ማግኜት ብንችልየበለጠ ሰለማንነቱ ማወቅ ይቻል ይሆናል፡፡
ክፍል ሁለትን በሚቀጥለው ሕትመት ይዘን እንመጣለን፡፡ ቸር ሰንብቱ፡፡
