top of page
Search

በ24ኛው ክፍለጦር ውስጥ የሚገኙ ወታደሮች ትጥቃቸውን እየሸጡ በመጥፋት ላይ ናቸው ተባለ •

  • Writer: sepastopol
    sepastopol
  • Apr 8, 2015
  • 1 min read

millitary-ethiopia.jpg

ትህዲኤን እንደዘገበው በምዕራብ እዝ በ24ኛ ክ/ጦር ውስጥ የሚገኙ የገዢው ኢህአዴግ ጉጅሌ ወታደሮች በየወቅቱ መሳሪያቸውንና ትጥቃቸውን እየሸጡ በመጥፋት ላይ እንዳሉ ተገለፀ:: ትህዴን ከክፍለጦሩ ውስጥ ባገኘነው መረጃ መሰረት ሲል በዘገበው ዘገባው በምዕራብ እዝ 24ኛ ክ/ጦር የገዢው ኢህአደግ ጉጅሌ የሰራዊት አባላት በሚቀጠሩበት ወቅት በስርአቱ የሚገባላቸው ቃል ሰለማይተገበር ካላቸው የማህበራዊ ችግር የተነሳ መሳሪያዎቻቸውንና ትጥቃቸውን እየሸጡ በመጥፋት ላይ እንደሚገኙ ከገለፀ በኋላ። በተለይ ደግሞ የክፍለ ጦሩ አባላት 2ኛ ረጅመንት የሆኑት ሁለት ወታደሮች መጋቢት 20/ 2007 ዓ/ም ክፍላቸውን ትተው ዳንሻ አልፈው በጎንደር መንገድ በመሄድ ላይ እያሉ ለሲቪሉ ማህበረሰብ መሳሪያቸውንና ትጥቃቸውን ግዙን መሳፈሪያ አጥተናል እንዳሏቸው ሊታወቅ ተችሏል::

መረጃው በማከል እንዳስረዳው የክፍለ ጦሩ አዛዦች ለሰራዊቱ የማህበራዊ አገልግሎት ተብሎ የመጣውን ገንዘብ። ከታች እስከ ላይ ተሳስረው ለግል ጥቅማቸው እያዋሉት መሆናቸውን በሰራዊቱ ተገምግሞ ሲያበቃ። እስከ አሁን ድረስ ግን የተተገበረ ለውጥ እንደሌለ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል ሲል ትህዴን ዘግቧል::

 
 
 

コメント


    ሰባስቶፖል የመይሳው 
ኢትዮጵያዊነት ወይም ሞት !

ጋዜጠኞች ይፈቱ 

ጦማርያኑ ይፈቱ 

ፖለቲከኞች ይፈቱ 

ወያኔ ይውረድ 

ብሔራዊ ውርደት በቃ 

   አንድነት ለነጻነት  
  ይከታተሉን 
  • Facebook Basic Black
  • Twitter Basic Black
  • Google+ Basic Black

ተዛማጅ ገጾች 

news
news
g7pf news
arbegnoch

         ያነበቡትን ወደዉታል ? አንግዲያውስ ላንባቢዎች አዳዲስ መረጃዎችን ለማቅረብ ይተባበሩን ..ኢትዮጵያኒዝም 

Donate with PayPal

© 2023 by "This Just In". Proudly created with Wix.com

bottom of page