ሰላም ለመላው የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያየድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አባላት እንዲሁም ለመላው ኢትዮጵያውያን በኖርዌይ በሙሉ!!
- sepastopol
- Oct 7, 2014
- 1 min read
ሰላም ለመላው የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያየድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አባላት እንዲሁም ለመላው ኢትዮጵያውያን በኖርዌይ በሙሉ!!
ኢንቨስትመንት በኢትዮጵያ /“INVEST IN ETHIOPIA”/ በሚል ርእስ በኦክቶበር 16/2014 ኦስሎ ላይ ሴሚናር ይካሀዳል፥፥ ዝግጅቱቱን ያዘጋጀው Norwegian-African Business Association /NABA/ ሲሆን በዝግጅቱ ላይ የአምባገነኑ የወያኔው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አቶ ቴዎድሮስ አድሃኖም ገብረየስ፥ እንዲሁም የኖርዌይ አምባሳደር በኢትዮጵያ ሚ/ር አንድሪያስ ጋርደር እና አምባሳደር ወይንሸት ታደሰ የተለያዩ የኖርዌጂያን የንግድ ድርጅቶች ጋር ተገናኝተው ለመወያየትና ፓሮግራም ተይዟል፥፥
ዝግጅቱ የሚደረገው በሃሙስ ኦክቶበር 16/2014 ከ 09:00-11:30 ሲሆን ከ11፥30—12፥30 የምሳ ፕሮግራም ይኖራቸዋል፥ በመሆኑም ውድ ኢትዮጵያውያን በኖርዌይ በሙሉ እንድታውቁትና በንቃትእንድትከታተሉ እናሳስባለን፥፥
አድራሻው Confederation of Norwegian Enterprise (NHO) ማለትም Næringslivets Hus Middelthuns gate 27 Majorstuen, Oslo ሲሆን ተጨማሪ መረጃ በቅርብ ቀን
ለበለጠ መረጃ፥ http://norwegianafrican.no/…/16th-of-october-invest-in-ethi…
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
Comments