top of page

ዓለምአቀፍ ጠበቆች የኢትዮጵያን ባለስልጣናት ለፍርድ ለማቅረብ እንቅስቃሴ ጀመሩ

  • Sep 20, 2014
  • 1 min read

ዓለምአቀፍ ጠበቆች የኢትዮጵያን ባለስልጣናት ለፍርድ ለማቅረብ እንቅስቃሴ ጀመሩ

በወጣት አብዱላሂ ሁሴን አማካኝነት በኢትዮጵያ የኦጋዴን ክፍል የተፈጸመውን የጦር ወንጀልና የሰብአዊ መብት ጥሰት ፊልም የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም በስዊድን ቁጥር አንድ ቴሌቪዥን በትናንትናው እለት መቅረቡን ተከትሎ አለማቀፉ ጠበቆች ጉዳዩን ወደ አለማቀፍ ፍርድ ቤት ለመውሰድ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ኢሳት በጥቅምት 5 ቀን 2005 ዜናው አስታወቀ። ወጣት አብዱላሂ ለኢሳት እንደገለጸው ፊልሙ ከተላለፈ በሁዋላ ሚዲያዎች ሰፊ ሽፋን የሰጡት ሲሆን፣ ስቴላም የተባሉ የ አይ ሲ ጄ ጠበቃ ጉዳዩን ፍርድ ቤት እንደሚያቀርብ በሬዲዮ ይፋ አድርገዋል። የስዊድን የጦር ወንጀል ኮሚሽን ፍርድ ቤትም ማስረጃዎችን በመመርመር ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ለመውሰድ ከወጣት አብዲ ጋራ ቀጠሮ ይዟል። ጠበቆቹ ጄኔቫ ካለው አይሲጄ እና ከሌሎችም የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን ጉዳዩን ወደ አለማቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ለመውሰድ እንደሚሞክሩ ኢሳት አመልክቷል። ቀደም ሲል ይፋ ከተደረገው በተጨማሪ አዳዲስ መረጃ የያዘው አዲሱ ፊልም “ልዩ ፖሊስ” እየተባለ በሚጠራው ሀይል የተፈጸመ የዘር ማጥፋት ወንጀልና የክልሉን ፕሬዚዳንት የተቸች አንዲት ሴት በኦበነግ አባልነት ስትፈረጅ የሚያሳይ መረጃ ተካቶበታል ። የክልሉ ፖሊስ ሀላፊ በእስር ላይ የሚገኙትን ሴቶች በመድፈር ብዙ ህጻናት በእስር ቤት ውስጥ መወለዳቸውን በፖሊሶች በራሳቸው ሲነገር የሚያሳይ ፊልም መካተቱትን ወጣት አብዱላሂ ገልጿል። ፊልሙ ” የዲክታተሮች እስረኞች” የሚል ርእስ ተሰጥቶታል። ጉዳዩን በማስመልከት የአለማቀፍ የህግ ባለሙያዎች ኮሚሽን በእንግሊዝኛ ኢንተርናሽናል ኮሚሽን ኦፍ ጁሪስትስ ኮሚሽነር የሆኑት ስቴላ ጋርደ ለኢሳት እንደገለጹት የወንጀሉን ፈጻሚዎች ወደ ፍርድ ለማቅርብ የሚችሉትን ሁሉ እንደሚጥሩ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ የአለማቀፍ ወንጀል (ICC) ፈራሚ አገር ባለመሆኑዋ ማስረጃውን በቀጥታ ለፍርድ ቤቱ መላክ እንደማይቻል የገለጹት ኪሚሽነር ጋርደ፣ ይሁን እንጅ ሰቆቃን ለመከላከል የተቋቋመው ኮሚቴ (Committee Against Torture) ፈራሚ አገር በመሆኑ ጉዳዩን በዚሁ በኩል ለመከታተል እና የስዊድን ፖሊስ ምርመራ ጀምሮ እርምጃ ለመውሰድ እንዲችሉ ጥረት እንደሚያደርጉ ከኢሳት ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።

 
 
 

Comments


    ሰባስቶፖል የመይሳው 
ኢትዮጵያዊነት ወይም ሞት !

ጋዜጠኞች ይፈቱ 

ጦማርያኑ ይፈቱ 

ፖለቲከኞች ይፈቱ 

ወያኔ ይውረድ 

ብሔራዊ ውርደት በቃ 

   አንድነት ለነጻነት  
  ይከታተሉን 
  • Facebook Basic Black
  • Twitter Basic Black
  • Google+ Basic Black

ተዛማጅ ገጾች 

news
news
g7pf news
arbegnoch

         ያነበቡትን ወደዉታል ? አንግዲያውስ ላንባቢዎች አዳዲስ መረጃዎችን ለማቅረብ ይተባበሩን ..ኢትዮጵያኒዝም 

Donate with PayPal

© 2023 by "This Just In". Proudly created with Wix.com

bottom of page