top of page

ኢንጂነር ይልቃል ከአገር እንዳይወጡ ተከለከሉ፣

  • Apr 1, 2015
  • 1 min read

1623753_1547958398807449_5560175126928805323_n.jpg

ኢንጂነር ይልቃል ከአገር እንዳይወጡ ተከለከሉ፣ አቶ በላይ ፍቃዱ ወደ አገር ቤት ተመልሰዋል የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር እንደገና ከአገር እንዳይወጣ ተከለከለ። ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች ፣ አገር ዉስጥ ለሚደርገዉ ሰላማዊ የምርጫ ዘመቻ ከኢትዮጵያዉያን የገንዘብ ድጋፍ ለማሰባሰብና በአገር ቤት ስላለው ስትግል ማብርሪያ ለመስጠት በዲሲ፣ ቦስተን፣ ቺካጎ፣ ሲያትል በመሳሰሉት ከተሞች ስብሰባ ለመካፈል ነበር ወደ አሜሪካ ሊመጣ የነበረው።

ተወዳጁ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመነበር የነበሩት አቶ በላይ ፍቃዱ ከወራት በፊት በነበረ እቅድ መሰረት ለተወሰኑ ሳምንታት በአሜሪካ ቆይታ አድርገው ወደ አገር ቤት ተመልሰዋል።

ኢንጂነር ይልቃል ከአገር እንዳይወጣ ሲከለክል ይሄ ሁለተኛ ሲሆን፣ ሕወሃት የዜጎች ሰብዓዊ መብት ረጋጭ መሆኑ ከሚያሳዩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ማስረጃዎች መካከል ይሄም አንዱ ነው።

 
 
 

Comments


    ሰባስቶፖል የመይሳው 
ኢትዮጵያዊነት ወይም ሞት !

ጋዜጠኞች ይፈቱ 

ጦማርያኑ ይፈቱ 

ፖለቲከኞች ይፈቱ 

ወያኔ ይውረድ 

ብሔራዊ ውርደት በቃ 

   አንድነት ለነጻነት  
  ይከታተሉን 
  • Facebook Basic Black
  • Twitter Basic Black
  • Google+ Basic Black

ተዛማጅ ገጾች 

news
news
g7pf news
arbegnoch

         ያነበቡትን ወደዉታል ? አንግዲያውስ ላንባቢዎች አዳዲስ መረጃዎችን ለማቅረብ ይተባበሩን ..ኢትዮጵያኒዝም 

Donate with PayPal

© 2023 by "This Just In". Proudly created with Wix.com

bottom of page