ኦነግና ወያኔ ተታኮሱ
- sepastopol
- Jun 1, 2015
- 1 min read
ይሄን ዜና ያወጣው የኬንያው ስታንዳርድ ዲጂታል ነው።
የግጭቱ ትልቅነት እና ትንሽነት ልዮነት ይኖረው ይሆናል ፤ በወያኔ ሰራዊት እና በኦነግ መካከል ግን ግጭት ተከስቷል።
በዚሁ ሳምንት በሶማሊያ ድንበር ላይ ( እዚህ ገጽ ላይም ዜናው ቀርቧል)እንዲሁ ከሶማሊያ ታጣቃዎች ጋር ግጭት ተከስቶ ከሰላሳ አምስት በላይ ሰዎች ሞተዋል ( አንዳንዶች ቁጥሩን ከሃምሳ በላይ ያደርሱታል)
ለወትሮው ኦነግ በራሱ ስጋት የመሆን አቅም ያለው አልነበረም። ነገር ግን አሁን በአመራሩ ውስጥ የእስልምና አክራሪነት ዝንባ ያላቸው ወገኖች እንዳሉ ግልጽ ነው። እነዚህ ሃይሎች ግብጽን ጨምሮ ከሌሎች እስላማዊ ሃይሎች የፓለቲካ ግንኙነት ሊኖራቸው እንደሚችል እና የሎጂስቲክ አቅርቦትም እንደሚያገኙ መገመት ያስፈልጋል ።
ኦነግ በአክራሪ (በግልጽ ባይወጣም) ወደቀ ማለት ፤ የመዋጋት አቅሙንም የአክራሪነት ዝንባሌ ባላቸው ሃይሎች ሊያጠናክር ይችላል ፤ ከኬኒያም ሌላ በሶማሊያ የመንደርደሪያ እና የመዘጋጃ (በህቡዕ) መሰረት ሊያገኝ ይችላል። ኬኒያ ውስጥ ያለው ሁኔታ ራሱ ለኦነግ ተስማሚ ነው ፤ ከእምነትም ከጎሳ ስሜትም አንጻር።
ወያኔ ደሞ ጀብደኝነት በሚመስል ሁኔታ ነገር ግን መነሻው የደህንነት ስጋት በሆነ ምክንያት በኬኒያ ያለውን የህዝብ አመለካከት ለጥላቻ በሚያነሳሳ መልኩ በግዴለሽነት የፓለቲካም የደህንነትም ችግር እየፈጠረ ነው። ይሄ በአክራሪነት ለሚጠናከረው የኦነግ ሃይል ( ኬንያውያኖች ባያውቁትም ቅሉ) ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ አይቀርም።
በሶማሊያም ድንበር በኬኒያም ድንበር ያለውን ሁኔታ ፤ የእስልምና ተስፋፊ ኢምፓየር ( ቢያንስ በአይዲዮሎጂ ደረጃ ) መፍጠር ከሚፈልጉ ኃይሎች ፍላጎት ጋር ተዳምሮ ለኢትዮጵያ ቀላል ፈተና አይደለም። እነ ቱርክ ሶማሌ ላይ የአይዲዮሎጂ ስራ ሲሰሩ ቆይተዋል፤ ወያኔ ደሞ በኢትዮጵያ ተክሏቸዋል።
አሳሳቢ ሁኔታ ነው።
Comments