top of page
Search

በኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መከላከያ ሰራዊት ከሃይል መሪ እስከ ክፍለ ጦር አዛዥ እየተካሄደ በሚገኘው ስብሰባ ላይ ውጥረት በተሞላበት መንገድ ጥያቄዎች መነሳታቸው ተገለፀ

  • Writer: sepastopol
    sepastopol
  • Oct 14, 2014
  • 1 min read

ከመከላከያ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በከፍተኛ አዛዦች ከሚቀርቡ ሃሳቦች የወታደር ደመወዝ ጭማሪ እንዴት ብሎ ችግር እንደፈጠረና ሰራዊት እየጠፋ እንደሆነ፥ ግብፅ የአባይን ግድብ መገደብ ተቀብየዋለሁ ብትልም፤ ቆይታ ችግር ልትፈጥር ስለምትችል በውስጣችን ያለው ሰራዊትም እየጠፋ ስለሆነ እንዴት አድርገን እናስቁመው የሚሉና ሌሎችም ጥያቄዎች እንደተነሱ ለማወቅ ተችሏል፣ በታችኞች ወገን ደግሞ “እየጠፋ ያለው ሰራዊት ምክንያቱ እናንተና መንግስት የፈጠራችሁት ችግር ነው ይህም ለሰራዊቱ ሳታማክሩ ደመወዙን ከላይ እየቆረጣችሁ ታስቀራላችሁ በተለይ በቅርቡ ለልብስ 480 ብር ለጫማ 330 ብር ለቲሸርትና ሌሎችም እየተባለ ይቀነሳል፣ ይህ ደግሞ መንግስት በሰራዊቱ ላይ ንግድ እያካሄደ ነው የተጨመረው ደመወዝም ተመልሶ ወደ መንግስት ገቢ እየተደረገ ነው፣” ሲሉ አማርረው ተናግረዋል፣ እነዚህ የታችኞች የሰራዊቱ ሃላፊዎች ጨምረውም።- “የ7 አመት አገልግሎት ጨርሶ ኑሮየን ልምራ ብሎ የሚጠይቅ ወታደር ይከለከላል፣ መንግስት ራሱ ያወጣውን ህግ ራሱ እየጣሰው ነው ይህ ሁኔታ በእንዲህ ከቀጠለ በውትድርና የሚቀጥል ሰራዊት የለም እየጠፋ ወደ ሃገሩና ወደ ትጥቅ ትግል ከሚያካሂዱ ድርጅቶች እየተቀላቀለ ነው።” ሲሉ መናገራቸውን ጉዳዩን የሚከታተሉ ምንጮቻችን የደረሰን መረጃ አመለከተ፣ -

 
 
 

Comments


    ሰባስቶፖል የመይሳው 
ኢትዮጵያዊነት ወይም ሞት !

ጋዜጠኞች ይፈቱ 

ጦማርያኑ ይፈቱ 

ፖለቲከኞች ይፈቱ 

ወያኔ ይውረድ 

ብሔራዊ ውርደት በቃ 

   አንድነት ለነጻነት  
  ይከታተሉን 
  • Facebook Basic Black
  • Twitter Basic Black
  • Google+ Basic Black

ተዛማጅ ገጾች 

news
news
g7pf news
arbegnoch

         ያነበቡትን ወደዉታል ? አንግዲያውስ ላንባቢዎች አዳዲስ መረጃዎችን ለማቅረብ ይተባበሩን ..ኢትዮጵያኒዝም 

Donate with PayPal

© 2023 by "This Just In". Proudly created with Wix.com

bottom of page