top of page
Search

ሰበር ዜና-የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዛግብት እና መፃህፍት ቤት በስሩ ለረጅም ጊዜ የነበሩትን በፈረንሳይኛ፣ስፓኒሽ፣ፖላንድ፣ጀርመንኛ ወዘተ ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ የተፃ

  • Writer: sepastopol
    sepastopol
  • Nov 12, 2014
  • 1 min read

የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዛግብት እና መፃህፍት ቤት መፃሕፍቱን የሚሸጠው በጨረታ ጭምርም ነው።ዛሬ ህዳር 2/2007 ዓም ሸገር ራድዮ በምሽቱ ዜና ላይእንደዘገበው ብሔራዊ በተመዛግብት እና መፃህፍት ቤቱ መፃሕፍቱን ለመሸጡ የተሰጠው ምክንያት ''ቦታ ስለጠበበን ሌሎች ቅጂዎች ማስቀመጫ ስላጣን ለመሸጥ ወስነናል ሌላ ምክንያት የለም'' ማለታቸውን ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመስርያቤቱ ሰራተኛ በቀጥታ ለራድዮ ጣብያው ሲናገሩ አስደምጧል።

ስለኢትዮጵያ ታሪክ የተጻፉት እነኝህ መፃህፍት በሌላው ዓለም በቀላሉ የማይገኙ እና የተፃፉትም ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ ብቻ መሆኑን እያወቁ ''ቦታ አጣበቡ'' ተብለው ሽያጭ ላይ ናቸው። በጣም የሚገርም ነው።ቦታ ጠበበን ተብሎ ለዘመናት የተከማቹ መፃህፍት እንዲሸጡ የወሰነው ኃላፊ ኢትዮጵያዊ ነው? አሁን በጨረታ ለመግዛት የአንዱ ሀገር ሙዝየም ወይንም መፃህፍት ቤት በጅምላ ሊገዛው እንደሚችል ትልቅ ስጋት ፈጥሯል።ይህ ማለት ነገ ለምርምር ኢትዮጵያውያን ወደ ገዛው ሀገር ብዙ የውጭ ምንዛሪ እየከፈሉ ይሄዳሉ ማለት ነው።ዛሬ የብሔራዊ መዛግብት ሰራተኞች ስፓኒሽ፣ፖላንድኛ፣ጀርመንኛ ባይችሉ ነገ እነኝህን ቋንቋዎች የሚችል ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያ አታፈራም? ወይንም ነገ የሚችል ትውልድ አይነሳም? በምን መለክያ ነው የሀገር እና የህዝብ ሀብት ለጨረታ የሚቀርቡት?

እዚህ አውሮፓ ለምሳሌ ስዊድን እና ኖርዌይ ውስጥ ያሉ ብሔራዊ መዛግብት እና ትልቁ የህዝብ መፃህፍት ቤት በየትኛውም ሀገር የታተሙ መፃህፍት፣መፅሄቶች እና ጋዜጦች በየትኛውም ቋንቋ ቢታተሙ በጀት መድበው ይገዛሉ። ለምሳሌ ኢትዮጵያ የሚታተም ማናቸውም መፅሐፍ እና ጋዜጣ አዲስ ዘመንን ጨምሮ ከወር ወር ተከታትለው ይገዛሉ ያስቀምጣሉ።ያንን ቋንቋ የሚናገር ኖረ፣ አለኖረ የሚል ጥያቄ የለም።

አሁን በተለይ ጋዜጦቹ ዲጂታል ከሆኑ ቀን በቀን እየቀዱ ፋይል ያደርጋሉ።እነኝህ ፅሁፎች ነገ ገንዘብ ብቻ ሳይሆኑ ትልቅ የመመራመርያ መሳርያም ናቸው። ኢትዮጵያ ግን ያውም ስለራሷ የተፃፉትን መፃህፍት ''ቦታ ጠበበኝ'' የሚሉ ከንቱዎች ለጨረታ አቀረቡት።ምናለ ቢያንስ ለዩንቨርስቲዎች በአደራ ቢሰጡ? የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የኢትዮጵያ ጥናት እና ምርምር ኢንስቲትዩት እነኝህን መፃህፍት መያዝ አንዱ የስራው አካል አይደለም? ለምን እንዲሸጡ ተወሰነ?

ምናለ ኢትዮጵያን መጥላታችሁን በልኩ ብታደርጉልን? በነገራችን ላይ መፃሕፍቱን ለረጅም ጊዜ ሲያከማች የነበረው ይሄው ዛሬ ለመሸጥ የሚያስማማው መስርያቤት መሆኑን ይታወቃል።ኢትዮጵያን ያላችሁ መፃሕፍቱን አድኑ!!!

ጉዳያችን

ህዳር 3/2007 ዓም (ኖቬምበር 12/2014)

 
 
 

Comments


    ሰባስቶፖል የመይሳው 
ኢትዮጵያዊነት ወይም ሞት !

ጋዜጠኞች ይፈቱ 

ጦማርያኑ ይፈቱ 

ፖለቲከኞች ይፈቱ 

ወያኔ ይውረድ 

ብሔራዊ ውርደት በቃ 

   አንድነት ለነጻነት  
  ይከታተሉን 
  • Facebook Basic Black
  • Twitter Basic Black
  • Google+ Basic Black

ተዛማጅ ገጾች 

news
news
g7pf news
arbegnoch

         ያነበቡትን ወደዉታል ? አንግዲያውስ ላንባቢዎች አዳዲስ መረጃዎችን ለማቅረብ ይተባበሩን ..ኢትዮጵያኒዝም 

Donate with PayPal

© 2023 by "This Just In". Proudly created with Wix.com

bottom of page