top of page
Search

ደቡብ ጎንደር ደብረታቦር ለሰዓታት በጥይት እሩምታ ስትታመስ ቆየች

  • Writer: sepastopol
    sepastopol
  • Oct 21, 2014
  • 1 min read

(ዘ-ሐበሻ) በደቡብ ጎንደር ደብረታቦር ከተማ ለሰዓታት በጥይት ስትታመስ መቆየቷን ምንጮች ለዘ-ሐበሻ አስታወቁ:: ከግብር ጋር በተያያዘ ተነሳ በተባለው በዚሁ የጥይት ተኩስ ሶስት አርሶ አደሮች መቁሰላቸው የተዘገበ ሲሆን የሞተ ሰው ግን እንደሌለ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል::

በሌላ በኩል ምኒልክ ሳልሳዊ በደቡብ ጎንደር ደብረታቦር ከተማ ከግብር ጋር በተያያዘ ክፈል ሌላው ቀደም ሲል ከፍያለሁ በሚል በተነሳው ጸብ ፓሊሰ በአሰቃቂ ሁኔታ አርሶአደሩን በመደብደቡ ገበያ ላይ የነበረው ሰው ህግ ፊት አቅርበህ እንዲቀጣ ታደርጋለህ እንጂ አትገድለውም በማለቱ የተነሳ ደብረታቦር ከተማ ለሰዓታት መናወጧንም ዘግቧል::

በዛሬው ዕለት በተነሳው በዚሁ ግጭት የአንድ አርሶ አደር እጅ መቆረጡን የዘገበው ምኒልክ ሌሎች ሶስት አርሶአደሮችም በጽኑ መቁሰላቸውን ዘገቧል:: ተኩስ ያነሳው ፖሊስም ወደ ደበረታቦር ሆስፒታል የተወሰደ መሆኑን የሚናገሩት የአይን እማኞች ሕይወቱ በአስጊ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ጠቁመዋል::

 
 
 

Kommentare


    ሰባስቶፖል የመይሳው 
ኢትዮጵያዊነት ወይም ሞት !

ጋዜጠኞች ይፈቱ 

ጦማርያኑ ይፈቱ 

ፖለቲከኞች ይፈቱ 

ወያኔ ይውረድ 

ብሔራዊ ውርደት በቃ 

   አንድነት ለነጻነት  
  ይከታተሉን 
  • Facebook Basic Black
  • Twitter Basic Black
  • Google+ Basic Black

ተዛማጅ ገጾች 

news
news
g7pf news
arbegnoch

         ያነበቡትን ወደዉታል ? አንግዲያውስ ላንባቢዎች አዳዲስ መረጃዎችን ለማቅረብ ይተባበሩን ..ኢትዮጵያኒዝም 

Donate with PayPal

© 2023 by "This Just In". Proudly created with Wix.com

bottom of page