top of page

ህወሃት መሪ ያጣ ድርጅት ነው። Abebe Gellaw

  • Apr 4, 2015
  • 1 min read

images (1).jpg

ህወሃት መሪ ያጣ ድርጅት ነው። እኔ ለህወሃቶች የምመኝላቸው፣ እውነተኛ እራእይ ያለው መሪ እንዲያገኙ ነው። ለነገ ሳይስቡ ዛሬ ሆድን በኪሳራ ከሞምላት፣ እራስን ከማወደስ፣ ሌሎችን ከማኮሰስ፣ አፈናቅሎ ከመውረስ፣ አምታቶ ከመዝረፍ፣ በሃሰት ከመክሰስ፣ ህዝብን ፈርቶ ከመኖር፣ በደካማ ዜጎች ስቃይ ከመደሰት፣ በዘርና በጎጥ ከመከፋፈል፣ በባዶው ከመጎረር፣ የሃሰት ክብርና ዲግሪ ከጥቁር ገበያ በርካሹ ከመሰብሰብ፣ ጥራት የሌላቸው የሰው አሻንጉሊቶች ከመሰብሰብ የሚያድን መሪ ያስፈልጋቸዋል። ህወሃቶች ቆራጥ መሪ ሲያገኙ የትናንቱ ስህተታቸው ሁሉ ፍንትው ብሎ ይታያቸዋል። የበደሉትን ሁሉ ይቅርታ ይለምናሉ። አገር ማለት ሁሉም ያልአድርኦ በዜግነቱ ተከብሮ ከማንም ሳይበልጥ ከማንም ሳያንስ ሊኖርበት የሚገባው ምድር መሆኑ ይገለጥላቸዋል። ህወሃቶች መሪ ሲያገኙ ወደ ገደል ቁልቁል ከማብረር ይድናሉ። ፍሬን ይይዛሉ! ቆም ብለው ያስባሉ… “ውድ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ! በነጻነት ስም፣ ለችግር፣ ለመከራ፣ ለስደት፣ ለእስራት፣ ለግድያ፣ ለግፍ፣ ለዝርፊያ፣ ለአድልኦ፣ ለስርአት አልባነት፣ ተዘርዝሮ ለማያልቅ በደልና ግፍ ዳርገንሃል። ለሁላችንም የሚሆን አዲስ ምዕራፍ መክፈት ግድ ሆኖብናል። ይቅርታህን እንለምናለን!” የሚል ደፋር መሪ ያሳፈልጋቸዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ ሁል ግዜም ይቅር ባይ ነው። መንደር መሃል እንደነጋበት ጅብ መሄጃ ከማጣቱ በፊት ህወሃት ደፋር መሪ እንዲኖረው እመኝለታለሁ። የእነ መለስን ስህተት ከሚደግም መሪ ይልቅ እወነተኛ ራእይ ያለው ቆራጥ መሪ ያስፈልገዋል። አርቆ አሳቢ፣ ከአድልኦ እና ጠባብነት የጸዳ ከዛሬ ከንቱነት ይልቅ ለመጪው ትውልድ ሁሉ የሚያስብ መሪ..

 
 
 

Comments


    ሰባስቶፖል የመይሳው 
ኢትዮጵያዊነት ወይም ሞት !

ጋዜጠኞች ይፈቱ 

ጦማርያኑ ይፈቱ 

ፖለቲከኞች ይፈቱ 

ወያኔ ይውረድ 

ብሔራዊ ውርደት በቃ 

   አንድነት ለነጻነት  
  ይከታተሉን 
  • Facebook Basic Black
  • Twitter Basic Black
  • Google+ Basic Black

ተዛማጅ ገጾች 

news
news
g7pf news
arbegnoch

         ያነበቡትን ወደዉታል ? አንግዲያውስ ላንባቢዎች አዳዲስ መረጃዎችን ለማቅረብ ይተባበሩን ..ኢትዮጵያኒዝም 

Donate with PayPal

© 2023 by "This Just In". Proudly created with Wix.com

bottom of page