top of page
Search

የአንድነት ፓርቲ ሴቶች ጉዳይ ምክትል ኃላፊ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፀመባት

  • Writer: sepastopol
    sepastopol
  • Jan 13, 2015
  • 1 min read

የአንድነት ፓርቲ ሴቶች ጉዳይ ምክትል ኃላፊ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፀመባት

ወይዘሪት ወይንሸት፣ ንፍስ ስልክ አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ ሁለት ሰዎች ከረፋዱ 5፡30 ላይ ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመባት

ለፍኖተ-ነፃነት የደረሰው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወይዘሪት ወይንሸት፣ ነፍሰጡር መሆኗ የሚታወቅ ሲሆን ደብዳቢዎቹም ሆዷን በመርገጥ ድብደባውን ሲፈፅሙባት እንደነበር

ለማወቅ ተችሏል፡፡ ደብዳቢዎቹ ድብደባውን ፈፅመው የተሰወሩ ሲሆን ወይዘሪት ወይንሸት፣ በአሁኑ ሰዓት ራሷን ስታ ሆስፒታል

መግባቷን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ወይንሸት፣ አንድነት ፓርቲ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለማካሄድ በጠራው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በከፍተኛ ድምፅ የአስመራጭ ኮሚቴ

ሰብሳቢ ሆና በመመረጥ በምርጫው ላይ ጉልህ ሚና በመጫወት ድርሻዋን መወጣቷ ይታወሳል፡፡ በእለቱ በተካሄደው ጠቅላላ

ጉባኤ ላይ በአንድነት ስም የሚነግዱትን ግለሰቦች በማውገዝ አስተያየቷን መሰንዘሯን ተከትሎ ድብደባው ሊፈፀምባት እንደተቻለ

ለማወቅ ተችሏል፡፡

ወይዘሪት ወይንሸት፣ በፓርቲው ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ያላት ወጣት ከመሆኗም በተጨማሪ የአንድነት ፓርቲ ሴቶች ጉዳይ

ምክትል ሀላፊ በመሆን በመስራት ላይ ትገኛለች፡፡ በዚህ ሳምንት ብቻ በአንድነት አባላት ላይ ድብደባ ሲደርስ ለሁለተኛ

ጊዜ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ባለፈው እሁድ በአቶ መሳይ ትኩ፣ ላይ ድብደባ መፈፀሙ ይታወሳል፡

 
 
 

Yorumlar


    ሰባስቶፖል የመይሳው 
ኢትዮጵያዊነት ወይም ሞት !

ጋዜጠኞች ይፈቱ 

ጦማርያኑ ይፈቱ 

ፖለቲከኞች ይፈቱ 

ወያኔ ይውረድ 

ብሔራዊ ውርደት በቃ 

   አንድነት ለነጻነት  
  ይከታተሉን 
  • Facebook Basic Black
  • Twitter Basic Black
  • Google+ Basic Black

ተዛማጅ ገጾች 

news
news
g7pf news
arbegnoch

         ያነበቡትን ወደዉታል ? አንግዲያውስ ላንባቢዎች አዳዲስ መረጃዎችን ለማቅረብ ይተባበሩን ..ኢትዮጵያኒዝም 

Donate with PayPal

© 2023 by "This Just In". Proudly created with Wix.com

bottom of page