top of page
Search

የአርበኞችና ግንቦት ሰባት ዲሞክራሲያዊ ግንባር በአስመራ ሊመሰረት ነው::የግንቦት ሰባት አመራር አባላት አስመራ ገቡ ::

  • Writer: sepastopol
    sepastopol
  • Dec 17, 2014
  • 1 min read

የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይሎች (Amara Force) እኛ በውህደቱ የለንበትም ብሏል:: Minilik Salsawi ምንሊክ ሳልሳዊ - ከአስመራ ከተማ የሚገኙ ምንጮቼ በስልክ እንዳስታወኩኝ ካለፈው ሃሙስ ጀምሮ የግንቦት ሰባት አመራር አባላት የሆኑት አቶ ነእመን ዘለቀ:የአቶ አንዳርጋቸው ወንድም አቶ ብዙአየሁ ጽጌ አቶ አበበ ቦጋለ እና ሌሎች የኢሳት ሪፖርተሮችን አስከትለው አስመራ የገቡ ሲሆን የአርበኞች ግንባር አመራሮች ወደ አስመራ የሚልኩትን ሰው መርጠው ባለመጨረሳቸው እንደዘገዩ ሲጠቆም እስከ እሁድ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል::ዶክተር ብርሃኑ ነጋ መግባታቸውን ለማረጋገጥ ቢሞከርም ሆተሎች ጥብቅ የጸጥታ ክትትል ስለሚደረግባቸው መረጃዎች ለጊዜው እንዲዘገዩ ተደርጓል:: በአስመራ የተለያየ ሆተል ማረፊያ የተዘጋጀላቸው የግንቦት ሰባት አመራሮች የአርበኞች ግንባር አመራሮች እንደገቡ በመጭው አዲስ አመት ጥር መጀመሪያ የውህደት መስራች ጉባያቸውን በማድረግ የአርበኞችና ግንቦት ሰባት ዲሞክራሲያዊ ግንባር ይመሰርታሉ ተብሎ ሲጠበቅ ውህደቱን የአርበኞች ግንቦት ሰባት ደምህት እና ሻእቢያ ሰራዊቶች ሊያጅቡት ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል ሲሉ ምንጮቹ ከአስመራ ገልጸዋል:: እንደ ደምሕት እና ኦነግ እንዲሁም የጋምቤላ ቤንሻንጉል እና አፋር ነጻ አውጪዎች በውህደቱ እንዳይሳተፉ ተደርጓል ያሉት የአስመራ ምንጮች ሻእቢያ የጎሳ ድርጅቶችን ለአላማው ስለሚተቀምባቸው ከአንድነት ሃይሎች ጋር እንዲዋሃዱ አይፈሊግም ሲሉ ተናግረዋል::(በዚህ ጉዳይ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ምንጮቹ አሁን እንዳይጻፍ ጠይቀዋል::) የአይሮፕላን ወጪያቸውን ሸፍነው አስነራ የደረሱት ነጻ አውጪዎች በሻእቢያ አስመራ ከተማ ውስጥ ሙሉ ወጪያቸው ሲሸፈን የመብራት አገልግሎት እንዳይቋረጥባቸው ጄኔራተር በመትከል እና እንዲሁም የደህንነት እና የጸጥታ ጥበቃ በማድረግ ላይ እንደሆነ ምንጮቹ ሲናገሩ በግንባር ያገኟቸው የግንቦት ሰባት ሰዎች ለጊዜው ዝርዝር ምረጃ ሊሰጡ ፈቃደኞች እንዳልሆኑ ገልጸዋል:: በውህደቱ ዙሪያ በአርማጮ በረሃ ያሉትን የአማራ ፎርስ ሰራዊት አመራሮችን አነጋግሬቸው እንደመለሱልኝ ከሆነ ክታሰሩ አባሎቶቻችን ውጪ በአስመራ ያለንን ሃይል ያስወጣን እና ከሻእቢያ ጋር ያለውን ግንኙነት ዘግተናል ሲሉ የገለጹ ሲሆን ካሁን በፊት ባወጡት መግለጫ ከአስመራ መንግስት ጋር ሆኖ ዪትዮጵያን ህዝብ ነጻነት ማሰብ ስህተት መፍጠር ነው ሲሉ ገልጸው ነበር::በአስመራ በኩል የተዘጋጁትን ነጻ አውጪዎች የተሳካ ቀሪ ዘመን እየተመኘው ቀሪ ዝርዝር ዘገባ ይዤ ለመመለስ ቃል እገባለሁ:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

MINILIK SALSAWI


 
 
 

Comments


    ሰባስቶፖል የመይሳው 
ኢትዮጵያዊነት ወይም ሞት !

ጋዜጠኞች ይፈቱ 

ጦማርያኑ ይፈቱ 

ፖለቲከኞች ይፈቱ 

ወያኔ ይውረድ 

ብሔራዊ ውርደት በቃ 

   አንድነት ለነጻነት  
  ይከታተሉን 
  • Facebook Basic Black
  • Twitter Basic Black
  • Google+ Basic Black

ተዛማጅ ገጾች 

news
news
g7pf news
arbegnoch

         ያነበቡትን ወደዉታል ? አንግዲያውስ ላንባቢዎች አዳዲስ መረጃዎችን ለማቅረብ ይተባበሩን ..ኢትዮጵያኒዝም 

Donate with PayPal

© 2023 by "This Just In". Proudly created with Wix.com

bottom of page