አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተባለው የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት
- sepastopol
- May 23, 2015
- 1 min read

News May 24, 2015 (ግንቦት 15 ቀን 2007 ዓ.ም.) #አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተባለው የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት ሐሙስ ግንቦት 14 ቀን ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ ይካሄዳል በተባለው ምርጫ ዋዜማ በኢትዮጵያውና መሰራታዊና ሰብአዊ መብት ላይ የተቀናጀና የተቀነባበረ አፈና በስፋት እየተካሄደ መሆኑን አጋልጧል። የምርጫው ውድድር በሚደረግበት ወቅት የዜጎች የመናገር፤ የመሰብሰብና የመደራጀት መብታቸው ታፍኗል፤ ይህም አፈና ዜጎች በነጻነትና ያለ ፍራቻ በምርጫም ሆነ በሌላ መንግስታዊ ስራዎች ከመሳተፍ ያገዳቸው ከመሆናቸው ሌላ በህጋዊ መንገድ ለመቃወም እንቅፋት ፈጥሯል በማለት የአምነስቲው የምስራቅ አፍሪካና የአፍሪካ ቀንድ እንዲሁም የትልልቆች ሀይቆች ግዛታዊ ተወካይ ተናግረዋል። የአምነስቲው መግለጫ የወያኔ ባለስልጣኖች በህጋዊ መንገድ የተመዘገቡ ፓርቲ አባላትን፤ ጋዜጠኞችን፤ ጦማሪያዎችንና በተቃውሞ ሰልፍ የተሰለፉትን በርካታ ዜጎች ማሰራቸውን፤ የተመዘገቡ የተቃዋሚ ድርጅቶች ተወዳዳሪዎችን ህገ ወጥ በሆኑ መንገድ መሰረዛቸውን፤ የዘረዘረ ሲሆን እንዲሁም የተቃዋሚ ድርጅቶች አባሎችና ተወዳዳሪዎች በጸጥታ ኃይሎች መድብደባቸውንና መታሰራቸውን አጋልጧል። በተጨማሪም የተላያዩ ማስፈራሪያዎች ለጋዜጠኞችና ለፖለቲካ ድርጅቶች አባላትና ባጠቃላይ ለተቃዋሚዎችን በማስተላለፍ ድምጻቸውን ጸጥ ለማድረግ ሞክረዋል ብሏል። በርካታ የተቃዋሚ ድርጅቶች አባላት ኢሰብአዊ በሆነ ሁኔታ ተደብደበው እስር ቤት የገቡ መሆኑን ጠቅሶ እስክንድር ነጋንና ርዮት ዓለሙን ጨምሮ ከ17 በላይ የሆኑ ጋዜጠኞች ተፈርዶባቸው በእስር እንደሚማቅቁ እንዲሁም በርካታዎቹ ወደ ጎረቤት አገሮች የተሰደዱ መሆናቸውን ዘርዝሮ አቅርቧል። ምርጫው በማንኛውም መመዘኛ ፍትሐዊና ርቱዓዊ እንደማይሆን ገልጾ ምርጫውን እታዘባለው እያለ ለሚመጻደቀው የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ ክፍልም የምርጫውን ሂደት በትክክል ታዝቦ ትክክለኛና አድሎ አልባ መረጃ እንዲያቀርብ የአምነስቲው መግለጫ አሳስቧል።
Comentários