top of page

የ‹‹ፍትህ አካላት›› ስብሰባ በአቶ በረከት ማስጠንቀቂያ ተጠናቀቀ

  • Sep 25, 2014
  • 1 min read

የ‹‹ፍትህ አካላት›› ስብሰባ በአቶ በረከት ማስጠንቀቂያ ተጠናቀቀ Septeber25,2014 • ‹‹ የተባላችሁትን መስራት አለባችሁ፣ ግዴታችሁም ነው›› አቶ በረከት • ‹‹በቀጭን ትዕዛዝ ነው የምንሰራው፣ የተጻፈ ህግ አይሰራም›› ዳኞች ከሁለት ሳምንት በፊት በአቶ በረከት ስምኦን የተከፈተውና 15 ቀን የፈጀው ባህርዳር ላይ የተደረገው የ‹‹ፍትህ አካላት›› ስብሰባ ትናንት መስከረም 14/2007 ዓ.ም በአቶ በረከት ስምኦን ማስጠንቀቂያ መጠናቀቁን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡ ስብሰባውን የዘጉት አቶ በረከት ስምኦን ‹‹ፖሊስ፣ አቀቤ ህግና ዳኛ ከአስፈጻሚው (ከካቢኔው) ጋር ተስማምቶና እጅና ጓንት ሆኖ መስራ አለበት፡፡ ይህ ነው ልማታዊ የፍትህ ስርዓት፡፡›› ማለታቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ በተቃራኒው ተሰብሳቢዎቹ ‹‹ከአስፈጻሚው አካል ጋር እጅና ጓንት ሆናችሁ ስሩ ማለት የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት እንዲኖር መፍቀድ ነው፣ ሊሰበስበን ይገባ የነበረው የካቢኔ አካል ሳይሆን የራሳችን ተቋም የሆነው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው፣ ስልጠናው በራሱ የዳኝነት ስርዓቱን፣ ተቋሙንና ግለሰባዊ መብታችንን የጣሰ ነው፡፡›› ሲሉ ቅሬታቸውን እንደገለጹ ታውቋል፡፡ በአንጻሩ አቶ በረከት ‹‹አሜሪካን ጨምሮ በየትኛውም አገር የፍትህ ስርዓት አስፈጻሚ አካሉ ጣልቃ ይገባል፣ ይህ የምታነሱት ሀሳብ አደናቃፊ ሀሳብ ነው፣ የተባላችሁትን መስራት አለባችሁ፣ ግዴታችሁም ነው›› ማለታቸውን ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡ በስብሰባው ላይ የተገኙት ዳኞችም ‹‹በቀጭን ትዕዛዝ ነው የምንሰራው፣ አድር የተባለውን ማድረግ ነው፣ የተጻፈው ህግ አይሰራም›› በሚል የወረደላቸውን ትዕዛዝ እንደሚያስፈጽሙ ጠቁመዋል፡፡ በስብሰባው የተገኙት ሰብሳቢ ዳኛ (የተቋም ባለቤት)ና የስራ ሂደት አስተባባሪ በስብሰባው ላልተገኙት ባልደረቦቻቸው ከእነ አቶ በረከት በወረደላቸውን ትዕዛዝ መሰረት ‹‹አቅጣጫ ይሰጣሉ››ም ተብሏል፡፡ ነገረ ኢትዮጵያ


 
 
 

Comments


    ሰባስቶፖል የመይሳው 
ኢትዮጵያዊነት ወይም ሞት !

ጋዜጠኞች ይፈቱ 

ጦማርያኑ ይፈቱ 

ፖለቲከኞች ይፈቱ 

ወያኔ ይውረድ 

ብሔራዊ ውርደት በቃ 

   አንድነት ለነጻነት  
  ይከታተሉን 
  • Facebook Basic Black
  • Twitter Basic Black
  • Google+ Basic Black

ተዛማጅ ገጾች 

news
news
g7pf news
arbegnoch

         ያነበቡትን ወደዉታል ? አንግዲያውስ ላንባቢዎች አዳዲስ መረጃዎችን ለማቅረብ ይተባበሩን ..ኢትዮጵያኒዝም 

Donate with PayPal

© 2023 by "This Just In". Proudly created with Wix.com

bottom of page