top of page

ኤርሚያስ ለገሰ ስለ ክንፈ ሚካኤል ደበበ(አበበ ቀስቶ)

  • Oct 17, 2014
  • 1 min read

ኤርሚያስ ለገሰ ስለ ክንፈ ሚካኤል ደበበ(አበበ ቀስቶ) ጀግንነት በመፅሃፉ ላይ በገፅ 65 የሰጠው ምስክርነት "አበበ ቀስቶ ገራሚ ሰው ነው በካድሬነት ዘመኔ ኢህአዲግን እሚንቅ እንደሱ አጋጥሞኝ አያውቅም። ብዙሃኑ በፍራቻ አቅማዳ ውስጥ ተደብቆ በነበረበት ሰአት ኢህአዲግን በአደባባይ በመቃወም፣ ሌቦችን በማጋለጥ ፋና ወጊ ነበር።ስለብዙ ባለስልጣን የማያውቀው ምስጢር የለም።ኢህአዲግ አበበ በተወዳደረበት ወረዳ ምንም ድምፅ እንደማያገኝ ሲረዳ ከምርጫው ፉክክር እሱን ገለል የሚሉበት አማራጮች ታሰቡ እሱን ማስፈራራት የሚታሰብ አልነበረም ምድር ቢንቀጠቀጥ የሚፈራ ሰው አይደለም። በቁጥጥር ስር ለማዋል ደግሞ ወንጀል ሲሰራ እጅ ከፍንጅ መያዝአለበት ስለዚህ የቀረው የመጨረሻ አማራጭ በገንዘብ መደለል ሆነ ለአበበ 50,000 ብር ተመደበለት ይህን ብር አግባብቶ ለመስጠት ዳኛ ልኡል ገ/ማርያምና ኪሮስ ተመራጭ ሆኑ ዳኛ ልኡል የህውሀት አባል ሲሆን በኢህአዲግ ከፍተኛ አመኔታ እሚጣልበትና ትላልቅ ፖለቲካ ቀመስ ጉዳዮችን የሚመለከት ነው(የቴዲ አፍሮን ክስ ውሳኔ ያስተላለፈው ይህ ዳኛ ነው) ዳኛ ልኡል እና ኪሮስ በቀበሌያቸው መዝናኛ ክበብ አብረውት መታየት ጀመሩ። እያደር ለኢህአዲግ ምርጫ ኮሚቴ ተስፋ ሰጪ መልእክቶች መሰማት ቀጠሉ ምርጫው ሊካሄድ ጥቂት ቀናት ሲቀረው አበበ ቀስቶ ውሳኔውን እንዲህ በማለት አሳወቀ"....የተጋበዝኩትና ብራችሁን የተጠቀምኩት እናንተ ጋር የማይነጥፍ የብር ማምረቻ ስላለ ነው ምርጫ የምወዳደረው ግን ለገንዘብ ሳይሆን ይህን አስከፊ ስርአት ለመጣልና ለነፃነቴ ነው። በዚህ ላይ ለመደራደር ህሊናዬ አይፈቅድም።" አበበ ቀስቶ ተወዳደረ አሸንፎ ተሸነፈ። ይህ ጀግና ወያኔን በማሸበሩ አሸባሪ ተብሎ በአሁን ሰአት በዝዋይ ወህኒ ቤት ህክምና ተከልክሎ በስቃይ ላይ ነው!

 
 
 

Comments


    ሰባስቶፖል የመይሳው 
ኢትዮጵያዊነት ወይም ሞት !

ጋዜጠኞች ይፈቱ 

ጦማርያኑ ይፈቱ 

ፖለቲከኞች ይፈቱ 

ወያኔ ይውረድ 

ብሔራዊ ውርደት በቃ 

   አንድነት ለነጻነት  
  ይከታተሉን 
  • Facebook Basic Black
  • Twitter Basic Black
  • Google+ Basic Black

ተዛማጅ ገጾች 

news
news
g7pf news
arbegnoch

         ያነበቡትን ወደዉታል ? አንግዲያውስ ላንባቢዎች አዳዲስ መረጃዎችን ለማቅረብ ይተባበሩን ..ኢትዮጵያኒዝም 

Donate with PayPal

© 2023 by "This Just In". Proudly created with Wix.com

bottom of page