top of page

ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ አውቶቡስ ተገልብጦ የ17 ሰዎች ሕይወት አለፈ

  • Writer: sepastopol
    sepastopol
  • Oct 5, 2014
  • 1 min read

በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሚያሰቅቅ ሁኔታ እየደረሰ ያለው የመኪና አደጋና በዚሁ ጉዳትም የሚያልቀው ሕዝብ ብዛት እጅጉን አሳሳቢ ደረጃ ላይ እየደረሰ ነው። ዛሬም ወደ አዲስ አበባ 65 መንገደኞችን ጭኖ ይጓዝ የነበረ አውቶቡስ ተገልብጦ 17 ሰዎች ወዲያውኑ መሞታቸው ታውቋል። በቅርብ ጊዜ ውስጥ እንኳ በዘ-ሐበሻ ድረገጽ ላይ ከዘገብናቸው ዘግናኝ የመኪና አደጋዎች ውስጥ፦

ከሞያሌ ወደ ሻሸመኔ የሚጓዝ አገር አቋራጭ አውቶቡስ ተገልብጦ 17 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉ፤ ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር የሚጓዝ አውቶቡስ ተገልብጦ 41 ሰዎች ማለቃቸው፤ በአዲስ አበባ ከካራ ወደ መርካቶ የሚጓዝ አውቶቡስ 15 ሜትር ጥልቀት ካለው ገደል ገብቶ የሰዎች ሕይወት ማለፉ፤ ወደ ደብረማርቆስ የሚጓዝ አውቶቡስ ተገልብጦ የ13 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱና ሌሎችም ይገኙበታል።

ዛሬ ከሃገር ቤት የተሰማው ዜና እንደሚያስረዳው ከደባርቅ ወደ አዲስ አበባ 65 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ተገልብጦ የ17 ሰዎች ህይወት አልፏል። አደጋው የደረሰው ዛሬ ከቀኑ 6:30 ላይ አውቶብሱ በአማራ ክልል፣ ደጀን ወረዳ፣ ባልበሌ ቀበሌ አካባቢ በሚገኝና 50 ሜትር ጥልቀት ባለው ገደል ገብቶ ነው።

መንግስታዊ ሚድያዎች እንደዘገቡት በዚህ አደጋ የ17 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ 37 ሰዎችም ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።


 
 
 

Comentarios


    ሰባስቶፖል የመይሳው 
ኢትዮጵያዊነት ወይም ሞት !

ጋዜጠኞች ይፈቱ 

ጦማርያኑ ይፈቱ 

ፖለቲከኞች ይፈቱ 

ወያኔ ይውረድ 

ብሔራዊ ውርደት በቃ 

   አንድነት ለነጻነት  
  ይከታተሉን 
  • Facebook Basic Black
  • Twitter Basic Black
  • Google+ Basic Black

ተዛማጅ ገጾች 

news
news
g7pf news
arbegnoch

         ያነበቡትን ወደዉታል ? አንግዲያውስ ላንባቢዎች አዳዲስ መረጃዎችን ለማቅረብ ይተባበሩን ..ኢትዮጵያኒዝም 

Donate with PayPal

© 2023 by "This Just In". Proudly created with Wix.com

bottom of page