ልዑል ዶ/ር አስፋወሰን ዓሥራተ የኢትዮጵያ ችግር መፍትሄው ብሔራዊ እርቅ ብቻ እንደሆነ ይናገራሉ
- sepastopol
- Apr 10, 2015
- 1 min read

ድምጽ ምንጭ SBS Amharic Radio.
የእቴጌ መነን የልጅ ልጅ፣ የልዑል አሥራተ ካሣና የንግሥት ዙሪያሽ ወርቅ ገብረ እግዚአብሔር ልጅ የሆኑት መኖሪያቸውን በለርመን ሀገር ያደረጉት ለዑሉ ላለፉት 40 ዓመታት ኢትዮጵያ ያሳለፈችው ዘመን የጨለማ ዘመን ታሪክ ነው ይላሉ: ኢትዮጵያ በእነዚህ 40 ዓመታት የእርስ በእርስ ጥላቻ የተስፋፋበት፣ የአብሮ መስራት መንፈስ የጠፋበት ፣ የምቀኝነት አንደበት የጨመረበት ስርዓት እንጂ ለወጥ ያመጣ ስርዓት የለም ብለው ያምናሉ::
የንጉሱ ስርዓት የመጀመሪያውን የብሔራዊ እርቅ አጋጣሚን እንዳበላሸ ተናግረው በመቀጠልም የተፈጠሩት አጋጣሚዋችን የተጠቀመ ስርዓት በድጋሚ እንዳልታየ ይናገራሉ:: ስለሆነም አሁን በተገኘው አጋጣሚ የብሔራዊ እርቅ ማድረግ እና የተሻለች ወደፊት የምትጓዝ ኢትዮጵያ መፍጠር አለብን ይላሉ እንደምሳሌም የጠቀሱት የደርጉ ስርዓት እነዚህን እነዚህን ጉዳዮች አጥፍተናል ብለው ቢቀርቡ ይቅርታ ተባብለን ወደ አዲስ ምዕራፍ መግባት አለብን ይላሉ::
የኢህአዴግ ስርዓት የተጣላ በሌለበት ብሔራዊ እርቅ አያስፈልግም ለሚልበት አቋሙም ምላሽ አላቸው::
በእርግጥ የኢህአዴግ ስርዓት እና አስተሳሰብ በእውን (realism) ላይ የተመሰረተ አይደለም ኢህአዴግ ከፖለቲካዊ ጥቅም አንጻር ስለሚንቀሳቀስ እንጂ ብሄራዊ እርቅ መሰረታዊ የሶስት ስርዓት ታሪክን አስተካክሎ ወደፊት የሚያራምድ እውነታ ነው ብለዋል::
በስተመጨረሻም በስደት ለሚኖሩ፣ ለኢትዮጵያ መንግስት ፣ ለፖለቲካ ድርጅቶች እና አመራሮች መልዕክት አስተላልፈዋል
Comments