top of page

ከጋምቤላ ክልል ሜጢ የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን ወደ አዲስ አበባ ከመጡት ውስጥ ስምንቱ ታስረዋል

  • Writer: sepastopol
    sepastopol
  • Oct 6, 2014
  • 1 min read

መኢአድ በመጪው ሰኞ አለም አቀፍ ጋዜጣዊ መግለጫ እሰጣለሁ አለ። – የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ተፈናቃዮችን እየተመላለሱ በሰብአዊነት በመርዳት እና በማጽናናት ላይ ናቸው። – የአዲስ አበባ ሆስፒታሎች ተጎጂዎችን ለማጉላላት ያደረጉት ሙከራ በመኢአድ አባላት ጥረት ክሽፏል። – የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ተፈናቃዮቹን እንዲጎበኙ መኢአድ ጥሪውን አቅርቧል።

ባለፉት ሳምንታት በምእራብ ኢትዮጵያ በጋምቤላ ክልል በሚጤ ከተማ ከመሬት ቅርሚያ ጋር በተያያዘ በወያኔ ካድሬዎች ቀስቃሽነት ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ የተደረጉ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ችግር ውስጥ በቴፒ የሚገኙ ሲሆን የተወሰኑት ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በመኢአድ ቢሮ ውስጥ ተጠልለው የተጎዱት በመታከም ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል።

ወደ አዲስ አበባ ከደረሱት ተፈናቃዮች እና ተጎጂዎች መካክል መኢአድ ቢሮ ሳይደርሱ ከመንገድ ላይ ታፍነው የተወሰዱ ስምንት ተፈናቃዮች በስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እንደሚገኙ ጉዳዩን የሚከታተሉ የጉዳዩ ባለቤቶች በሰጡት መረጃ የታወቀ ሲሆን ሁኔታውን ለማረጋገጥ ተሞክሮ ፖሊስ መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። እንዲሁም ሲፈናቀሉ ጉዳት የደረሰባቸው አዲስ አበባ የደረሱ ተጎጂዎች ህክምና እንዲያገኙ ለማድረግ ከፍተኛ የሆነ ውጣ ውረድ በሆስፒታሎች የደረሰባቸው ሲሆን የቀበሌ መታወቂያ ወይንም የተፈናቀሉ መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ከክልሉ አምጡ በማለት ለማጉላላት የተደረገው ጥረት በመኢአድ አባላት ብርቱ ጥረት መክሸፉ ሲታወቅ ተጎጂዎቹ ህክምና እንዲያገኙ ተደርጓውል።

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች መኢአድ ባደረገው ጥሪ መሰረት አስፈላጊዎን ሰብአዊ እርዳታ እያደረጉ ሲሆን አሁንም የህዝቡን እርዳታ እና አጋርነት ለተጎጂዎቹ በተከታታይነት እንዲቀጥል እንዲሁም የሃገር ቢት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ተጎጂዎችን በመጎብኘት አጋርነታቸውን እንዲያረጋግጡ በድጋሚ መኢአድ ጥሪ አቅርቧል። በመጭው ሰኞ አለም አቀፍ ጋዜጣዊ መግለጫ በቢሮው እንደሚሰጥ ያስታወቀው መኢአድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እያደረጉ ያሉትን ሰብአዊ እርዳታ እና መጽናናት በማድነቅ በዚህ እንዲቀጥሉ የሰብአዊነት ጥሪውን አቅርቧል።

Source/zehabesha.com

Posted by/Lemlem Kebede


 
 
 

Комментарии


    ሰባስቶፖል የመይሳው 
ኢትዮጵያዊነት ወይም ሞት !

ጋዜጠኞች ይፈቱ 

ጦማርያኑ ይፈቱ 

ፖለቲከኞች ይፈቱ 

ወያኔ ይውረድ 

ብሔራዊ ውርደት በቃ 

   አንድነት ለነጻነት  
  ይከታተሉን 
  • Facebook Basic Black
  • Twitter Basic Black
  • Google+ Basic Black

ተዛማጅ ገጾች 

news
news
g7pf news
arbegnoch

         ያነበቡትን ወደዉታል ? አንግዲያውስ ላንባቢዎች አዳዲስ መረጃዎችን ለማቅረብ ይተባበሩን ..ኢትዮጵያኒዝም 

Donate with PayPal

© 2023 by "This Just In". Proudly created with Wix.com

bottom of page