top of page
Search

ገዥው ፓርቲ መጪውን ምርጫ ተከትሎ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ብቻ ሳይሆን በህዝቡ ላይ ጭምር ከፍተኛ ጫና እየፈጸመ እንደሆነ በተለያዩ ክልል ነዋሪዎች ገለጹ።

  • Writer: sepastopol
    sepastopol
  • Jan 17, 2015
  • 2 min read

የአዲስ አበባ፣የደሴ፣ የሀዋሳ፣የአርባምንጪ፣ የሀረር፣ የሚዛን ተፈሪ፣የሰበታ፣ የባህርዳር፣ የወልቂጤና የሌሎችም ከተሞች ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት፣በካድሬዎች አማካይነት ህዝቡ የምርጫ ካርድ በግዳጅ እንዲወስድ እና ድምጹን ለኢህአዴግ እንዲሰጥ እየተደረገበት ያለው ግፊት ከመቼውም ጊዜ በላይ እየከፋ መጥቷል ከካድሬዎቹም ህዝቡን እያስፈራሩ በግድ ኢህአዴግን እንዲመርጡ እያደረጉ ነው።

በግድ የኢህአዴግ አባል እንዲሆኑና ኢህአዴግን እንዲመርጡ እየተገደዱ መሆናቸውንም የገለጹ በርካቶች ናቸው። ከዚህም በላይ አንዳንድ ውስጥ አዋቂዎች ኢህአዴግ አንዳንድ ሰዎችን ያለፍላጎታቸው በተለያዩ የንግድ እንቅስቃሴዎቻቸው ጫና በመፍጠር ለሱ እንዲሰሩለት በማስጠንቀቅ በየምርጫ ጣቢያው በገለልተኛ ስም ማስቀመጡ የተጋለጠ ሲሆን፤ ሰዎቹ-ከተቃዋሚዎች ጥያቄ ቢቀርብላቸው የሚል ምላሽ ይሰጡ ዘንድ መመሪያ እንደተነገራቸው ተሰምቷል። በተመሳሳይ ምርጫውን ተከትሎ በተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ላይ እየተፈጸመ ያለው እስርና ድብደባ ተባብሶ ቀጥሏል። ታህሳስ 27/2007 ዓ,ም በባህርዳር ከተማ የኢትዮጰያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መድረክ አባላት – በስርዓቱ አገልጋዮች ታፍነው ወዳልታወቀ ስፍራ መወሰዳቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና ያመለክታል። ታፍነው ከተወሰዱት የመድረክ አባላት መካከል፤ አቶ ቴዎድሮስ መለስ፤ ወ/ሮ ሪዒማ ከድር፤ በባህር ዳር ዩንቨርስቲ መምህር የነበረው አቶ ተፈራ ማሙና ሌሎችም የሚገኙበት ሲሆን፤ የታፈኑበት ምክንያትም ሆነ ፤ያሉበት ስፍራ እስካሁን ድረስ አልታወቀም። እንዲሁም ” ኢቲቪ ውሸታም ነው ፣ ኢህአዴግ ሌባ ነው”ብለሀል ተብሎ ክስ የተመሰረተበትና የሶስት ዓመት እስራት የተፈረደበት የመላው ኢትዮጰያ አንድነት ድርጅት አባል የሆነው አዲሱ ሁሴን፤ በእስር ቤት ከፍተኛ ድብደባና ግርፋት እየተፈጸመበት እንደሆነ ድርጅቱ ገልጿል። የደቡብ ወሎ የመኢአድ አባል የሆነው አዲሱ ሁሴን ፍርደኛ እስረኛ ሆኖ ከድብደባና ግርፋት ማረፍ አለመቻሉ፤ በኢትዮጰያ እስር ቤቶች ለሚፈጸሙ የከፉ ሰብ ዓዊ መብት ጥሰቶች አንድ ማሳያ ነው ብለዋል-መረጃውን ያደረሱን የመኢአድ አባል። ከሰሞኑ ብቻ ብቻ ሁለት የአንድነት ፓርቲ አባላት የፐጻርቲውን ጠቅላላ ጉባኤ ተሳትፈው ወደቤታቸው ሲያቀኑ መደብደባቸው እና በወላይታ የሰማያዊ ፓርቲ አስተረባባሪዎች መታሰራቸው ይታወቃል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የመላው ኢትዮጰያ አንድነት ፓርቲና የኢትዮጰያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ በጋራ ባወጡት መግለጫ ገዥው ፓርቲና ምርጫ ቦርድ በተቃዋሚዎች ላይ በተለይም በሰማያዊ፣ በአንድነትና በ መ ኢአድ ፓርቲዎች ላይ የሚፈጽሙትን ዛቻና በደል እንዲያቆሙ መጠየቃቸውን ነገረ-ኢትዮጵያ ዘግቧል።

ፓርቲዎቹ ህዳር 7/2007 ዓ.ም ‹‹በምርጫ ዋዜማ በፓርቲዎች ላይ የሚደርሰው ደባና ዛቻ በአስቸኳይ ይቁም›› በሚል በጋራ ባወጡት መግለጫ ፤ ሰማያዊ ፓርቲ አገራዊ ግዴታውን እየተወጣ በመሆኑ፣ እንዲሁም መኢአድና አንድነት ብቃት ያላቸው ልሂቃንን ማፍራት በመቻላቸው ስጋት የተፈጠረበት ገዥው ፓርቲ – ፓርቲዎቹን ለማጥፋት እየጣረ መሆኑን በመጥቀስ፤<> ሲሉ ወቅሰዋል፡፡ ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው-ገዥው ፓርቲ -በፓርቲዎቹ ላይ እየፈጸመ ካለው ድርጊት እንዲቆጠብ፤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድመረ ከገዥው ፓርቲ መሳሪያነት ወጥቶ የተጣለበትን ኃላፊነት እንዲወጣ፤ አሳስበዋል፡፡

 
 
 

Comments


    ሰባስቶፖል የመይሳው 
ኢትዮጵያዊነት ወይም ሞት !

ጋዜጠኞች ይፈቱ 

ጦማርያኑ ይፈቱ 

ፖለቲከኞች ይፈቱ 

ወያኔ ይውረድ 

ብሔራዊ ውርደት በቃ 

   አንድነት ለነጻነት  
  ይከታተሉን 
  • Facebook Basic Black
  • Twitter Basic Black
  • Google+ Basic Black

ተዛማጅ ገጾች 

news
news
g7pf news
arbegnoch

         ያነበቡትን ወደዉታል ? አንግዲያውስ ላንባቢዎች አዳዲስ መረጃዎችን ለማቅረብ ይተባበሩን ..ኢትዮጵያኒዝም 

Donate with PayPal

© 2023 by "This Just In". Proudly created with Wix.com

bottom of page