top of page
Search

መነሻ ገጽ - ዜና - ዶ/ር ደብረ ጽዮን በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦታ በአደዋ ይወዳደራሉ

  • Writer: sepastopol
    sepastopol
  • Mar 14, 2015
  • 2 min read

0803fe72dc628e4a2bf444d22497ca6e_L.jpg

ኢሕአዴግ ሥልጣን ከያዘ ጊዜ ጀምሮ በተካሄዱት አራት ጠቅላላ ምርጫዎች የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በተወዳደሩበት በአደዋ የምርጫ ክልል ለመጀመሪያ ጊዜ በዘንድሮ ምርጫ ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል ኢሕአዴግን ወክለው እንደሚወዳደሩበት ለማወቅ ተችሏል፡፡

በመጪው ግንቦት በሚካሄደው አምስተኛ ጠቅላላ ምርጫ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር የትውልድ ቦታና ጠንካራ የፖለቲካ ይዞታ ወክለው፣ ለተወካዮች ምክር ቤት የሚወዳደሩት የሕወሓት ምክትል ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የፋይናንስና የኢኮኖሚ ዘርፍ ክላስተር አስተባባሪና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው በመሥራት ላይ የሚገኙት ዶ/ር ደብረ ጽዮን የሕወሓት ነባር ታጋይ ሲሆኑ፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ በኋላ የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበርና የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው በማገልገል ላይ ይግኛሉ፡፡

ዶ/ር ደብረ ጽዮን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲወዳደሩ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡ ወደ ፌዴራል መንግሥት ከመምጣታቸው በፊት በደቡብ ትግራይ ክልል ምክትል ዋና አስተዳዳሪ፣ በኋላም የትግራይ ክልል የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሠርተዋል፡፡

የአደዋ ከተማ ተወላጅ የሆኑት ዶ/ር ደብረ ጽዮን ወደ ትጥቅ ትግል ከመግባታቸው በፊት፣ ከተማውን በመወከል ታዋቂ የእግር ኳስ ተጫዋች እንደነበሩ የሚያውቋቸው ይናገራሉ፡፡

አደዋን ወክለው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአራት ተከታታይ ምርጫዎች የተወዳደሩት ሟቹ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ሕወሓትን ከ1977 ዓ.ም. ጀምሮ ኢሕአዴግም ከተመሠረተበት ከ1981 ዓ.ም. ጀምሮ በሊቀመንበርነት የመሩ ሲሆን፣ መጀመሪያ ለሦስት ዓመታት የሽግግር መንግሥቱ ፕሬዚዳንት፣ ቀጥሎም እስከ ሕልፈተ ሕይወታቸው በጠቅላይ ሚኒስትርነት አገሪቱን መምራታቸው ይታወሳል፡፡

በአራተኛው ጠቅላላ ምርጫ የቀድሞዋ ሕወሓት ታጋይ ወ/ት አረጋሽ አዳነ ዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ለሉዓላዊነት ፓርቲ አባል የሆነበትን መድረክ በመወከል፣ ከቀድሞ የትግል ጓዳቸው ከአቶ መለስ ጋር መፎካከራቸው አይዘነጋም፡፡ በአሁኑ ምርጫ ግን ዶ/ር ደብረ ጽዮንን የሚወዳደረውን ተፎካካሪ ዕጩ ማወቅ አልተቻለም፡፡

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የዕጩ ተወዳዳሪዎችን የመጨረሻ ዝርዝር የያዘውን ቅጽ አራት በመባል የሚታወቀውን ሰነድ ይፋ ባለማድረጉ፣ በተለይ የኢሕአዴግና የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚወዳደሩባቸውን የምርጫ ክልሎች ለማወቅ አልተቻለም፡፡ ባለፈው ሳምንት ዋነኛ የኢሕአዴግና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ዕጩዎች በአዲስ አበባ የሚወዳደሩበትን ይፋ ያልሆነ ዝርዝር ዋቢ በማድረግ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

 
 
 

Comments


    ሰባስቶፖል የመይሳው 
ኢትዮጵያዊነት ወይም ሞት !

ጋዜጠኞች ይፈቱ 

ጦማርያኑ ይፈቱ 

ፖለቲከኞች ይፈቱ 

ወያኔ ይውረድ 

ብሔራዊ ውርደት በቃ 

   አንድነት ለነጻነት  
  ይከታተሉን 
  • Facebook Basic Black
  • Twitter Basic Black
  • Google+ Basic Black

ተዛማጅ ገጾች 

news
news
g7pf news
arbegnoch

         ያነበቡትን ወደዉታል ? አንግዲያውስ ላንባቢዎች አዳዲስ መረጃዎችን ለማቅረብ ይተባበሩን ..ኢትዮጵያኒዝም 

Donate with PayPal

© 2023 by "This Just In". Proudly created with Wix.com

bottom of page