ይለያል ዘንድሮ የወያኔ ኑሮ DC
- sepastopol
- Oct 6, 2014
- 1 min read
ይለያል ማክሰኞ " ባንዲራ ጨርቅ ነው" መለስ ዜናዊ " ባንዲራችን ተዋረደ" የህወሀት ደጋፊዎች ማክሰኞ በአሜሪካ የህወሀት ደጋፊዎች በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደጃፍ ሰልፍ ሊያደርጉ ነው። የአሜሪካን መንግስት ለኤምባሲው ጥበቃ አላደረገም በሚል ተቃውሞ ለማሰማት ሰሞኑን በቅስቀሳ ተጠምደው ነው የሰነበቱት። የሰኞው የኤምባሲው ትዕይንት ክፉኛ አበሳጭቷቸዋል፡፡ እናም መለስ ጨርቅ ነው ያላትን ባንዲራ እያነሱ በቅስቀሳ ተጠምደዋል። ጭራሽ " አባቶቻችን የወደቁለትን" ዓይነት ቀረርቶ ሁሉ እያስገቡ ለማክሰኞው ሰልፍ እየቀሰቀሱ ናቸው። ዲሲን የጦርነት አውድማ እናደርጋታለን ብለዋል። ኢትዮጵያውያን ደግሞ የአጸፋ እርምጃ ለመውሰድ በተመሳሳይ ቀን፡ በተመሳሳይ ቦታ፡ በተመሳሳይ ሰዓት ተጠራርተዋል፡፡ ማክሰኞ ይለይለታል ህወሀቶች ከየስቴቱ ይመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። የዲሲ ኢትዮጵያውያን " ይለያል ዘንድሮ የወያኔ ኑሮ" ን ከፍ አድርገው እያሰሙ ናቸው፡፡
Comments