top of page

ናይሮቢ የሚገኘውን የጋዜጠኛ ሚሊዩን ሹሩቤ አስከሬን ወያኔ ወሰደው።

  • Oct 16, 2014
  • 1 min read

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) የጋዜጠኞች ፕሬዝዳንት ነኝ ብሎ ራሱን የሰየመው አንተነህ አብርሃም ለጋዜጠኞች እየደወለ እየዛተ ነው፡፡ በቅርቡ የስደቱን አለም የተቀላቀለው እና ባጋጠመው የምግብ መመረዝ ድንገት ከዚህ አለም በሞት የተለየው የማራኪ መጽሄት ማኔጂንግ ዳይሪክተር እና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ሚሊዮን ሹሩቤ አስከሬን ወያኔ በጉልበት መውሰዱን ከናይሮቢ ተሰምቷል። በወያኒ ሴራ በተመረዘ ምግብ ሞቷል የሚባለው እና ለሞቱን መንስኤ እንደሆነች የምትጠረጠረው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማት ባልቤት የሆነች ግለሰብ ራሷን የሰወረች መሆኑ ሲታወቅ ጋዚጠኛ ሚሊዮንን ከዚመሞቱ ቀድሞ በየምሽቱ እየመጣች በዘመናዊ መኪና ፒክ እያደረገቸው ስታዝናናው እንደነበር ይታወቃል።የሚሊዮን ሹሩቤን አስከሬን ወደ ሃገር ቤት ለመላክ ሲሰሩ የነበሩ ስደተኛ ጋዜጠኞች ፕሮሰስ ሲያደርጉበት የነበረውን ዶክመንት አስረክበዋል፡፡ የጋዜጠኞች ፕሬዝዳንት ነኝ ብሎ ራሱን የሰየመው አንተነህ አብርሃም ለጋዜጠኞች እየደወለ እየዛተ ነው፡፡ መንግስት ጋዜጠኞችን አላሰደድኩም በማለት የጀመረውን ድራማ በአሳዛኝ ሁኔታ አስክሬን ቁጭ ብለው የሚጠብቁት ቤተሰብ ላይ ድራማ መስራት ስለጀመረና አስከሬኑን ወደ ሃገር ቤት ለመላክ እየሰራ ያለን ጋዜጠኞች ለደህንነታችን አስጊ ሁኔታ በመፈጠሩ ካሁን በኋላ የጋዜጠኛ ሚሊዮን አስክሬን መላክ ጉዳይ ከእኛ ቁጥጥር ውጭ መሆኑን ሃገር ውስጥና ከሀገር ውጪ ያላችሁ የስራ ባልደረቦቻችን እንዲሁም መላው ህዝብ እንድታውቁት ይሁን ፡፡ ከቤተሰብ ተወክለው መጡ የተባሉት ሰዎች የማናውቃቸው ሲሆን አስከሬኑን ለመውሰድ ሀገር ውስጥ ገብታለች የተባለችው የጋዜጠኛ ሚሊዮን ሹሩቤ እህት የት እንዳለች የማናውቅና እህቱንም ማን እንደተቀበላት የምናውቀው ነገር አለመኖሩን ማሳወቅ እንፈልጋለን ፡፡የሚሊዮን ሹሩቤን ሞት ተከትሎ በኪንይ የምግኙ ስደተኛ ጋዜጠኞች በከፍተኛ አደጋ ውስጥ እና ክትትል ስር መግባታቸው ታውቋል።

 
 
 

Comments


    ሰባስቶፖል የመይሳው 
ኢትዮጵያዊነት ወይም ሞት !

ጋዜጠኞች ይፈቱ 

ጦማርያኑ ይፈቱ 

ፖለቲከኞች ይፈቱ 

ወያኔ ይውረድ 

ብሔራዊ ውርደት በቃ 

   አንድነት ለነጻነት  
  ይከታተሉን 
  • Facebook Basic Black
  • Twitter Basic Black
  • Google+ Basic Black

ተዛማጅ ገጾች 

news
news
g7pf news
arbegnoch

         ያነበቡትን ወደዉታል ? አንግዲያውስ ላንባቢዎች አዳዲስ መረጃዎችን ለማቅረብ ይተባበሩን ..ኢትዮጵያኒዝም 

Donate with PayPal

© 2023 by "This Just In". Proudly created with Wix.com

bottom of page