top of page

በዋሽንግተን ዲሲ ጥቂት የወያኔ ኢምባሲ ሠራተኞች እና ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በየፊናቸው ሰልፍ ወጡ

  • Writer: sepastopol
    sepastopol
  • Oct 7, 2014
  • 2 min read

ጥቂት የሕወሓት የዋሽንግተን ዲሲ ኢምባሲ ሠራተኞች እና አንዳንድ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጉሮሮ ተነጥቆ በሚሰጣቸው የስኮላርሺፕ ገንዘብ የደለቡ የስርዓቱ ደጋፊዎች በሰለሞን ተካልኝ መሪነት በስቴት ዲፓርትመንት ደጃፍ ዛሬ ሰልፍ ወጡ። በተመሳሳይም የአሜሪካ መንግስት በዋሽንግተን ዲሲ የሕወሓት ኢምባሲ ውስጥ በኢትዮጵያውያን ላይ ጥይት የተኮሰውን የስርዓቱን ተላላኪ ከሃገሩ በማባረሩ ለዚህም ምስጋና ለማቅረብ ኢትዮጵያውያን በስቴት ዲፓርትመንት ተመሳሳይ ሰልፍ አድርገዋል።

ሃገር ወዳዱ ኢትዮጵያውያን ልሙጡን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ በመያዝ እንዲሁም የሕወሃት ደጋፊዎች በመሃሉ ላይ ሰማያዊ ኮከብ ያለብትን እና ብዙዎች አይወክለኝም የሚሉትን ባንዲራ ይዘው ሰልፍ የወጡ ሲሆን በስቴት ዲፓርትመንት ደጃፍ በየፊናቸው ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ አርፍደዋል። የሕወሓት ደጋፊዎች “ኢምባሲያችን ተደፈረ፣ ባንዲራችን ተዋረደ” በሚል ሰልፍ የጠሩ ሲሆን ኢትዮጵያውያኑ በበኩላቸው ሃገራችንን ከነክብሯና ባንዲራዋ ያዋረደው ገዢው የሕወሓት መንግስት ነው በማለት የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያውያኑ ላይ ጥይት የተኮሰውን ግለሰብ ወደሃገሩ በማባረሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ቀድሞ ከተቃዋሚዎች ጋር የነበረውና ተገልብጦ የሕወሓት ደጋፊ ሆኖ ቁጭ ያለው ሰለሞን ተካልኝ የሕወሓት ደጋፊዎችን ሰልፍ የመራ ሲሆን፤ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያኑም ሰለሞን የሕወሓትን መንግስት ይቃወምበት የነበረውን “ሁሉም ዜሮ ዜሮ” የሚለውን ዘፈኑን ከፍተው ለምስጋናው ሰልፍ ማድመቂያ አድርገውታል። ሰለሞን ጥቂት የኢምባሲ ሠራተኞችን ሰብስቦ ራሱን በራሱ በማይክራፎን “ሰለሞን እንዲህ የሚሆነው ለሃገሩ ለባንዲራው ነው፤” ያስባለ ሲሆን የሕወሃት ሰልፍ አላማውን ስቶ እንደተባለው የአሜሪካ መንግስትን መቃወሚያ ሳይሆን የሰለሞን ተካልኝ ሞራል መገንቢያና ማወደሻ ሆኖ አልፏል ሲሉ በአካባቢው የነበሩ ኢትዮጵያውያን ለዘ-ሐበሻ ዘጋቢ ተናግረዋል።

በዋሽንግተን ዲሲ መንግስትን የሚደግፍም ሆነ የሚቃወመው በአንድ ቦታ ቆሞ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጉ ለራሳቸው ለወያኔ ደጋፊዎች ሊያሳፍራቸው ይገባል የሚሉት አንድ አስተያየት ሰጪ “እኛ እንዲህ ያለው ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ነው ትግላችን። ሕወሓትን የሚደግፍም የሚቃወምም በእኩል እንዲታይ። ሆኖም በሃገራችን መንግስትን መቃወም የማንችል መሆኑን የወያኔ ደጋፊዎች እያወቁት ሰሜን አሜሪካ ላይ ከእኛ እኩል ሰልፍ መውጣታቸውና የአሜሪካ መንግስት የመናገር መብትን መፍቀዱ የሚደግፉት መንግስት የሚሰራው ስህተት እንደሆነና እንዲማሩበት ትልቁን ሚና ይጫወታል: ሆኖም ግን ደጋፊዎቹ በአሜሪካ ሃገር ያገኙትን ነጻነት እኛ ሃገራችን ላይ እንድናገኝ ስለማይፈልጉ ከኛ እኲል ዲሞክራሲያዊ መንግስት እየደገፍን ነው ብለው መውጣታቸው ሊያሳፍራቸው ይገባል። ልክ እንደአሜሪካ መንግስት ሁሉ የሚደግፉት የሕወሓት መንግስት ተቃራኒ ሃሳብ ያላቸውን ወገኖች እኩል የመናገር መብት ሊሰጥ እንደሚገባ ከዚህ ሰልፍ ሊማሩ ይገባል” ብለውናል።


 
 
 

Comentarios


    ሰባስቶፖል የመይሳው 
ኢትዮጵያዊነት ወይም ሞት !

ጋዜጠኞች ይፈቱ 

ጦማርያኑ ይፈቱ 

ፖለቲከኞች ይፈቱ 

ወያኔ ይውረድ 

ብሔራዊ ውርደት በቃ 

   አንድነት ለነጻነት  
  ይከታተሉን 
  • Facebook Basic Black
  • Twitter Basic Black
  • Google+ Basic Black

ተዛማጅ ገጾች 

news
news
g7pf news
arbegnoch

         ያነበቡትን ወደዉታል ? አንግዲያውስ ላንባቢዎች አዳዲስ መረጃዎችን ለማቅረብ ይተባበሩን ..ኢትዮጵያኒዝም 

Donate with PayPal

© 2023 by "This Just In". Proudly created with Wix.com

bottom of page