top of page
Search

በቅድሚያ ነጻነት

  • Writer: sepastopol
    sepastopol
  • Mar 11, 2015
  • 1 min read

11044541_10206224743520665_2811321881273229228_n.jpg

ህዝቡ ተቃውሞውን በተለያዩ መንገዶች መግለጹን ቀጥሏል።በየሱቆች በስፋት እየተሰራጬ የሚገኘው “ርእዮት ሳሙና” አንዱ ነው።

በኢትዮጰያ ህዝባዊ ስብሰባዎችና ሰልፎች ቢታገዱም ህዝቡ በስርዓቱ ላይ ያለውን ተቃውሞ በተለያዩ መንገዶች መግለጹን ቀጥሏል። መጋቢት ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተለይ በአዲስ አበባ በተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ ግድግዳዎችና የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች በየእለቱ “ጭቆና በቃን! ነጸነትና ፍትህ እንፈልጋለን! ለነጸነት ትግል ተነስ!” በሚሉ መፈክሮች አሸብርቀው መታየታቸው የተለመደ ሆኗል። በቅርቡ ደግሞ እነኚሁ የፍትህና የነጻነት ጥያቄዎች በመገበያያ የብር ኖቶች ላይ ሳይቀር በስፋት እየተስተዋሉ መሆናቸው የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። ሂደቱ በዚህ ከቀጠሉ የብር ኖቶች በሙሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ በመፈክር ጽሁፎች መጥለቅለቃቸው እንደማይቀርም መረጃውን ያደረሱን አካላት ገልጸዋል። ከዚህም ባሻገር የአንዳንድ ነጋዴዎች ምርቶች ሳይቀር በታሰሩ የነጻነት ታጋዮች ስም ተሰይመው መታየታቸውን የግለጹት ምንጮች፤ይሁንና ይህ የሆነው በስም መገጣጠም ይሁን አለያም አምራቾቹ ሆነ ብለው በነጻነት ታጋዮቹ ስም ሰይመው በእርግጥኝነት እንዳላወቁ አልሸሸጉም። ከነዚህ ምርቶች መካከል በየሱቆች በስፋት እየተሰራጬ የሚገኘው “ርእዮት ሳሙና” አንዱ ነው። ጉዳዩን አስመልክቶ የ ርእዮት እህት እስከዳር ዓለሙ በፌስ ቡክ ገጿ ባሰፈረችው አስተያየት ፦”የእኛሰፈርሱቆችይህንንምርትበየመደርደሪያቸዉሞልተዉትሳይይህችልጅበጽሑፏለማፅዳትየሞከረችውአልበቃብሏትበፈሳሽሳሙናመልክመጣችእንዴ?ብዬአሰብኩ ” ብላለች። ባለፉት ወራት በቦሌ አካባቢ የሚገኙ ግድግዳዎችና አጥሮች ፦”መሪዎቻችን ይፈቱ! ፍትህ ለኮሚቴዎቻቸን! ጭቆናው ይብቃ!”በሚሉና በሌሎች መሰል መፈክሮች ተሞልተው መታየታቸው ይታወሳል።

 
 
 

Comments


    ሰባስቶፖል የመይሳው 
ኢትዮጵያዊነት ወይም ሞት !

ጋዜጠኞች ይፈቱ 

ጦማርያኑ ይፈቱ 

ፖለቲከኞች ይፈቱ 

ወያኔ ይውረድ 

ብሔራዊ ውርደት በቃ 

   አንድነት ለነጻነት  
  ይከታተሉን 
  • Facebook Basic Black
  • Twitter Basic Black
  • Google+ Basic Black

ተዛማጅ ገጾች 

news
news
g7pf news
arbegnoch

         ያነበቡትን ወደዉታል ? አንግዲያውስ ላንባቢዎች አዳዲስ መረጃዎችን ለማቅረብ ይተባበሩን ..ኢትዮጵያኒዝም 

Donate with PayPal

© 2023 by "This Just In". Proudly created with Wix.com

bottom of page