top of page
Search

መድረክ “በፌዴራሊዝም ” ጉዳይ እንዳይከራከር ታገደ

  • Writer: sepastopol
    sepastopol
  • Mar 14, 2015
  • 1 min read

hqdefault.jpg

የኢህአዴግ ምርጫ ቦርድ እንደገለፀው በነገው ዕለት በቴለቪዥን የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር ይጀመራል፡፡ የነገው ክርክር ሰብኣዊ መብትና መድብለ ፓርቲ የተመለከተ ሲሆን ነገ ከጥዋቱ 3፡00 ሰዓት ተደርጎ ቀን ሙሉ ኢህአዴግ እማይጥመውን ንግግር በመቀስ ሲቆርጦው ከዋለ በኋለ ማታ ከ 2 ሰዓት ዜና በሁዋላ ይቀርባል ተብለዋል፡፡

በተያያዘ ዜና መድረክ በፌዴራሊዝም ላይ በሚደረግ ክርክር እናዳይከራከር ተከልክለዋል፡፡ ህዝብ ከህዝብ ጋር እያናቆረ ያለው አሸባሪው የኢሀአዴግ ፍረዳሊዝም እንዳንተቸውና አማራጭ ፌዴራሊዝማችን እንዳናቀርብ በጠበንጃ አምላኪዎች ታግደናል፡፡ በእውነቱ መጣም አሳዣኝ ነው፡፡ በዚህ ወሣኝ ርአስ ላይ እንዴት እንከለከላለን? መድረክ እኔና ዶክተር መረራ ጉዲናን በፌዴራሊዝም ጉዳይ ላይ እንድንከራከር ወኩሎን ነበር፡፡ ሆኖም ግን ኢህአዴግ በኔ ሳንባ ከሚተነፍሱ ቅልብ ፓርቲዎች ጋር ብቻ ነው የምከራከረው ብሎ እምቢ በማለት ህገወጥነቱን ቀጥሎበታል፡፡ ኢህአዴግ ከክርክሩ የጨረገደን በክርክሩ እንደምንዘርረው ስላወቀ ነው፡፡ አምስት አመት ሙሉ ጠብቀን ለመድረክ የተሰጠው 6 ደቂቃ ብቻ ነው ግን ኢህአዴግ 6 ደቂቃዋም በጣም ስለፈራት ከለከለን፡፡ አጃኢብ! ለማንኛውም ነገ ሰብኣዊ መብትና መድብለ ፓርቲ በሚል ዶክተር መረራና የመድረክ የወጣቶች ክንፍ ምክትል ሊቀመንበር አቶ አብርሃም ሳልህ መድረክን ወክለው ይቀርባሉ፡፡

 
 
 

Commentaires


    ሰባስቶፖል የመይሳው 
ኢትዮጵያዊነት ወይም ሞት !

ጋዜጠኞች ይፈቱ 

ጦማርያኑ ይፈቱ 

ፖለቲከኞች ይፈቱ 

ወያኔ ይውረድ 

ብሔራዊ ውርደት በቃ 

   አንድነት ለነጻነት  
  ይከታተሉን 
  • Facebook Basic Black
  • Twitter Basic Black
  • Google+ Basic Black

ተዛማጅ ገጾች 

news
news
g7pf news
arbegnoch

         ያነበቡትን ወደዉታል ? አንግዲያውስ ላንባቢዎች አዳዲስ መረጃዎችን ለማቅረብ ይተባበሩን ..ኢትዮጵያኒዝም 

Donate with PayPal

© 2023 by "This Just In". Proudly created with Wix.com

bottom of page