Search
አርበኞች ግንቦት ሰባት በወያኔ ላይ ጥቃት አደረሰ
- sepastopol
- Jul 3, 2015
- 1 min read

"ትግራይ ውስጥ በሚገኙ በሦስቱ ቦታዎች በተደረው አራት ሰዓታትን የፈጀ መራራ ውጊያ ከተለያዩ ሶስት ክፍሎች የተደራጀው የጠላት ጦር በአርበኞች ግንቦት ሰባት የነፃነት ፋኖዎች ፈርጣማ ክንድ ክፉኛ ተደቁሶ የተበታተነ ሲሆን በትንሹ ከ50 በላይ ወታደሮች ሲሞቱ ከ60 በላይ ደግሞ ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል፡፡ የሞቱትና የቆሰሉት ወታደሮቹ ቁጥር አሁን ከተገለፀው ከሁለትና ሦስት እጥፍ ሊያሻቅብ እንደሚችል ይገመታል፡፡ ስለዚህም በአሁኑ ሰዓት አርበኞች ግንቦት 7 ጦርነት አውጇል በሚል ከሁመራ-ዳንሻ፣ ከሁመራ-ሽሬ እና እንዲሁም በተጨማሪ ከሁመራ-ጎንደር የሚገኙት አውራ ጎዳናዎች ጥርቅም ብለው በጦር ሰራዊት ተዘግተው ምንም አይነት የመኪና እንቅስቃሴ የለም፡፡ እስከ ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ በጉጉት ሲጠብቀው የኖረው ህወሓትን በጠብመንጃ የማስወገዱ ጦርነት ፍልሚያ አብሳሪ የሆነው ፊሽካ በአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ እነሆ ተነፍቷል፡፡
コメント