top of page
Search

ወይዘሮ አዜብ መስፍን በደህንነት ሹሙ ጥርስ ውስጥ ዳግም መታኘክ ጀምረዋል::

  • Writer: sepastopol
    sepastopol
  • Mar 14, 2015
  • 1 min read

images (1).jpg

መውደቂያው የደረሰው ወያኔ እርስ በርሱ መበላላት ጀምሯል:ትግላችንን አጠናክረን መቀጠል ያለብን ወሳኝ ወቅት ላይ ነን:: - Minilik Salsawi - የደህንነት ሹሙ ጌታቸው ማለት እንደ ወይዘሮ አዜብ አነጋገር "...ሰታዊ መሲሉ ክምተመን ዝናከስ.." እንደሆነ ሲታወቅ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወይዘሮ አዜብ በቤተሰቦቻቸው ስም ያቋቋሙት ድርጅት እና ያፈሩት ሃብት እና ንብረት ላይ ክትትል እንዲደረግ አቶ ጌታቸው አሰፋ ቡድናቸውን ማዘዛቻው ወይዘሮዋ በደህንነት ሹሙ ጥርስ ውስጥ ዳግም መታኘክ መጀመራቸው ታውቋል::ወዳጆቻቸውን ተገን በማድረግ በቤተሰቦቻቸው ስም የሚገቡ ከባድ እና ቀላል መሳሪያዎች እንዲሁም የተለያዩ ቁሳቁሶች ቀረጥ ስለማይከፈልባችው ጥያቄ በአዜብ መስፍን ላይ ቢያስነሳም ወይዘሮዋ ከተጠየቅን አብረን ነው መጠየቅ ያለብን ሲሉ ከዚህ ቀደም መልስ መስጠታቸው እና ከዘረፋ ጋር ጋር የተያያዘ ጥቄዎች ሲነሳባቸው በጄኔራሎች ካኪ ስር መደበቅ ተግባራቸው መሆኑ ለደህንነት ፈላጭ ቆራጮ እንዳልተዋጠላቸው ታውቋል::

ከዚህ ቀደም በቤተመንግስቱ የውስጥ ሽኩቻ ውስጥ ቂም በቀል እንዳለባቸው የሚነግርላቸው የደህንነቱ ሹም አቶ ጌታቸው ወይዘሮ አዜብን አጥምዶ የሰው መሳቂያ ለማድረግ ከማሴር አልተቆጠቡን ሲሉ የወይዘሮዋ የቅርብ ሰዎች በምሬት ይናገረሉ:: ወዳጅ መሳይ ተናዳፊ እባብ ሰታዊ መሲሉ ክምተመን ዝናከስ ብላ አዜብ የምትጠራው ጌታቸው በዘመዶቿ ስም ያፈራችውን ንብረት የመውረስ እና ሸጦ ገንዘቡን በሌላው እንደለመደው ከሃገር የማሻገር እቅድ እንደያዘ የቅርብ ወዳጆቿ አክለው ገልጸዋል::በደህንነት ሰዉየውና በሴትየዋ መካከል ያለውን ቅራኔ ፈትቶ ጉዳዩን ለማረጋጋት አቶ በረከት ስምኦን እና ጄኔራል ሳሞራ ጥረት ላይ መሆናቸው ታውቋል::

በውጪና በውስጥ ስልጣኑን ለህዝብ እንዲያስረክብ ትልቅ ጫና የበዛበት ወያኔ ከሃገር እና ህዝብ ሃብት በተጨማሪ እርስ በርሱ መበላላት እና መዘራረፍ የጀመረ ሲሆን ኢትዮጵያውያን ትግላችንን አጠናክረን በመቀጠል ይህንን የበሰበሰ ዘራፊ ስር አት ለማስወገድ በጋራ እና በአንድነት በመታገል የዜግነት ሃላፊነታችንን መወጣት አለብን::

 
 
 

Comentarios


    ሰባስቶፖል የመይሳው 
ኢትዮጵያዊነት ወይም ሞት !

ጋዜጠኞች ይፈቱ 

ጦማርያኑ ይፈቱ 

ፖለቲከኞች ይፈቱ 

ወያኔ ይውረድ 

ብሔራዊ ውርደት በቃ 

   አንድነት ለነጻነት  
  ይከታተሉን 
  • Facebook Basic Black
  • Twitter Basic Black
  • Google+ Basic Black

ተዛማጅ ገጾች 

news
news
g7pf news
arbegnoch

         ያነበቡትን ወደዉታል ? አንግዲያውስ ላንባቢዎች አዳዲስ መረጃዎችን ለማቅረብ ይተባበሩን ..ኢትዮጵያኒዝም 

Donate with PayPal

© 2023 by "This Just In". Proudly created with Wix.com

bottom of page