top of page
Search

24/04/15 በኢትዮጵያን እናድን አንድነት ማህበር በእስራኤል የተዘጋጀ የጸሎትየሀዘንና የሻማ ማብራት ሥነ-ሥርአት ስብሰባ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ

  • Writer: sepastopol
    sepastopol
  • Apr 26, 2015
  • 2 min read

መምህር አባ ሀረገወይን ብርሌ በክብር እንግድነት በተገኙበት

በአንድ ሳምንት ውስጥ በተለያየ አቅጣጫና አገሮች የተለያየ የጭካኔ ኢ ሰብዓዊና ዘግናኝ እርምጃ

የተወሰደባቸውን ንጹሃን ወገኖቻችንን አስመልክቶ በኢትዮጵያን እናድን አንድነት ማህበር በእስራዔል

የተዘጋጀው ወገናዊ፤ የጸሎትና የሻማ ማብራት የስብሰባ ዝግጅት እጅግ ልብ በሚነካና ወገናዊነቱ በሚያኮራ ስነ

ስርዓት ተፈጽሟዋል ::

ቀደም ብሎ ማህበሩ ባወጣው ማስታወቂያ ቅደም ተከተል መሰረት የማህበሩ አመራር ካደረገው የዝግጅቱ ስነ

ስርዓት ገለጻ ቀጥሎ ዝግጅቱን የሃይማኖት አባቶች በቡራኬ የከፈቱት ሲሆን ከአጀማመሩ እስከ ፍጻሜው

በተሳካ ሂደት ተጠናቆአል ::

በዝግጅቱ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሃይማኖትና ብሔር ሳይለየው በኢትዮጵያዊነቱና በሰውነቱ ብቻ በወገኖቻችን

ላይ የደረሰውን ዘግናኝ የሰይጣን ተግባር ለማውገዝና በንጹህ ደም ለተሰውት የህሊና ጸሎት ብሎም በግሉ

ወይም በሚወክለው የሃይማኖት ወይም የማህበር ተቁአም የተሰማውን የሃዘን ስሜትና ብሶት ለመግለጽ

በተቻለ መጠን ጥቁር ለብሶ በቦታው በመገኘት ወገናዊ ተሳትፎውን በንግግርና ሻማ በማብራት አሳይቷል ::

ኤርትራዊ ወገኖቻችንም አብረው በዝግጅቱ ላይ የተገኙ ሲሆን ለዚህም የአንድነት ተሳትፎ ቀደም ብሎ

ማህበሩ ጥሪ አድርጎላቸውና ሰፊዋን የኢትዮጵያ ካርታ በመቅረጽ የሁለቱንም አገሮች ባንዲራ ላይና ታች

አድርጎ በዝግጅቱ ቦታ በማስቀመጥ አንድነታችንን በማንጸባረቅ : እነሱም የሚናገሩበትን ክፍለ ጊዜ (የንግግር

ሰዓት) በማዘጋጀት በተወካያቸው በኩል ንግግር በማድረግና ሻማ በማብራት የሀዘናችን ተካፋይ ሆነዋል ::

ከማች ቤተስብ ከአዲስ አበባ በስልክ የሀዝን ስሜታቸውን ለታድሚዎች ገልጸዋል ምስግናም አቅርበዋል

ከካናዳ በእስራኤል በግል ግብኝት ላይ የነበሩት አቶ መላኩ በየነ ጉብኝታቸውን አቋርጠው በፕሮግራሙ

በመሳተፍ እጅግ ልብ የሚነካ የሃዘን ስሜታችውን ገልጸዋል

በዝግጅቱ ቦታ ብዙ የተሰዉት ወገኖቻችን ፎቶዎችና ሻማዎች ተደርድረው : እንዲሁም የኢትዮጵያ

የእስራዔልና የኤርትራ ባንዲራዎች ከፍ ብለው ሲውለበለቡ ታይተዋል ::

የሃይማኖት አባቶች : ጎልማሶች : ሴቶችና ወጣቶች ሃዘናቸውንና ለዚህም ሃዘን የዳረገንን የአስተዳደር

ድህነትወይም ወያኔ ነው መንግስት ጠላት የሆነብን ሕዝብ ነን በማለት በሃዘን በንዴትና በእንባ ብሶታቸውን

እየተፈራረቁ ተናግረዋል ::መፈሳዊና የሃዘን መዝሙሮች ተስምተዋል

በተለይ የሃይማኖት አባት የሆኑት መምህር አባ ሐረገወይን ብርሌ ሕዝቡን እጅ ለጅ አያይዘው ባደረጉት

ንግግር ወገን

መሬት ላይ ተንበርክኮ እንባውን አፍስሷል :: በዚያችም ቅጽበት በታረዱት ወንድሞቻችን ስም ባደረጉት

ንግግር ሆድና ጀርባ መስሎ አመታት የኖረው ኢትዮጵያዊና ኤርትራዊ ወገን አንድ አካል ሆኖ ታይቷል ::

በአጠቃላይ ዝግጅቱ ካጀማመሩ እስከ ፍጻሜው ፍጹም ሰላምና ፍቅር የሞላበት ወገን እጅ ለጅ ተያይዞ

ያነባበት : አንገት ደፍቶ የጸለየበት : ወያኔንና አሸባሪዎችን ያወገዘበትና ለወደፊቱ አንድነትን የሰበከበት

በጸሎት ተጀምሮ በምስጋና የተጠናቀቀ ከ400 ያላነሱ ታዳሚዎች የተሳተፉበት የተሳካ ስብሰባ ነበር::

በሌላ በኩል የአለም አብያተ ቤተ ክርስቲያን ተወካዮችና የውያኔው አምባስደር በተግኘበት

በ25/04/15 በእየሩሳሌም ደብረ ገነት ኪዳነ ምህርት ቤተ ክርስቲያን ተመሳሳይ የጸሎት ስነ-ሥርዓት የተካሄደ

ቢሆንም አምባስደሩ ለመናገር ሲሞክር እዚያው በነበሩ ጥቂት ወግኖች ባድጉት ጥረት ንግግሩን ሊያቋርጥ

ተገዷል

 
 
 

Comments


    ሰባስቶፖል የመይሳው 
ኢትዮጵያዊነት ወይም ሞት !

ጋዜጠኞች ይፈቱ 

ጦማርያኑ ይፈቱ 

ፖለቲከኞች ይፈቱ 

ወያኔ ይውረድ 

ብሔራዊ ውርደት በቃ 

   አንድነት ለነጻነት  
  ይከታተሉን 
  • Facebook Basic Black
  • Twitter Basic Black
  • Google+ Basic Black

ተዛማጅ ገጾች 

news
news
g7pf news
arbegnoch

         ያነበቡትን ወደዉታል ? አንግዲያውስ ላንባቢዎች አዳዲስ መረጃዎችን ለማቅረብ ይተባበሩን ..ኢትዮጵያኒዝም 

Donate with PayPal

© 2023 by "This Just In". Proudly created with Wix.com

bottom of page