top of page

የግብፅ እና የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ተወዛገቡ

  • Writer: sepastopol
    sepastopol
  • Mar 27, 2015
  • 1 min read

Part-PAR-Par8130295-1-1-0.jpg

የኢትዮጵያ እና የግብፅ የንግድ የንግድ ማህበረሰብ ልዑካን አባላት ስብሰባ ትላንት በሸራተን አዲስ ሆቴል ሲካሄድ የሁለቱም ሃገራት የጸጥታ ሠራተኞች ጋዜጠኞችን በማስገባት ባለመስማማታቸው ተወዛገቡ፡፡ በግምት ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ገደማ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እና የግብጹ ፕሬዚደንት አብዱልፈታህ አልሲሲ በተገኙበት የሁለቱ ሀገራት የንግድ ማህበረሰብ አባላት ባሰተፈው ስብሰባ ላይ ለመዘገብ የሄዱ የኢትዮጽያ ጋዜጠኞች በግብጽ የጸጥታ ኃይሎች ገብተው እንዳይዘግቡ የተከለከሉ ሲሆን የኢትዮጽያ የጸጥታ ኃይሎች በተቃራኒው ጋዜጠኞቹ ገብተው እንዲዘግቡ በመወሰናቸው ለጥቂት ደቂቃዎች አለመግባባትና ግርግር ተፈጥሯል፡፡ ሆኖም ጋዜጠኞቹ እንዲገቡ በመፈቀዱ አለመግባባቱ ረግቧል፡፡ በዚህ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ እና ግብፅ የንግድ ግንኙነት በየዓመቱ ለውጥ እያመጣ ቢሆንም አመታዊ የንግድ ልውውጡ መድረስ ይገባል ተብሎ ከተገመተው የአምስት ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር አንፃር ሲታይ ግን ዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተገምግሟል። በኢትዮጵያ ለሚሰማሩ የግብፅ ባለሃብቶች ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያገኙ ነው ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በውይይቱ ላይ ማረጋገጫ ሰጥተዋል፡፡ በውይይቱ ላይ የግብፅ ፕሬዝዳን አብዱልፋታህ አል ሲሲ ሃገራቱ በዲፕሎማሲ መስክ እያሳዩት ያለውን ግንኙነት በኢኮኖሚ መስክም እንዲጠናከር ግብፅ ፍላጎቷ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 
 
 

Comments


    ሰባስቶፖል የመይሳው 
ኢትዮጵያዊነት ወይም ሞት !

ጋዜጠኞች ይፈቱ 

ጦማርያኑ ይፈቱ 

ፖለቲከኞች ይፈቱ 

ወያኔ ይውረድ 

ብሔራዊ ውርደት በቃ 

   አንድነት ለነጻነት  
  ይከታተሉን 
  • Facebook Basic Black
  • Twitter Basic Black
  • Google+ Basic Black

ተዛማጅ ገጾች 

news
news
g7pf news
arbegnoch

         ያነበቡትን ወደዉታል ? አንግዲያውስ ላንባቢዎች አዳዲስ መረጃዎችን ለማቅረብ ይተባበሩን ..ኢትዮጵያኒዝም 

Donate with PayPal

© 2023 by "This Just In". Proudly created with Wix.com

bottom of page