top of page
Search

በአብርሃ ጅራ አለመረጋጋቱ ጨምሯል

  • Writer: sepastopol
    sepastopol
  • Mar 19, 2015
  • 1 min read

408041_101047526726868_1117025839_n.jpg

ኢሳት ዜና :-በምእራብ አርማጭሆ ወረዳ በአብርሃ ጅራ ከተማ ተቃዋሚ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩት ሁሉ እየተያዙ በመታሰር ላይ ናቸው። ካለፉት ሶስት ቀናት ጀምሮ እየተካሄደ ባለው ጥብቅ ፍተሻ በርካታ የኢህአዴግ አባላትና የጸጥታ ሃይሎች ተይዘው ሲታሰሩ፣ ቁጥራቸው በውል ያልተወቀ ነዋሪዎች ደግሞ አፈሳውን በመፍራት እያመለጡ የትጥቅ ትግል የሚያደርጉ ተቃዋሚዎችን በመቀላቀል ላይ ናቸው። እስካሁን በተደረገው አፈሳ የወረዳው ምክር ቤት የህዝብ ግንኙነት ዋና ሃላፊ ተቃዋሚዎችን ይረዳል በሚል ሲያዝ፣ ከ20 ያላነሱ የመንግስት ሰራተኞችና መምህራንም ተይዘዋል። ሁለት ፖሊሶች ደግሞ አምልጠው ተቃዋሚዎችን ተቀላቅለዋል። በአካባቢው ያለው አለመረጋጋት ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰ ሲሆን፣ ፌደራል ፖሊሶችና መከላከያ በህዝቡ ላይ ሽብር እየፈጠሩ መሆኑን ነዋሪዎች በመናገር ላይ ናቸው። በአብርሃጅራ የፋርማሲስት ባለቤት የሆኑትና በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ እውቅና ያላቸው አቶ አበራ ጀግኔ ድንበር አቋርጠው አርበኞች ግንቦት7ትን ተቀላቅለዋል ተብሎ መወራቱ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች አፈሳውንና ጥቃቱን እንዲያባብሱ እንዳደረጋቸው ነዋሪዎች ይገልጻሉ።

 
 
 

תגובות


    ሰባስቶፖል የመይሳው 
ኢትዮጵያዊነት ወይም ሞት !

ጋዜጠኞች ይፈቱ 

ጦማርያኑ ይፈቱ 

ፖለቲከኞች ይፈቱ 

ወያኔ ይውረድ 

ብሔራዊ ውርደት በቃ 

   አንድነት ለነጻነት  
  ይከታተሉን 
  • Facebook Basic Black
  • Twitter Basic Black
  • Google+ Basic Black

ተዛማጅ ገጾች 

news
news
g7pf news
arbegnoch

         ያነበቡትን ወደዉታል ? አንግዲያውስ ላንባቢዎች አዳዲስ መረጃዎችን ለማቅረብ ይተባበሩን ..ኢትዮጵያኒዝም 

Donate with PayPal

© 2023 by "This Just In". Proudly created with Wix.com

bottom of page